Get Mystery Box with random crypto!

ረከስኩ ሁዳዴን እለቱ ሁዳዴ እማስብ ለሆዴ ይህ አይበቃኝ ብሎ ረከስኩ በቆሎ አቃለው ወደጄ ጥያቄ | 📚 የኛ_ግጥም 📚

ረከስኩ ሁዳዴን

እለቱ ሁዳዴ
እማስብ ለሆዴ
ይህ አይበቃኝ ብሎ
ረከስኩ በቆሎ
አቃለው ወደጄ ጥያቄ ይፈጥራል
ሰው እንዴት ብሎ በቆሎ ሁዳዴን ይሽራል
ወዲ ነው ነገሩ.....
ልጁ ልቤን ወስዶ ዝም እንዳልኩኝ ነበር
ጠጋ ጠጋ ተጠጋ ወደኔ
ለስላሳ እጆቹን አሳረፈ ከጭኔ
አጠመቀኝ ላበት
መነሳት አቃተኝ ከተቀመጥኩበት
ተነስቶ ሄደና ገርበብ ብላ ነበር በሯን ጠረቀማት
ሸሚዙን አውልቆ ካለሁበት መምጣት
ቆሎ እያዘገነኝ
ተረት ጀመረልኝ
.
.
.
ከያ በኋላማ



እኔ ማስታውሰው
ተረቱ ማለቂያው አንድ ቃል ነበረው
እሱም እንዲ ......ነበር
ከተራራው መሀል አንድ ልጀ ነበረ
ድክምክም አለና እዛው ላይ አደረ
የኋላ
.
.
የኋላ

ተረቱን ስረዳው
ተራራን መስሎ ከጡቶቼ መሀል እሱ ነው ያደረው

.
በተረት አስክሮ ፆሜን አስረስቶ
ይኸው መና አስቀረኝ ከፈጣሪ አጣልቶ

ami #ለፈገግታ ነዉ


#ሼር አደራ