Get Mystery Box with random crypto!

ህይወት ካለ ጉድለት አልተሰራችም። ስለዚህ ሁሉም ጉድለቱን ይዞ ይጉዋዛል የእፎይታን አፈር እስኪ | ግጥም እናጣጥም

ህይወት ካለ ጉድለት አልተሰራችም። ስለዚህ ሁሉም ጉድለቱን ይዞ ይጉዋዛል የእፎይታን አፈር እስኪቀምስ ያዝግማል።ፍንጭትህ በምን ትደፍነዋለህ ባለመሳቅ ብትል የተጨማደደ ግንባር ታተርፍለህ። የድድህ መጥቆር የጥርስህን ንጣት አይሸፍነውም ውበት ይሆንለታል እንጂ እነኚህ በክፍተትና በጥቁረት የተሞሉ ጌጦች ለፈገግታችን ድምቀት ናቸው። እናም እናዝግማለን እህህ ማለት አይበጅምና በጉድለት መኳል እንመርጣለን ። መከፍታችን ለእግዜር ና ለኛ የድልድይ መንገድ ነው። ምንድነው ችግርህ ? የምንልበት
ምን አጠፍው ብለህ የምታዋይበት ፣ሙላልልኝ ብለን የምንጨቀጭቅበት፣ እግዜርነቱን የምናምንበት ፣ዝቅታችንን የምናውቅበት ነው። ያ ባይሆንማ አዳም እፀበለስን አትብላ ባልተባለ ነበር ባይጎድልበት ዝቅታውን እንዴት ያውቅ ነበር? ሲፈጥረን አጉድሎብናል የሰጠን ግን ከሁሉ ይበልጣል ።ይሄን አምኖ ምስጋናውን የማይነሳ በእውነት እሱ ብፁህ ነው።

ናርዲ