Get Mystery Box with random crypto!

#hafi_ነኝ እስኪ እናስብ ዝም ብለን የምንጠላው ሰው ከሩቅ የምናውቀው አንዳ | 🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤

#hafi_ነኝ
እስኪ እናስብ
ዝም ብለን የምንጠላው ሰው

ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?

"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"

"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"

"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"

ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ::


ፈጣሪ እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት ነበረው:: እርሱ ግን እንዲሁ ወደደን:: ከእኛ ምንም ባያገኝም ስለ እኛ ያለው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (unconditional love) ነበረ:: እርሱ እንዲሁ ወዶናል እኛ ግን እንዲሁ ሰው እንጠላለን::
ያለ ምክንያት መውደድ ቢያቅተን እንኳን ያለ ምክንያት መጥላታችን (unconditional hate) ቢቀር ምናለ?
የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል::

እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን ፈጣሪ ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "ፈጣሪ መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም::

ቆም ብለን እስኪ እናስብ
ልባችን ለጥላቻ ሳይሆን ለፍቅር ክፍት እናድርገው

ሀሳባችሁን በ @hafizy_25 አድርሱን
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @hafila25
⇨ @hafila25
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───