Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚንየም በሰራተኛው የተገደሉ ሁለቱ ህፃናት! በአዲስ አበባ  ለሚ ኩራ ክፍለ ከተ | Gorgora Media

ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚንየም በሰራተኛው የተገደሉ ሁለቱ ህፃናት!

በአዲስ አበባ  ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 4   ቦሌ አራብሳ  ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመው የግድያ ወንጀል፤ የተፈፀመው  ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ነው፡፡በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራ  ወንጀል ፈፃሚ  አማካኝነት ክርስቲያን መላኩና  ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሶስት አመት ህፃናት በስለት ተወጋግተው ህይወታቸው አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደተናገሩት  ወንጀል ፈፃሚው በቁጥጥር ስር  ውላለች፡፡የህፃናቱ ህይወት በወንጀል ፈፃሚዋ  እንዴት  እንዳለፈና  ሌሎችንም መረጃዎች ፓሊስ ተጨማሪ መረጃ እያጣራ እንደሚገኝ እና  ህብረሰተቡም  እንዲረጋጋም ም/ ኮማንደር  ማርቆስ አደራ ብለዋል፡፡

ነብስ ይማር!