Get Mystery Box with random crypto!

“የኛ የኢትዮጵያዊያን ያለፈው ታሪክ እጅግ ያሳዝናል። ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ እስካሁን ድረ | GOFERE BUSINESS TIPS 💰

“የኛ የኢትዮጵያዊያን ያለፈው ታሪክ እጅግ ያሳዝናል። ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ፍጹም የሆነ ሰላም አግኝተን አናውቅምና። የተወደደች ሀገራችን፣ ዘወትር በጠላቶች ተከባ ስትኖር ነበረች፤ ትኖራለችም። ነገርግን በእግዚአብሔር ቸርነት የውጭ ጠላት ከዚህ በፊት አላዋረደንም። አንድነትም ስንሆን ምንም የሚደፍረን እንደሌለ ታሪክ ይመሰክራል። ዘወትርም በስምምነትና በፍቅር አድረን ብንሆን እስከ ዛሬ ድረስ ብዙውን ትልልቅ ነገር መፈጸም እንችል እንደነበር ጥርጥር የለውም። እግዚአብሔር ብዙ በረከት ሰጥቶናልና። ትምሕርትን በቶሎ መቀበል የሚችል ልቦናና የጦረኛን ባሕሪ፣ ማለፍያና ሀብታም አገርንም። ካለመስማማታችን የተነሳ ግን ሌሎች ሕዝቦች በአዕምሮና በጥበብ እየበረቱ ሲሄዱ እኛ ወደ ኋላ ቀረን። እንደ አረመኖች እስኪቆጥሩን ድረስ። የዱሮውም ያሁንም ኑሮዋችን እጅግ ያሳዝናል። በመላው ዓለም ላይ ሰላም ሲሰፋ አዕምሮም ስትበራ እኛ በጨለማ እንኖራለን። እርስ በርሳችን መጠራጠርንም አልተውነም። ሕዝቦቹም ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር ተቃቅፈው ስለ ልማታቸው ባንድነት ሁነው ሲደክሙ እኛ አንድ ዘርና ወንድማማች መሆናችንን ገና አልተገለጸልንም። እርስ በርሳችን መፋጀትም እስከ ዛሬ ድረስ ጀግንነት ይመስለናል። ስለዚህም እግዚአብሄር ለብርታት የሚሆነውን ስጥወታ ሁሉ ሰጥቶን ሳለ ባለቤቶቹ ሰነፍን። ሌሎቹም ነገሥታት እንደ ሰነፎች ይቆጥሩናል፣ይንቁናልም" ~ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ፣ ኢትዮጵያዊው ዶክተር፣ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ እና ምሁር!

(ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ሥራዎች፣ 2002 ዓ.ል፣ ገጽ 19-20)

@goferebusiness