Get Mystery Box with random crypto!

Big Game: አስታውስ(ሺ) ☞አንድ ቀን ይመ ጣል አንተ እራስህ የለበስከውን ልብስ ሰዎች አገላ | ግጥም እናጣጥም

Big Game:
አስታውስ(ሺ)

☞አንድ ቀን ይመ ጣል አንተ እራስህ የለበስከውን ልብስ ሰዎች አገላብጠው የሚያውለወቁልህ ቀን

☞የተከፈተ አፍ እና አይንህን ሰዎች የሚዘጉልህ ቀን

☞ተራምደህ ከሄድክበት ቦታ ሰዎች ተሸክመው የሚያስወጡህ ቀን

☞ ቤተሰብሽን እንኳን ታፍሪ የነበርሽው በሰው እጅ ገላሽ የሚታጠብበት ቀን

☞ጌጣጌጥሽ ሁሉ ከላይሽ ላይ የሚወልቅበት ቀን

✘✘✘✘✘✘✘✘✘✘
ፌስቡኬ

★Friend request ይላካል ዝም
★አሰላሙ አለይኩም ጭጭ
★ኧረ አናግሪኝ፣ ለምን ዘጋሺኝ? መልስ የለም !!!
ማን ይመልስ? እኔ ወደማይቀረው አለም ሄጃለሁ
ያ ራህማን !!
አጂብ ልብ የሚነካ ታሪክ እባከወን ያንብቡት

¶እናት ከልጇ ሞት በኋላ ያጋጠማት ልዩ ታሪክ¶
..................
¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶
ልጅ በአንድ የዲን ዩንቨርስቲ ተማሪ ስትሆን ልዩ
ድምጽም ነበራት፡፡ በዚህም ሁለ ግዜ ለሊት ቁርአን ትቀራ ነበር፡፡ ቂራአቷም እጅግ ያማረ ነበር፡፡ እናት ወደ ክፍሏ
ስትሄድ ከልጇ ከፍለ በር ላይ በመቆም ያማረ ቂራአቷን
ሁል ግዜ ታዳምጥ ነበር፡፡ በዚህ አየነት ቀናቶች ያልፉ
ነበር፡፡ ከእለታት አነድ ቀን ይህች ልጅ ታመመች፡
ቤተሰቦቿም ወደ ሀኪም ቤት ወሰዷት፡፡

በሆስፒታሉም ለቀናት ቆየች፡፡ ማገገም
አልቻለችም ህይወቷ በሆስፒታሉ ውስጥ አለፈ፡፡
ቤተሰብ በጣም አዘነ በተለይ እናት በልጇ ሞት እጅጉን
አዝናለች፡፡ የመጀመሪያው እናት ለጇን ያጣችበት ቀን
የአመት ያክል ረዘመባት፡፡ መሽቶ ወደ ክፍሏ
የምትሄድበት ሰአት ላይ እናት እንደለመደችው
ከልጇ ክፍል በር ላይ ቆመች ይሄኔ አንድ
አስደንጋጭ ነገር ሰማች ከክፍሉ ወስጥ ብዙ ሆኖ
ዝግ ባለ ድምጽ ለቅሶ ይሰማል፡፡ ወደ ውስጥ
ለመግባት ፈራች፡፡ እስኪነጋ ጠብቃ እናት
ሌሊት ከልጇ ቤት ወስጥ የሰማቸውን ለቤተሰብ
ነገረች፡፡ ወደ ከፍሉ ገቡ ምንም ነገር የለም፡፡
በሁለተኛው ቀን እናት እንደለመደችው
በተመሳሳይ ሰአት ወደ ልጇ ክፍል ስትሄድ ትላንት
የሰማችውን ድመጽ በድጋሚ ሰማች የሰማችውንም ለባለቤቷ ነገረችው፡፡ ባለቤቷም ሲነጋ የሰማሽው ምን
እንደሆነ እናጣራለን አሁን ተኚ ይላታል፡፡ ጠዋት ላይ
ወደ ከፍሉ ሲሄዱ ምንም ነገር የለም፡፡ እናት ግን
ድምጹን መስማቷን እርግጠኛ ነበረች፡፡
የሰማችውን ለአነድ ጓደኛዋ ትነግራታለች፡፡
ጓደኛዋም አንድ አዋቂ ሰው ብታማከር የተሻለ
እንደሆነ ትነግራታለች፡፡ እናትም አንድ ሸኽ ጋር
በመሄድ ስለ ሁኔታው ነገረቻቸው፡፡ ሼኹም
በሁኔታው በመገረም በሰአቱ በመገኘት
ሁኔታውን ማየት አለበኝ በማለት ተነስተው ሄዱ፡፡
ከዚህ ቀደም ልጅ በቤቱ ወስጥ ትሰራው የነበረውን
ሁሉ እናት ለሸኹ ነገረቻቸው፡፡ ልክ ሰአቱ
ሲደርስ ወደ ክፍሉ ተጠጉ፡፡ እናት ከዚህ ቀደም ለሁለት
ተከታታይ ቀናት ስትሰማው የነበረው የለቅሶ ድምጽ
ዛሬ ለሶስተኛ ግዜ ተሰማ፡፡ሼኹ ይህንን ሲሰሙ
አለቀሱ እናትም ያ ሸይኽ ምንድንው የሚያስለቅሳቹ
ስትል ጠየቀች፡፡ ሸይኹም አላሁ አክበር ይህ እኮ
የመላኢኮች የለቅሶ ድምጽ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሁል
ግዜ ሌሊት ልጅሽ እያለች ከሰማይ በመውረድ
እየተሰበሰቡ ቁርአን ያዳምጡ ነበር አሁን ያንን
ድምጽ በማጣታቸው ነው የሚያለቅሱት፡፡ ሱብሀነላህ

እርሶ ዘንድ እንዲቀር አይፍቀዱ Share ያርጉት —
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናገሩ"አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል።ከቀብር ሥነስርአቱም በህዋላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት ሙንከር እና ነኪር የተባሉ ምላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው በእምነቱ ጉዳይ ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ ። ሆኖም ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጋደኛዬም ነው ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላቹ እኔ ግን ወደ ጀነት መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው እልሄድም"። ከዝያም ወደ ሞተው አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ ምንም ጭንቀት አይኖርብህም"፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ አልጋ ያዘጋጅለታል።
2. ረሰል(ሶ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት በቂያማ ቀን በአላህ ሱ.ወ ፊት ስንቆም ከቁርአን የበለጠ ለኛ ሚከራከርልን አይኖርም ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ።
3. እባክዎን ይህን መልእክት የቻሉትን ያህል ያስተላልፉ። ረሱል (ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም አረፍተ ነገር ብትሆን እንኩዋን ብለዋል።
4. ይህ መልእክት በ አላህ ፍቃድ በቀጣይ 7 ቀናት ቢያንስ 5 ሚልዬን ሰዎች እንዲዳረስ ዱአ እያደረግን ነው።
እባክዎን ይህን መልእክት ለ ቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎትና ላሚያውቅዋቸው ሁሉ በማስተላለፍ ከተትረፈረፈው የአላህ ምንዳ ተጠቃሚ ይሁኑ።
*እርስዎ ቁርአንን ሲይዙ ሰይጣን ራሱን ያመዋል።
*ሲከፍቱት ይወድቃል።
*እያነበቡት ሲያይ ራሱን ይስታል።
*ይህንን መልእክት ሊያስተላልፉ ሲያስቡ ላማዳከምና ለማስነፍ ይሞክራል።
እኔ አሸነፍኩት ምክንያቱም ለእርስዎ መላክ ችያለሁ።


5. እባክዎን ሸይጣንን ያሸንፉና ይህንን መልዕክት ቢያንስ ለ5 ሰው በ 5 ደቄቃ ውስጥ ያስተላልፉ።