Get Mystery Box with random crypto!

በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ የተዋህዶ ልጆች በያላችሁበት እንኳን ለግንቦት ልደታ ለማርያም አደረ | Hagerie Media

በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ የተዋህዶ ልጆች በያላችሁበት እንኳን ለግንቦት ልደታ ለማርያም አደረሳችሁ
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች (ኢሳ 7፡14)›› ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ የአምላካችን እግዚአብሔር ረድኤት በረከት አይለየን፡፡አሜን፡፡