Get Mystery Box with random crypto!

Gospel

የቴሌግራም ቻናል አርማ gospelfornation — Gospel G
የቴሌግራም ቻናል አርማ gospelfornation — Gospel
የሰርጥ አድራሻ: @gospelfornation
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.38K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛውንና እውነተኛውን ወንጌል የምስራች ለአለም ሁሉ የሚያበራውን #ኢየሱስ ብቻ ሚሰበክበት
contact us @tsegamulat

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 15:30:20 "ሶፍት በቅናሽ"

(ቢቶ)

ያለወትሮዬ ትላንት በቀን ምድር በዛች መከረኛ የሳር ፍራሼ ላይ ጧ ያለ እንቅልፍ ተኝቼ ነበረ። በቀን መተኛትን እጥለዋለሁ ምክንያቱም ማታ ላይ እንዳፈጠጥኩ ነው ማነጋው በዚህጊዜ አጉል ፍቅር አጃጅሎት በናፍቆት የተነሳ እንቅልፍ እምቢ ያለውን ሰው ነው የምመስለው እንጂ ቀን እንደተኛሁ ማንም አይረዳም። ይህ ደሞ ፎንቃጃይተር Disorder ነው። ስለዚህ ህመም እንድቀባጥር እና አስፋው መሸሻን Prank እንዳደርገው EBS Tv ቢጋብዘኝ እላለሁ።

"የተኛ ሰው ህልም የማየት ግዴታ አለበት" የተባልኩ ይመስል ትላንትም በቀን ምድር ህልም አይቼ ነበር።

ሲመስለኝ የሆነ አዳራሽ ውስጥ ቁጭ ብያለሁ ህዝቡ ከአፍ እስከገደፉ ሞልቶ አንድ የሚያብረቀርቅ ሱፍ የለበሰ ሶዬ ማይኩን በግራ እጁ ቀኝ እጁን ወደ ካሜራው እየዘረጋ እንዲህ ማለት ጀመረ "በቅርቡ እንደ'ኔ አይነት የጋብቻ አስተማሪ እንደማይኖር ላረጋግጥላችሁ ፈልጋለሁ አንድ የበራልኝን እውነት ልንገራችሁ መጀመሪያ አምላክ ምድርን ፈጠረ ከዚያም አረፈ... ከዚያም ሰውን ፈጠረ፣ ከዚያም አረፈ... ከዚያም ሴቶችን ፈጠረ እና ከዚያ በኋላ ያረፈ የለም! ወንድም ጅላጅል ሆኖ በመቅረቱ እንደ በግ ባኣኣኣኣ እያለ እንዲኖር ተፈርዶበታል። ይሄን እውነት የነገራችሁ ማን አለ? አኹን ይሄን የምታዩ ሴቶች ታረግዛላችሁ የቤተሰብ መምሪያ እቅድን አልፋችሁ ትፀንሳላችሁ" አለና በወርቅ በተለበጠው ሶፋው ላይ ቁጭ አለና አንድ ኩስምን ያለን ልጅ አቁሞ Interview ያደርገዋል ልጁም "የእግዚአብሔር ሰው ይገርምሃል አንተ ላብህን ጠርገህ የጣልከውን ሶፍት አንስቼ ከበላሁ በኋላ ከኩላሊት ህመም ተፈወስኩ" ሲል አዳራሹ በዕልልታና በፉጨት ቀለጠ ጉባኤው ፉዞጃይተር Disorder እንደገጠመው ገባኝ። ከኋላዬ አንድ ሰው ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ
"ስማ ቢት የድሮ ጠንቋይ ግብሬን አላሟላህም ብሎ አፈር ድሜ ያበላል የዘንድሮው Digital ጠንቋይ ሶፍት ያበላል 11% እድገት ይሉታል ይሄ ነው" አለኝ ወደ ኋላ ዞሬ ሳየው አባይነህ ነው። ይሄ ሶዬ በህልሜም ጭምር እየመጣ ለምን እንደሚከታተለኝ እንጃ። "አባይነህ ተወኝ እስቲ" ብዬ ፊቴን ወደ ወደ መድረኩ ሳቀና ቶም ኤንድ ጄሪ ካርቱን ፊልም ተከፍቶ ህዝቤ ሲኮመክም ደረስኩበት ከጉባኤው ስንወጣ ህዝቤ "ዛሬ የሚገርም የእግዚአብሔር ቃል መገለጥ ነበር" እየተባባሉ ስለቶም ኤንድ ጄሪ ፊልም ያወራሉ ከባድ ድንዛዜ ውስጥ እንዳለን ሳብሰለስል እናቴ በማማሰየዋ አንድ ሶስቴ በኃይል መታ ስታደርገኝ ከእንቅልፌ ባነንኩ

"እንዲህ እስክትደነዝዝ ድረስ ምን አይነት እንቅልፍ ነው የወሰደህ? አንተን ለማንቃት በማደርገው ጥረት ማማሳዬ እንዳትሰበር ነው የምሰጋው ... በል የኔ ፉዞ ተነስ ሳሎን ሰው እየጠበቀህ ነው" አለችኝ

ተነስቼ ወደ ሳሎን ሳመራ አብሮ አደጌ ራሄል በቶም ኤንድ ጄሪ ፊልም ተመስጣ አገኘኋት

"እህህህ ሪች አንቺ ነሽ እንዴ .... ሱዳን ተመልሰሽ የሄድሽ መስሎኝ"

"ላለመመለስ እኮ ነው የመጣኹት ... አንድ ትልቅ ስራ ልሰራ አስቤኣለሁ አንተም እንድታግዘኝ እፈልጋለሁ"

"ኧረ ችግር የለውም ..... ምን ልትሰሪ አሰብሽ?"

"ቸርች ልከፍት አስቤኣለሁ"

"አሃ ለአቅመ ንቅል ጴንጤ ደረሽ ማለት ነው?"

"ቢት ደሞ የምን ንቅል ጴንጤ አመጣህ? የምር ግን አንተ በምን ልታግዘኝ ትችላለህ?"

"ሶፍት በቅናሽ አቀርብልሻለሁ የኔ ጴንጤጃይተር Disorder ታማሚ "
52 viewsጥፋ ከዚህ, 12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 00:17:25 በመንፈሳዊ በረከት መደሰት
(ቢቶ)

"እግዚአብሔር ይባረክ" ይህ ቃል ከብዙዎቻችን አንደበት አይጠፋም። ያሰብነው ነገር ሲሳካ ውጥናችን ሲሞላ ያስጨነቀን ነገር ቀለል ሲልልን "እግዚአብሔር ይባረክ" እንላለን። ያሰብናቸው ነገሮች ሳይሳኩ ሲቀሩ ውጥናችን ሳይሞላ ሲከሽፍ በእውኑ "እግዚአብሔር ይባረክ" የማለት አቅም አለን ይኾን?! ዛሬ ላይ አጉረምራሚዎች ሆነን የቀረንበት አንዱ ምክንያት እግዚአብሔርን በተሳካልንና ባልተሳካልን ጉዳዮች መመዘን ስለጀመርን ይመስለኛል።

የመደሰቻ በረከቶቻችን ምድራዊው/ ቁሳዊው ነገር ሆኗል። ሳቃችን ፤ ደስታችን ከቁስ ነገር መበጀት ከጀመረ ሰነባብቷል። ለዛ ነው አብዛኞቻችን እርካታ እያጣን የመጣነው። ምን ስናስብ ይኾን ደስታችን ወደር የማይገኝለት? ምንስ ሲደረግልን ይኾን የእውነት መደሰት የምንችለው?

ዛሬ ላይ ወደ አንድ ነገር መመለስ መቻል አለብን "በመንፈሳዊ በረከት ወደ መደሰት" የደስታችን ምክንያት መመርመር መፈተሽ አለበት .... መንፈሳዊ በረከቶቻችን ረስተን ለምድራዊው ብቻ እየተጋን ከእውነተኛ ደስታ እየራቅን ነው ያለነው። በቁስ ደስታ ተጠምደናል። "እግዚአብሔር ይባረክ" የምንልባቸው ሁኔታዎች በምድራዊው በረከት ላይ ያተኮሩ ሆነዋል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ በኤፌሶን 3 : 1 - 14 ባለው ክፍል እግዚአብሔር አምላክ በራሱ ተነሳሽነት ከእኛ አንዳች ሳይፈልግ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት እንደባረከን ይነግረናል። ስለዚህም ምክንያት "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ" ይለናል።

በክፍሉ ውስጥ እግዚአብሔር እጅግ በሚደንቁ በረከቶች እንደባረከን ብዙ ነገር እንዳደረገልን ይነግረናል።

¤ በክርስቶስ መረጠን
¤ በበጎ ፈቃዱ ወደደን
¤ ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ ወሰነን
¤ ቤዛነትን አገኘን
¤ የበደል ስርየትን አገኘን
¤ ፀጋውና ጥበቡን በአዕምሮ ሁሉ አበዛልን
¤ የፍቃዱን ሚስጢር አስታወቀን
¤ ርስትን ተቀበልን
¤ በመንፈስ ቅዱስ ታተምን


ብዙ እንደተደረገለት ሰው እግዚአብሔርን እንባርካለን። በመንፈሳዊ በረከት እንደሰታለን።

አዎን በመንፈሳዊ በረከት ወደ መደሰት መመለስ አለብን።

“በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።”
— ኤፌሶን 1፥3
33 viewsጥፋ ከዚህ, 21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 06:42:25
'ቃና' በሚባል ቴሌቪዥን "Orfaos da Terra" በሚል በፖርቹጋል ቋንቋ ከተሰራ ተከታታይ ፊልም 'ፍልሰት' በሚል የሽፋን ትርጉም ተሰጥቶት የተተረጎመው ነውረኛ ፊልም ነበር። ፊልሙ ላይ የሚታየው ሴት ከሴት ጋር ሲሳሳሙና ሲጋቡ ሲሆን ግብረ-ሰዶማዊነትን/Lesbianነትን የሚያበረታቱ ትዕይንቶች ስላሉት 'ለትውልድ ይገደኛል' የሚል ሰው ሁሉ ሊያወግዘው የተገባ ድርጊት ነው።

ብዙውን ጊዜ ከባህላችን ከእምነታችን ጋር የሚጋጩ ድርጊቶችን ሊያላምዱን ሲፈልጉ አንዱ የሚመጡበት መንገድ ፊልም ነው። የምናያቸውን ፊልሞች መምረጥ ብቻ ሳይኾን በጥንቃቄ መምረጥ ግድ ይለናል። አንዳንድ ፊልሞችን የታሪክ ፍሰታቸውን ስለወደድን ብቻ መመለልከት ሳይኾን በውስጡ ምን አጭቋል የሚለውንም ማስተዋል ያስፈልጋል። እንደኛ ሀገር ባሉ በባህልና በዕምነተ ምክንያት የተዘጉ ጠቃሚ በሮች አሉን እነርሱን በዘመናዊነት ሰበብ ገርበብ አድርጎ ከመክፈት ይልቅ ዘግቶ መቀመጡ አይጎዳንም።
እንደ "ፍልሰት" አይነት ፊልሞች አኹን ላለው ትውልድ በድጥ ላይ ውሃ እንደመጨመር ነው። ቀድሞም አዳልጦት ለመውደቅ ቅርብ ነው ድጥ ላይ የቆመ ነውና።

የሆኖ ሆኖ የቃና ቴሌቪዥን ተከታታይ ባልሆን ቃና ላይ የምትሰራው ቤዛዊት ዘሪሁን ፊልሙ ከስክሪን መውረዱን ትናንት በገጿ ላይ ፅፋ አንብቤኣለሁ።
83 viewsጥፋ ከዚህ, 03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:29:56
"★መንግሥት በአስቸኳይ ይህንን የርኩሰት ፊልም ያስቁም!"

★ ክርስቲያኖች ተጠንቀቁ!! " ፍልሰት" በሚል ርዕስ በቃና ቲቪ የሚተላለፈውን የሴት ሰዶማውያን /ሌዝብያን / ፊልም ፈጽሞ እንዳታዩ። ★ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ለገንዘብ የሚስገበገቡ፣የራሳቸውን ጥቅም እንጂ በትውልድ ሕይወት ላይ የሚያመጣውን መጥፎ ተጽኅኖ የማያገናዝቡ ስግብግብ ግለሰቦች ያገኙትን የውጪ ፊልም ሁሉ በገንዘባቸው እያስተረጎሙ ትውልድን እያረከሱ ሃገርን እያቆሸሹ ይገኛሉ።

ይህ "ፍልሰት" የሚል የማታለያ ትርጉም የተሰጠው ፊልም "Orfaos da Terra" ከሚል የፓርቹጋል ቋንቋ የተወረሰ ሲሆን የፊልሙ ዋና ዓላማ በስደትና በፍቅር ስም የሴት ሰዶማዊነትን /ሌዝቢያዊነትን/ በትውልድ ልብ ውስጥ ለማስገባትና ወጣቶችን በረከሰ ተግባር ለማጥመድ በምሥጢር ታቅዶ የተሰራ ፊልም ነው። ፊልሙ እጅግ በረቀቀ ዘዴ ወጣቶችን በመሳብ ልባቸውን እያንጠለጠለ የአዕምሮ እጥበት/Brain wash/ በማድረግ ሴት ከሴት ጋር በዝሙት መጨመላለቅን እንደ ዘመናዊነትና እንደ ሥልጣኔ ለማሳየት የተዘጋጀ አጋንንታዊ ፊልም ነው።

እንዳይታወቅባቸው ግን በጦርነት ምክንያት የሚፈጠር ስደት አስመስለው ነው ያቀረቡት። ፊልሙ በማር የተለወሰ መርዝ ነው።... ስለዚህም ይህ" ፍልሰት " በሚል ርዕስ በተከታታይ ለሕዝብ በይፋ በቃና ቲቪ የሚተላለፍ ነውረኛ ፊልም በአስቸኳይ መቆም አለበት።.
102 viewsጥፋ ከዚህ, 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 22:50:53
ብሔራዊ የወንጌል ተልዕኮ አስተማባሪዎች ጉባኤ #National_Mission_Summit

[
#NMS_2022] መረጃ_1

ሠላም ለሁላችን ይሁን!


በየዓመቱ፣ ብሔራዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ (
#NLS) ተከትሎ የሚዘጋጀው የወንጌል ተልዕኮ አስተማባሪዎች ጉባኤ(#NMS) #ከነሐሴ 23—28 /2014 ዓ.ም ድረስ በቢሾፍቱ መሰረተ ክርስቶስ ኮሌጅ ይካሄዳል።

የጉባኤው ተሣታፊዎች ከኢቫሱ አባል ሕብረቶች የተወጣጡ የወንጌል ተልዕኮ አስተማባሪዎች (
#Evan_Mobilizers) ናቸው። ከየግቢዎቹ አምስት (5) አስተማባሪዎች ተካፋይ ይሆኑበታል።

እግዚአብሔር ሥራችንን ያከናውንልን፤ ፀጋውንም ያብዛልን!!

-------------------
#EvaSUE
#Advancing_Gods_Kingdom
#NMS_2022
#ታማኝ_የመንግስቱ_ምስክሮች
#Faithful_Witnesses_of_the_Kingdom
#DigitalEvangelismMedia
@WolaitaSodoEvaSUE
184 views𝕜𝕙𝕖𝕧𝕣𝕒 𝔸𝕓𝕚𝕟𝕖𝕥, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 23:00:39
#ሎዶቅያዊት
ሙዚቃዊ ተውኔት
የፊታችን እሁድ
በአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን
140 viewsጥፋ ከዚህ, 20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 13:35:27
#ሰንፔር
12ኛው መንፈሳዊ የስነፅሁፍ ምሽት
ከነባርና ከአዳዲስ እንግዶች ጋር
ቅዳሜ ከ12 ሰዓት ጀምሮ
163 viewsጥፋ ከዚህ, 10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 12:05:45
National Leadership summit 2022
Faithful witness of the kingdom

#EvaSUE #NLS_22 #Faithful_witness_of_the_kingdom #See #Witness #Endure
183 views𝕜𝕙𝕖𝕧𝕣𝕒 𝔸𝕓𝕚𝕟𝕖𝕥, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 23:12:04 በሕይወት ውጣ ውረድ መካከል ቀና በል/ይ!

በሕይወት ውጣ ውረዶች መካከል የሚገጥመን ነገር ብዙ ነው፡፡ አንዳንዱን ነገር ልንቀበለው፣ እውነት ብለን ልናምነው ሁሉ እንቸገራለን፡፡ ምናልባትም የደረሰው የኾነው ነገር በሙሉ በእኛ ላይ ብቻ የኾነ ያህል ሆኖ ይሰማናል፡፡ የዓለሙን ሁሉ መከራ እኛ የተሸከምን፤ የመከራ ዶፍ በብቸኝነት የወረደብን፤ እግዜሩም ለይቶ እኛ ላይ ብቻ በጠላትነት የዘመተ መስሎ ሁሉ ይሰማናል፡፡

የጓደኛዬ አያት አጭር በሚባል ጊዜ ሴት ልጆቻቸው በተከታታይ ሞቱባቸው፡፡ ሐዘኑ ምን ያህል መሪር እንደሚሆንባቸው ለማሰብ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው፡፡ የጓደኛዬን እናት ጨምሮ አምስት ልጆች ሞቱባቸው፡፡ ሐዘኑ እንኳን ለእሳቸው ለእኛም እንኳ ከባድ ነበር፡፡

የመጨረሻዋን ልጃቸውን ቀብረን እንደተመለስን ለማጽናናት እስኪቸግር ድረስ ሐዘናቸው መሪር ሆነ፡፡ “ለጉድ ከምታስቀምጠኝ ለምን እኔንስ አትወስደኝም? ምን በድዬህ ነው” እያሉ እሪ ይላሉ፡፡ ለማጽናናት የመጡት ቄስ ብድግ ብለው መስበክ ጀመሩ፤

“የእኔ እናት በመጽሐፍ ቅዱስ ኢዮብ የሚባለው ሰው ልጆቹ ሁሉ በአንድ ጊዜ አለቁበት” ሲሉ የጓደኛዬ አያት “ይተዉኝ አባ አምስት ልጅ በተከታታይ!” ብለው መለሱ፤ አባ ቀበል አድርገው “ኢዮብ ዐሥር ልጅ!” አሉ፡፡

እኛጋ ብቻ የመጣ፣ በእኛ ብቻ የደረሰ የመሰለን መከራ የብዙዎችን በር ያንኳኳ ነው፡፡ በርግጥ በአገር የመጣ ነው እንዴ? ብለን እንደማናቀለው አውቃለሁ፡፡ ግን በቃ ዓለሙ የስብራት ዓለም ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ “ግን ለምን?” ብለን ብንጠይቅ ምላሽ የማናገኝለት ነገር በሕይወታችን ይሆናል፡፡

ይህ የመጣብን የተለየ በደል ፈጽመን፣ ከሰዎች ይልቅ ዐመፃችን ከፍቶም አይደለም፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ አምላክ ብቻ ያውቃል፡፡ እንዲነግረንም ደግሞ አይገደድም፤ አምላክ ነዋ፣ ሉዐላዊ አምላክ፡፡ ግን አንድ ነገር መረዳት በጣም ጥሩ ነው፤ እንዲህ ያለ ነገር የገጠመን እኛ ብቻ አይደለንም፡፡

ከሁሉ በላይ በሐዘን ለተሰበሩ ልቦች ጠጋኝ አምላክ አለ፡፡ የሚሠራውን ስለሚያውቅ በእርሱ ልብን ማሳረፍ እጅግ መልካም ነው፡፡ ባልገቡን እና ምላሽ ባላገኘንላቸው ነገር ሁሉ ጌታነቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡ በእኛ ግርታ ምክንያት ከአምላክነት መንበሩ ዝቅ አይልም፡፡

ዘማሪቷ “ባይገባኝም እንኳ ቅሉ…” እንዳለችው፤ በመልካምነቱ ልብን ማሳረፍ የተገባ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ከሚገጥሙን ነገሮች የተነሳ የምንሄዳቸው የማይገቡ መንገዶች፣ የምንሰማቸው አታላይ ድምፆች የመጨረሻውን ጸጸት ያበዙታል፡፡

ሸክም ስለሆነብን ነገር ጌታ አምላክን ታምኖ እርሱን ደጅ መጥናት የተገባ ነገር ነው፤ ውጤቱ ምንም ቢሆን፡፡ የመከራን ቀን በአምላክ ጥላ ተሸሽጎ ማለፍን የመሰለ ነገር የለም፡፡ ደግሞስ እንዲህ ያሉትን የምጥ ቀናት ማን መሸሸጊያ ሊሆን ይችላል፡፡ በመከራስ ቀን ከአምላክ በቀር ሊጠራ የሚችል ማነው? ቢጠራስ ሸክምን አራግፎ እፎይታን ሊሰጥ ማን ይችላል?

ስለዚህም ልብን በአምላክ አበርትቶ እርሱን ሙጥኝ ማለትና ወደ ላይ ቀና ማለት መልካም ነው፡፡ በፊታችን ደግ ቀናት አሉ፡፡ ኢየሱስ ይመጣል! አልያም እኛ ወደ እርሱ እንሄዳለን፡፡ በዚህ እንጽናና!!!

መጋቢ ስንታየሁ በቀለ
168 viewsጥፋ ከዚህ, 20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 19:40:35
National Leadership summit 2022
Faithful witness of the kingdom

#EvaSUE #NLS_22 #Faithful_witness_of_the_kingdom #See #Witness #Endure
145 views𝕜𝕙𝕖𝕧𝕣𝕒 𝔸𝕓𝕚𝕟𝕖𝕥, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ