Get Mystery Box with random crypto!

ይስጥልኝ እንደት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ሰላም ጤና እድገት ብልፅግና በያላችሁበ | Gift Real Estate 1

ይስጥልኝ እንደት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
ሰላም
ጤና
እድገት
ብልፅግና በያላችሁበት ተመኘሁ
በቅንነት ሼር ያድርጉ

አለርጂ ምንድን ነው?


አለርጂ ራሱን የቻለ መንስኤ ያለው የጤና ችግር ነው፡፡ በህዋስም ሆነ በንጥረ ነገር መልክ
ወደ ሰውነታችን በሚገቡ ነገሮች የሰውነታችን የመከላከያ ኃይል ከመደበኛው
(ከሚጠበቀው) በላይ ምላሽ ሲሰጥ የሚፈጠር ክስተት ነው፡፡


በየትኛውም መንገድ ይሁን ወደ ሰውነታችን የሚገቡ ባዕድ ነገሮችን ለመከላከል ወይም
ለማጥፋት የሚያስችሉ ንጥረ ነገሮች (anti body) ማመንጨት የሰውነታችን በሽታን
የመከላከል ስርዓት ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡


ይህ ስርዓት ብዙውን ጊዜ የሚጠበቅበትን
ተግባር የሚያከናውን ቢሆንም፣ አንዳንድ ጊዜ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች በሚፈጥሩት
ተፅኖ ሳቢ፣ ጎጂዎችንና ጠቃሚ ሴሎችን በጅምላ በማጥፋት ከመጠን በላይ የሆነ እርምጃ
ይወስዳል፡፡

የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት አንዳንድ ጊዜ የራሳችንን አካል ክፍሎች
ለምሳሌ ኩላሊትን፣ ልብን፣ መገጣሚያንና የአካል ንቅለ ተከላ ሲደረግ እንደ ባዕድ
በመቁጠር ያጠቃል፡፡ በዚህ ጊዜ ከሚፈጠሩ ችግሮች አንዱና ዋነኛው አለርጂ ነው፡፡


ለአለርጂ አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ማንኛውም ሰው በየትኛውም ጊዜና ሰዓት አለርጂ በሚፈጠሩ የጤና ችግሮች የመጋለጥ
ዕድል አለው፡፡

ለዚህ ችግር የሚያጋልጡ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡
 የተለያዩ የምግብ አይነቶች
አለርጂን በማምጣት የሚታወቁ የምግብ አይነቶች አሉ፡፡

እነዚህም ወተትና የወተት
ተዋፅኦዎች፣ ዓሳና ዓሳ ነክ ምግቦች፣ እንቁላል፣ ተለያዩ የኦቾሎኒ አይነቶች፣ አኩሪ አተርና
ምግብን ለማጣፈጥ ወይም ለረጅም ጊዜ ለማቆየት ተብለው የሚጨምሩ ንጥረ ነገሮች
እንዲሁም በመድሃኒት ውስጥ የሚጨመሩ ኬሚካሎችና በፋብሪካ የታሸጉ ምግቦችለአለርጂ የማጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡


ሁሉም ሰው ለአንድ አይነት መድሃኒት አላርጂ ነው ማለት ባይቻልም፣ ለተለያዩ የህመም
አይነቶች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለአለርጂ መከሰት ምክንያት ይሆናሉ፡፡

በኬሚካል ማምረቻዎች የሚሰሩ
ለአረም ማጥፊያ ኬሚካሎች ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች እንዲሁም አቧራ፣ የዕፅዋት ብናኝ፣
ቀዝቃዛ የአየር ፀባይና ከቤት ውስጥ እንስሳት ጋር የዕለት ተዕለት ግንኙነት የሚያደርጉ
ሰዎች ለአለርጂ ተጋላጭ የመሆን ዕድል አላቸው፡፡

ነገር ግን ሁሉም ሰው ለአንድ አይነት ጉዳይ በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ አለርጂ ይሆናል ማለት
አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለአንዱ አለርጂ የሆነ ጉዳይ ለሌላው ላይሆን የሚችልበት ሁኔታ
ሰፊ በመሆኑ ነው፡፡


አለርጂ በአብዛኛው የሚከሰተው በየትኛው የሰውነት ክፍል ነው ?
ቆዳ ጋር ባለ ንኪኪ ቆዳ ላይ ይከሰታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
#በዓይን፣
#በአፍንጫ፣
#በአፍ፣
#በመተንፈሻ አካላትና በአንጀት አካባቢ ይከሰታል፡፡

አለርጂ ሲከሰት የሚታዩ ምልክቶች
አለርጂ ሲከት የተለያዩ ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን፣ አለርጂው እንደሚከሰትበት ቦታ
የሚታዩ ምልክቶችም የተለያዩ ናቸው፡:

#ለምሳሌ የአፍንጫ አላርጅ ፦

#አፍንጫ እና የመተንፈሻ አካላት አካባቢ ሲከሰት፡- ቀጭን ውሃ መሳይ ንፍጥ፣
ማስነጠስ፣ የአፍንጫ መደፈን፣ ማሳከክ፣ ማሳል፣ የመተንፈሻ አካላት እብጠትና ውሃ
መቋጠር፣ ፈሳሽ መብዛት፣ የአየር መታፈን፣ ፣ ሲር ሲር የሚል ድምፅ ሊከሰት ይችላል፡፡


አለርጂ ሲከሰት የሚያሳያቸው ምልክቶች ቀለል ያሉ ቢመስሉም ራስን ከመሳት እስከ ሞት
ድረስ ሊያደርስ የሚችል በሽታ እንደሆነ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡

በአንድ ይሁን በሌላ
ምክንያት የሚፈጠር አላርጅ፣ ተገቢውን ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚድን ቢሆንም
ተመልሶ የመምጣት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡


#የአፍንጫ አላርጅ መፍትሔ
፩ኛ ጥሬ ጨው በውሃ አሙቆ ወደአፍንጫ በማስገባት ማፅዳትና መለቅለቅ ጥሩ መፍትሔ ነው።

፪ኛ የሽነት ስር ቅርፍት ቀጥቅጦ አልሞ ፈጭቶ ዱቄቱን በትንሽ በትንሹ በአፍንጫ መሳብ ያስነጥሳል ግን ከበሽታው ይፈውሳል ተከታታይ ይጠቀሙት ከአላርጅ ሙሉ በሙሉ ያድናል።

በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ #ሸር #share ማድረግዎን እንዳይረሱ

➤ የቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶችና ቅደመ አያቶቻችን የጥበብ ሥራ የሀገር በቀል እፅዋትና የጠልሰም ሥራ ጥቅማቸው በግልጽ ይቀርባል ይብራራል

0913463201