Get Mystery Box with random crypto!

#hafi_ነኝ እስኪ እናስብ በሳሉት ቢላዋ..! አስገራሚ ታሪክ አንዱ ሚስቱን ይመታታል | 🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤

#hafi_ነኝ
እስኪ እናስብ
በሳሉት ቢላዋ..!

አስገራሚ ታሪክ አንዱ ሚስቱን ይመታታል። በአጋጣሚ ሊገድላት ሳያስብ በእጁ ትሞትበታለች፡፡ ጉዳዩ ይፋ ወጥቶ ዕዳ እንዳይኾንበት ምን ማድረግ እንዳለበት ያስባል። አስቦ አሰላስሎ በስተመጨረሻም አንድ ሀሳብ መጣለት። እርሱም ወደሰፈራቸው አዋቂ ነኝ ባይ ሰው ጋር መሄድ ነበር። ታዲያ ይሄ አዋቂ ተብዬ ሰውም መፍትሄ የሚለውን ሀሳብ እንዲህ ሲል ይመክረዋል።

ደጅህ ላይ ተቀምጥና ቆንጆ ወጣት ሲያልፍ ካየህ "አንዳች የምታግዘኝ ነገር አለ" በለውና ወደ ቤትህ አስገባው።ከዚያም ግደለውና ከባለቤትህ እሬሳ ጋር አጠገብ ለአጠገብ አጋድመው። የርሷን ቤተሰቦች ጥራና "ከዚህ ወጣት ጋር ሲያመነዝሩ ስመለከት እራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ እርምጃ ስወስድባቸው በእጄ ሞቱ” ብለህ ንገራቸው አለው።

አባ ውራውም መላ ነው ተብሎ የተነገረውን ተቀብሎ ደጃፉ ላይ ሄዶ ቁጭ ብሎ መጠባበቅ ይጀምራል። ብዙም ሳይቆይ አንድ ወጣት በአጠገቡ ሲያልፍ ተመለከተና "ወንድም አንዴ ላስቸግርህ? የሆነች ነገር እንድታግዘኝ ፈልጌህ ነበር" ብሎ አስማምቶ ወደ ቤት ያስገባዋል። እንደተመከረውም ይገድለውና ከሚስቱ ጀነዛ አጠገብ ያጋድመዋል።

የሚስቱ ቤተዘመዶች ሲመጡም በዝሙት ላይ አግኝቷቸው ራሱን መቆጣጠር አቅቶት እርምጃ እንደወሰደባቸው ይነግራቸዋል። እነርሱም ጥፋተኛ ሳያደርጉት ምክኒያቱን ይረዱትና ይተዉታል፡፡ ይሄንን የማምለጫ ዘዴ ነግሮት የነበረው ሰውዬ ገዳዩ ከምን እንደደረሰ ሊጠይቀው ቤቱ ይከሰታል። ገዳዩ ሰውዬም የመከረውን እንዳደረገና እንደተሳካለት በኩራትና በምስጋና ይነግረዋል። እስኪ የገደልከውን ልጅ አሳየኝ ብሎ አዋቂ ተብዬው ይጠይቀዋል።

ገዳዩ ወስዶ ሲያሳየውም ለካስ የተገደለው የራሱ የአዋቂ ነኝ ባዩ ልጅ ኖሯል! በሳሉት ቢለዋ መቆረጥ ይሉሃል እንደዚህ ነው! ለተንኮል ሰይፉን የሳለ እራሱ ይቆረጥበታል። ለወንድሙ ጉድጓድ የቆፈረ ራሱ ይገባበታል። የሌሎችን ነውር አደባባይ የሚበትን | የራሱ ነውር አደባባይ ይታይበታል።

@hafila25 @hafila25
@hafila25 @hafila25