Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም ወግና ልቦለድ📕📔📚

የቴሌግራም ቻናል አርማ getmwegnaleboled — ግጥም ወግና ልቦለድ📕📔📚
የቴሌግራም ቻናል አርማ getmwegnaleboled — ግጥም ወግና ልቦለድ📕📔📚
የሰርጥ አድራሻ: @getmwegnaleboled
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.45K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ channel ግጥሞች ወጎች መጻጽፍቶችና ልቦለዶች ይቀርባሉ ቤተሰብ በመሆን ይደሰቱ ይዝናኑ @SamiHope7 @yeabrehet

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-15 20:33:40 . #እውነት እና #ውሸት


እውነት እና ውሸት አንድ ቀን ተገናኙ። እናም ውሸት እውነትን እንዲህ አለው "የዛሬው ቀን ግሩም ድንቅ ነው።" እውነትም ሽቅብ አንጋጦ ሰማዩን ተመለከተና "ኣህ" ብሎ ትንፋሽ ካስወጣ ቦሀላ "በርግጥም የሚያምር ቀን ነው" ሲል አደነቀ።
አብረው ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ እየተዝናኑ ሲጓዙም ወደ አንድ የጉድጓድ ምንጭ ውሀ ዳርቻ ደረሱ። ውሸትም ለእውነት የውሀውን ጥሩነት ከነገረው ቦሀላ በጋራ እንዲተጣጠብ ጋበዘው እውነት ግን ጥርጣሬ ቢያድርበትም ገብቶ በመሞከር የውሀውን ጥሩነት ለማረጋገጥ ፈለገ።
እናም እውነት እና ውሸት ልብሳቸውን አወላልቀው ከውሀ ውስጥ ገብተው እየተጣጠብ እያለ ድንገት ውሸት ከውሀው በመውጣት የእውነትን ልብስ ለብሶ ከአካባቢው በጣም ራቀ።በሁኔታው የተናደደው እውነት ከውሀው በመውጣት ውሸትን ፍለጎ ልብሱን ለማስመለስ ባገኘው አቅጣጫ መሮጥ ጀመረ። አለም የተራቆተውን እውነት በንቀት እና በተቆጣ መንፈስ ያፈጥበት ጀመረ።
ምስኪኑም እውነትም በፍርሀት ወደ ጉድጓድ ተመልሶ እራሱን በመደበቅ ተሰወረ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ውሸት የእውነት የቀናና ያማረ አለባበስ ተላብሳ የማህበረሰብ ፍላጎትና መውደድ ልታሟላ በአለም ዳርቻ ትመላለሳለች።

ምክንያቱም በማናቸውም ሁናቴና ምክንያት አለም እራቆቱን የተጋለጠውን እውነት ማየትም ሆነ ማግኘትን አይፈልግም
@getmwegnaleboled @getmwegnaleboled
SHARE
SHARE
2.1K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 14:32:21 ሰላም ውዶቼ እንዴት ናቹ...
በዚህ ቻነል እንዲነሳና እንዲፃፍ የምትፈልጉት ማንኛውም ሀሳብ ካለ
Bezih @Samihope7
ልታስቀምጡልን ትችላላቹ።

መልካም ቀን
1.8K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 14:28:23 ፊልም አይደለም::እውነተኛ ህይወት ነው::መተወን አቁሙ::መኖር ጀምሩ::
1.8K views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 13:32:05 ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉት ነገር ካለ ያንን ነገር ለሰዎች አድርጉ፡፡
+
በዙርያችሁ ላሉ ሰዎች ቀናና በጎ ካልሆናችሁ ቀና እና በጎ ህይወት ለመኖር ትቸገራላችሁ፡፡
+
ስኬት፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ፍቅር እና በጎ ነገር ከፈለጋችሁ እነዚህን ነገሮች ለሰዎች ስጡ፡፡እነዚህን ነገሮች ወደ እናንተ ተመልሰው ሲመጡ ታላችሁ፡፡
+
ለምን ለሰዎች መጥፎ ትሆናላችሁ?
አእምሯችሁ የሚያጫወትባችሁ የውሸት ጨዋታ ስላለ ነው፡፡
+
የእናንተ አእምሮ ለሰው መጥፎ በመሆን ጥሩ ህይወት እንደሚኖር አድርጎ ይነግራችኋል፡፡
ራሳ ወዳድ ሆናችሁ ሰው በመበደል የሆነ ጥቅም ማገኘት እንደምትችሉ አድርጎ ይሰብካችኋል፡፡
ነገር ግን የውሸት ስብከት ነው፡፡
+
በጨለማ ብርሃን አይገኝም፡፡መጥፎ የሆነ ሰውም ጥሩ ሕይወት አይኖርም፡፡
አዎ ምን አልባት ለጊዜው ጥሩ ህይወት የሚኖር መስሎ ሊታይ ይችላል፡፡መጨረሻው ግን ምንጊዜም መጥፎ ነው፡፡

ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉት ነገር ካለ ያንን ነገር ለሰዎች በደስታ አድርጉ፡፡ለሰዎች ያደረጋችት ነገር ተመልሶ ወደ እናንተ ይመጣል፡፡
+
አስታውሱ ይህ የምንጊዜም የሕይወት ወርቃማው ህግ ነው፡፡

share
Join : @getmwegnaleboled
1.8K views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 11:50:17 ልብህ በአምላክ ደስ ይበለው::ፊትህም እንደ ጸሐይ ያብራ::
-
በዚህ ምድር ሰዎች አትመካ::ዛሬ የሚያስደስት ነገ የሚያስለቅስ ነው::ሰው ይቀየራል::ወበት ይረግፋል::ወጣትነት ያልፋል::ሀብትም ይጠፋል::
-
የማይጠፋው ብቸኛ ነገር ዘለዓለማዊዉ አምላክ ነው::የእርሱን ደስታ ከቀመስከው እውነተኛ ብርሀን ይሞላሃል::ነጻነት : ውበት : ሀይል : ፍቅር : ስላምና የህይወት ውድ ነገር ይከብሀል::
-
አትሽውድ::ሰዎች ምርጥ ነገር ሲያደርጉልህ አትበድ::ከአናትህ በላይ አታኑራቸው::በልብህ ዙፋን አታንግሳቸው::ይህን ካደርክ ስዎች ይቆጣጠሩሀል::ባላሰብክበት መንገድ ተለውጠው ይጉዱሀል::
-
ይልቅ ስዎች ምርጥ ሲሆኑ ምርጥ ያደርጋቸውን አምላክ አምስግን::በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን አምላክ ተመልከት::በልብህ ዙፋንም አንግሰው::ሰዎች ድንገት ቢቀየሩም አይጎዱህም::ምክንያቱም የአንተ ጨዋታ መቸም ከማይቀየረው እግዚአብሔር ጋር ነው::እንድ ጥሩ ውዳጅ ቢሄድ አምላክህ ሌላ አንድ ሚሊየን አንድ የተሻሉ ወዳጆችን ያምጣልሀል::ቢዝነሱም ቢከስር: ዝናህም ቢጎድል: ጤናህም ቢጠፋ: ስራም ብታጣ: ትዳርህም ቢጨልምና ሁሉንም ነገር ብታጣም ፈጣሪ ከአንተ ጋር ከሆነ ምንም ነገር አላጣህም::እንዲሁም የተሻለ ሰርፕራይዝ ጠብቅ::
-
ከዚህ አለም ነገሮችህ በላይ የዚህ አለም ነገሮች ፈጣሪን አስቀድም::ሌላው ሁሉ ይጨመርልሃል::
-
መልካም ቀን
@getmwegnaleboled
@getmwegnaleboled
1.8K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:04:39
1.8K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 08:41:03 Life isn't about finding yourself. Life is about creating yourself.

George Bernard Shaw

@getmwegnaleboled
@getmwegnaleboled
1.7K views05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:28:29
AMEN
1.8K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:49:42
ምንም ቢረዝምም ምንም ምደረስ ባይመስልህ ትደርሳለህ.... ምንም እንኳ መሰናክል ያለ ባይመስል ብትወድቅም, ብደክምም, ተነስተህ ቀጥል የጀመርከው መንገድ ከሰው ጋር ሳይሆን ከራስህ ጋር ነው ቀረቡም እራቁም መንገዱ ያንተ እና ያንተ ነው.... ቅድሚያ መስጠት ላለብህ ነገር ቅድሚያ ስጥ መንገድህን ሂድ እየሄድክ....
@getmwegnaleboled
@getmwegnaleboled
1.8K viewsedited  19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:07:07 ጦፒያ

ምነው እግዜር ጦፒያ ላይ ክንድህ በረታ?
በካቻምናው ታሪክ ቅፅሟ እንደተመታ
ለአምና ዛሬ ላይ ዳንኪራ እይተመታ
ምነው እግዜ ጨከንክባት፤
እናቴን ይብቃሽ በላት፤
ከእቅፍ አሳርፋት።

ምድራ ለም፤ ቆላ ወይን አደጋ
ሠዉ እሩሩ ሳይጠግብ የሚያበላ
ጥላውን ከመስጠት አይልም ወደኋላ
ይቺ ናት የኛ ድጓ አለም፤ ጦፒያ የምንላት
እጆችዋን ለ'ግዜር የዘረጋች አማላጅ የምንልካት
ይቺ ናት ጦፒያ አለም፤ ነጮች በስልጣኔ ሦሥትኛ የሚሏት።

ጦፒያ የጊዮን መፍለቂያ
የ'ግዜር ቅባ ቅዱስ መኖሪያ
ለቅዱስ አምላክ፤ ለም መዳረሻ
የሊቃውንት፤ የነገሥታት ክብር መንገሻ
የክቡር ታቦታት፤ የአብ፤ የወልድ፤ የመንፈስ ቅድስ፤ መሰለሻ
ይቺ ናት የኛ ቅዱስ አለም፤ ከአንድ ፈጣሪ "እግዚአብሔር" ውጪ የምናመልከው የለም።
@getmwegnaleboled
@getmwegnaleboled
2.2K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ