Get Mystery Box with random crypto!

ሚኒስትሯ የአፍሪካ ምርጧ የባህልና ቱሪዝም መሪ ተብለው ተሸለሙ፡፡ ባሕር ዳር፡ ኅዳር 23/2013 | Habesha news🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ሚኒስትሯ የአፍሪካ ምርጧ የባህልና ቱሪዝም መሪ ተብለው ተሸለሙ፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 23/2013 ዓ.ም (አብመድ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ኂሩት ካሳው የ2019 ምርጧ የአፍሪካ ቱሪዝም መሪ (WOMEN IN AFRICA TOURISM 2019 MOST ENERGETIC AND PASSIONATED AFRICAN TOURISM LEADER AWARD) አሸናፊ ሆነው መመረጣቸውን በጋና የሚገኘው ስትሪት ኦፍ ጎልድ ፋውንዴሽን የተሰኘው ድርጅት አስታውቋል፡፡
ሽልማቱ ከቀናት በኋላ ከአስር ቀን በኋላ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ እንደሚደረግ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሽልማት ኮሚቴው ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ በይፋዊ የማኀበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡
ሚኒስትሯ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ሽልማቱን አስመልክቶ ባሰፈሩት መልዕክት "በቱሪዝም፣ በሆቴልና መስተንግዶ በአጠቃላይ በዘርፉ ላይ ለተሰማራችሁ እና ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራኞተችና የሥራ ኃላፊዎች በሙሉ እውቅናው የእናንተው ነውና እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል፡፡
እጅ ለእጅ ተያይዘን ከሰራን ገና ሩቅ እንጓዛለን ነው ያሉት ሚኒስትሯ