Get Mystery Box with random crypto!

የምስኪኑ መፅናኛ (ቡሩክ ካሳሁን) ደሀ ቢሉኝ እንኳን ቤሳ ቤስቲ የሌለው ለሁለት ብር ዳቦ ሶስት | ግጥም ወግና ልቦለድ📕📔📚

የምስኪኑ መፅናኛ

(ቡሩክ ካሳሁን)

ደሀ ቢሉኝ እንኳን ቤሳ ቤስቲ የሌለው
ለሁለት ብር ዳቦ ሶስት ብር የጎደለው
በህይወት ዘመኔ ያሻኝ ባልበላ
ያሻቸውን በልተው እሱን ለማቃጠል ሲቸገሩ መላ
ቆሜ ተመልክቼ
ላመስግነው እንጂ ሁሉን ባይሰጠኝም
ካሻኮር ነው እንጂ ኮሌስትሮል የለብኝም!

@getmwegnaleboled