Get Mystery Box with random crypto!

በዚምባብዌ በአንድ ወቅት በተፈፀመ የባንክ ዘረፋ ጭምብል አጥልቀው የመጡ የዘራፊዎቹ መሪ 'እንዳት | ሀዲስ ሚዲያ - Haddis Media

በዚምባብዌ በአንድ ወቅት በተፈፀመ የባንክ ዘረፋ ጭምብል አጥልቀው የመጡ የዘራፊዎቹ መሪ "እንዳትንቀሳቀሱ ገንዘቡ የሀገሪቱ ነው ነፍሳችሁ ደግሞ የግላችሁ ነች" በማለት አስጠነቀቀ..!!!

በባንኩ የሚገኝ ሁሉም ሰው መሬት ላይ ተደፋ። ይህ "Mind Changing concept" ይባላል። የሰዎችን አእምሮ የሚያስብቡበትን መንገድ ማስለወጥ ነው።

አንዲት ለግላጋ ሴት ጠረጴዛው ላይ ስትንጋለል አንደኛው ዘራፊ "እባክሽ እንደ ሰለጠነ ሰው ሁኚ። ለዘረፋ እንጂ ሴት ለመድፈር አልመጣንም!" ብሎ ጮኸባት።

ይህ ደግሞ "Being Professional" ተብሎ ይጠራል። የሰለጠንክበትን አጀንዳ ብቻ ማስፈፀም። ከዛ ውጭ ልታተኩርበት የሚገባ ነገር ካለ ዓላማህን መሳት ነው።

የዘራፊዎቹ ቡድን ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ቡኃላ በዕድሜ አነስ የሚለው ማስትሬት ዲግሪ ያለው ብልህ ብላቴና በዕድሜ ትልቁን ዘራፊ (6ኛ ክፍል ብቻ ያጠናቀቀውን ጎልማሳ) "ታላቅ ወንድሜ ያገኘነውን ገንዘብ እንቁጠረው።" አለው።

ትልቁ ሌባ "ሞኝ ነህ እንዴ? የዘረፍነው ገንዘብ እኮ እጅግ ብዙ ነው ይሄን ሁሉ ስንቆጥር ቀናትም አይበቃንም። ማታ በTV የዘሩፍነው ገንዘብ መጠን በዜና ይገለፅ የለ እንዴ?" አለው

ይህ "Experience" የምንለው ነው። ዛሬ ዛሬ ከወረቀት ማስረጃ ይልቅ ልምድ ቦታ የሚሰጥበት አጋጣሚዎች አሉ።

ዘራፊዎቹ ከባንኩ እንደወጡ የባንከ ማናጀር ለሱፐርቫይዘሩ "በል በቶሎ ለፖሊስ ደውልና ዘረፋውን በአስቸኳይ አሳውቅ።" አለው። ሱፐርቫይዘሩ ግን "ቆይ ከካዝናው ውስጥ 10 ሚሊዮን ብር ለራሳችን እናውጣና ሌቦቹ ከወሰዱት 70 ሚሊዮን ብር ላይ ጨምረን ሪፖርት ብናደርግ ይሻላል።" አለ።

ይህ ደግሞ "Swim with the tide" ይባላል። የማይመቹ አጋጣሚዎችን ለራስህ አድቫንቴጅ በመውሰድ ራስህን መጥቀም ነው።

ሱፐርቫይዘሩ በአጋጣሚው ያገኙትን ሀብት ሲመለከት "ኧረ እንደውም በየወሩ ባንክ ቢዘረፍ አሪፍ ነው።" አለ

ይህ ደግሞ "Killing Bordem" ይባላል። ባልተጠበቁ አጋጣሚዎች ከአቅምህ በላይ የሆኑ ነገሮች ሲከሰቱ ከሙያህና ከስራህ ይልቅ ለግል ደስታህ ቅድሚያ መስጠት ነው።

በቀጣዩ ቀን በሀገሪቱ ብሔራዊ የTV ጣብያ ዜና ላይ ከባንኩ 100 ሚሊዮን መዘረፉ ተነገረ። ዘራፊዎቹ በተደጋጋሚ ቢቆጥሩ ቢቆጥሩ 20 ሚሊዮን ብር ብቻ ሆነ የዘረፉት። በጣም ተናደዱ እጅግ ተበሳጩ። "እኛ ሕይወታችንን ነፍሳችንን አደጋ ላይ ጥለን የዘረፍነው 20 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። የባንክ ማናጀሩ ግን 80 ሚሊዮን ብር በኛ ስም በነፃነት በእጆቹ ወሰደ። ሌባ ከመሆንማ መማር የተማረ መሆን ይሻላል" አሉ።

ይህ ደግሞ "Knowledge is worth as much as Gold" እውቀት እንደ ወርቅ ውድ መሆኑን የምታውቅበት ነጥብ ነው።

በመጨረሻ የባንክ ማናጀሩ እና ሱፐርቫይዘሩ ደስተኞች እና ሳቂታዎች ነበሩ።

አሚር ሲራጅ ከAfrican Nomad ገፅ እንደተረጎመው

ከላይ ካሉት ከ6 ነጥቦች የትኛው ይበልጥ አስፈላጊ ነው?
#ከFacebook_መንደር