Get Mystery Box with random crypto!

ውሸት ውሸት ውሸት #እውነታው ኢቢሲ ከትናንት ጀምሮ 'ኦፕን ማጋዚን የሚባል የህንድ መፅሄት | GONCHA PLUS 🌍

ውሸት ውሸት ውሸት

#እውነታው ኢቢሲ ከትናንት ጀምሮ "ኦፕን ማጋዚን የሚባል የህንድ መፅሄት በአፍሪካ የዲሞክራሲያዊ መሪዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ፣ ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድን በ1ኛ ደረጃ ላይ አስቀመጠ" የሚል ዘገባ ይዞ ሲወዘውዘው ነበር።

የእሱን መረጃ ይዘው ደግሞ የሀገሬ የሶሻል ሚድያ ገፆች እና የዩትዩብ ቻናሎች ሲቀባበሉት ነበር። ከኢቢሲ በተጨማሪ አዲስ ሚድያ ኔትዎርክ፣ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ፣ ኦቢኤን አማርኛ... ወዘተ መረጃውን ሲያጋሩ ነበር።

የመፅሄቱ ዋና ኤዲተር ኤስ ፕራሳናራጃን በዚህ ዙርያ መረጃ ለኢትዮጵያ ቼክ ማምሻውን ያደረሰ ሲሆን "እኛ እንዲህ አይነት መረጃ አላወጣንም፣ የእኛም ዘገባ አይደለም። ይህንን ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን" የሚል ምላሽ ልኳል።

በዲጂታል መልኩ የታተሙ የመፅሄቱን የቅርብ ግዜ ህትመቶች የተመለከትኩ ሲሆን የተጠቀሰው አይነት መረጃ ይዘው እንዳልወጡ ማየት ይቻላል።

ከሁሉም የሚገርመው ግን የዚህ ሀሰተኛ መረጃ መነሻ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ ስም ተመሳስሎ በተከፈተ አንድ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት የተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ማየት ይቻላል። ይህ አካውንት ደግሞ ሀሰተኛ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ በተከታታይ መረጃዎችን አቅርቦ ነበር።

ይቺን እንኳን ሳያጣሩ ለሚልዮን ተከታታዮች መረጃ ማቅረብ አይከብድም... ወይም እንደ ክበበው ገዳ አባባል "አይሰቀጥጥም"


ተጨማሪ ከፈለጉ የደወል ምልክቷን ይጫኑ

❯❯❯ ❮❮❮