Get Mystery Box with random crypto!

መጣሁልሽ ሀገሬ እነሆ የገና ስጦታዬ.... በቅድሚያ ከኢትዮጵያ ርቃችሁ በሁሉም የዓለማችን ክፍሎ | G Mesay Kebede Official

መጣሁልሽ ሀገሬ

እነሆ የገና ስጦታዬ....

በቅድሚያ ከኢትዮጵያ ርቃችሁ በሁሉም የዓለማችን ክፍሎች ትገኙ የነበራችሁ፦ ኢትዮጵያን የምትወዱ፣ ስለአገራቹ የምታስቡና የምትጨነቁ ወድ ወገኖቼ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል /ለገና/ በሰላም አደረሳችሁ። እንኳን በሰላም የአገራችሁን አፈር ለመርገጥ አበቃችሁ። አሁንም በአካል 'ሩቅ በመንፈስ ግን ኢትዮጵያን እያሰባችሁ ያላችሁ ወገኖቼ እናንተም ወደምትወዷት አገራችሁ የልባችሁ መሻት ተፈጽሞ በሰላም ያምጣችሁ። በአገራችን እንግዳ ከሩቅ ሲመጣ በአቅም ተዘጋጅቶ መቀበል ባህላችን ነውና እነሆ እኔም በሙያዬ እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለትና በዚሁም በዓሉን ለምታከብሩ የገና ስጦታ ይሆንልኝ ዘንድ መጣሁልሽ አገሬ የተሰኘ ሙዚቃ አበጀሁ። ነገ ማታ በምነው ሸዋ ኢንተርተይመን ወደናንተ ይደርሳል።

ጂ መሳይ ከበደ