Get Mystery Box with random crypto!

#መልካም ወጣት መልካም ወጣት መሆን ከፈለጉ ግቢ ጉባኤ ይማሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ገብተው | 💯

#መልካም ወጣት

መልካም ወጣት መሆን ከፈለጉ ግቢ ጉባኤ ይማሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ገብተው ይማሩ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጆች ገብተው ይማሩ ወደ አብነት ትምህርት ቤቶች ገብተው ይማሩ በጠቅላላው ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ፣ መምህራንን በመጠየቅ፣ የሠርክ ጉባኤያትን በመከታተል፣ ቅዳሴ በማስቀደስ፣ በመጾም፣ በመጸለይ እና በመሳሰሉት መልካም ወጣት መሆን ይችላሉ።

ከከኃዲ ተምረው ታማኝ መሆን አይቻልም። የዲያብሎስን ትምህርት ሰምተው ቅዱስ የሆኑ የሉም። ሁሉም አጋንንት ሆኑ እንጂ። ስለዚህ በፍርኖ ዳቦ እና በሻይ እያታለሉ መልካም ወጣት እናድርግህ ያለውን መከተል አይገባም። መልካም ፍሬ የሚያፈራ መልካም ዛፍ ነው። ከክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ መጠበቅ ትልቅ ጅልነት ነው።

ከየግቢ ጉባኤው ለክረምት ወደየቤተሰቦቻችሁ ስትሄዱ ሕጻናትን ወጣቶችን እየሰበሰባችሁ የተማራችሁትን አስተምሩ።

#Facebook_telegram_tiktok
https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/
“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7