Get Mystery Box with random crypto!

እንደምን ከረማችሁልኝማ?? ተጠፋፋንኣ?? ከጀርባዬ የተቀመጡ ባልና ሚስት ወይም ፍቅረኛሞች እ | 📚 የኛ_ግጥም 📚

እንደምን ከረማችሁልኝማ?? ተጠፋፋንኣ??

ከጀርባዬ የተቀመጡ ባልና ሚስት ወይም ፍቅረኛሞች

እሷ :- ይሄኛው አይሻልም?

እሱ:- ይሄ ብዙ ኪሎ ሜትር ተነድቷል:: ሌላ ምረጪ...

(አንድ የሆነ ያገለገለ መኪና የሚገዛበት ሳይት ውስጥ መኪና ሊገዛላት ይመስለኛል እየመረጡ ነው::)

እሷ:- እሺ የቱ ይሁን?

እሱ:- ደስ ያለሽን...

"ደስ ያለሽን" ይላታል እንጂኮ ያሳይችውን ሁሉ በሆነ ሰበብ ይጥልባታል:: .. ተወደደ... ቀለሙ ደስ አይልም.... መልሶ ደግሞ "ደስ ያለሽን" ... ይላታል ....

የሆነ ካፌ ምናምን ተቀምጣችሁ የሚቀጥለው ወንበር ላይ ያሉ ሰዎች የሚያወሩትን ልቅም አድርጋችሁ ከመስማታችሁ የተነሳ ከእነርሱ ጋር የመጣችሁ ምናምን ወይም የምታውቋቸው ነገር መስሏችሁ አያውቅም??

ዞር ብዬ "አንቺ አይገባሽም እንዴ በቃ ብሩ የሚቀንሰውን ምረጪ !" ልላት ሁላ ምንም አልቀረኝም::

መዓት ካሳየችው በኃላ የሆነኛውን "አዎ ይሄ አሪፍ ነው!! ይሄን እንገዛለን" ሲላት ወሬውን በጣም ከመሳተፌ የተነሳ

"እስኪ እስኪ??" ልል ነበር

ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝማ

መጥቻለሁ ለማለት ነው::

semir ami