Get Mystery Box with random crypto!

#hafi_ነኝ እስኪ እናስብ ደሞ ስማኝ ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለ | 🤔❤እስኪ እናስብ 🤔❤

#hafi_ነኝ
እስኪ እናስብ
ደሞ ስማኝ
ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመሥማት ጆሮ ሥጥ ማለትጅ!!
ጠንካራ ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሣትንም ልመድ ማለት እጅ!!
ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሠው ሀቅ አትለፍ ማለት እጅ!!
አትቆጣ ማለት ሥሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣህ ቶሎ ተመለሥ ማለት እጅ!!
ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነእጅ!!
ጠላትህን ውደድ ማለትጠላት ጥሩ ነው አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ሥለሚያሸንፍ እጅ!!
ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እጅ!!
እራስህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እዲኖርህ ዛሬ የምትሠራውን ስራ ውደድ ማለት እጅ!!
ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ሥለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እጅ!!
ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ሣትሠራ አትሙት ማለት እጅ!!
ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ግዜህን፣ልብህን ያለህን ነገር ሁሉ አሳልፈህ ለመሥጠት ዝግጁ ሁን ማለት እጅ!!
እውነተኛ ሁን ማለት ሠዎች ባሉበት ቦታ ብቻ እውነትን ተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እጅ!!
አትጣላ ማለት ከሠው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እጅ!!
ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እጅ!!
ቆንጆ ነህ ማለትከሌሎች የተሻልክ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሀል ማለት እጅ!!
አዋቂ ሁን ማለት እደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እጅ!!

ሀሳባችሁን በ @hafizy_25 አድርሱን
.««««««««««««««»»»»»»»»»»»»»»
ቻናሉን ከወደዳችሁት ፤ አዲስ ሰለሆነ ሼር በማረግ እንድትተባበሩን

┏━━━•••━━ ••• ━ ••• ━┓
Join➹ @hafila25
┗━ ••• ━ ••• ━━•••━━━