Get Mystery Box with random crypto!

ትህነግ የጓዳ ውሉን ይፋ አደረገው! ትህነግ በጀኔራል ታደሰ ወረደ በኩል የጓዳ ውሉን በማያሻማ | Getachew shiferaw

ትህነግ የጓዳ ውሉን ይፋ አደረገው!

ትህነግ በጀኔራል ታደሰ ወረደ በኩል የጓዳ ውሉን በማያሻማ መልኩ ይፋ አድርጓል። ብልፅግና ጠለምትና ራያን በቅርቡ፣ ከዛም ወልቃይትን አሳልፎ ለመስጠት የተዋዋለበትን በይፋ ተናግሯል። ከ50 ሺህ በላይ ንፁሃን በትህነግ ታጣቂ ከራያ የተፈናቀሉት በጓዳ ውሉ መሰረት እንደሆነ ይታወቃል። አማራ እየተወረረ ያለው በጓዳ ውሉ መሰረት ነው።

የብልፅግና አመራሮች ስለ ትህነግ ትጥቁን መፍታት ወዘተ ሲያወሩ "ውሸታቸውን ነው" የምንለው በምክንያት ነው። ጦርነት የሚፈልግ ኃይል ወዘተ እያለ የሚያወግዙ የሚመስሉት ውሸት ነው። የአማራን ግዛቶች አሳልፈው ለመስጠት የተዋዋሉት በወረራ መሆኑ ይፋ ወጥቷል። ታደሰ ወረደ ብልፅግና አማራን በኃይል እንዲይዙ የሰጣቸውን ድጋፍና ፈቃድ በሚዲያ ወጥቶ ሲገልፅ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው። እነ ተመስገን ጥሩነህ "ያፈነገጠ ወዘተ" እያሉ ሀሰት ሲናገሩ፣ ጀኔራል ታደሰ በይፋ መጥቶ ከብልፅግና ጋር የተዋዋሉት የጓዳ ውል መሆኑን እየገለፀ ነው።

አማራን በትህነግ እያስወረረ የሚገኘው ብልፅግና ነው። ትህነግ ባለፈው በጌታቸው ረዳና ታደሰ ወረደ፣ ዛሬም በታደሰ ወረደ በኩል ወረራው ከብልፅግና ጋር በተስማሙት መሰረት የተደረገ እንደሆነና እንደሚቀጥል ሲገልፅ ብልፅግና ትንፍሽ አላለም። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሮች ናቸው ወረራው በስምምነት የተፈፀመ መሆኑን የሚናገሩት። ያፈነገጠ ወዘተ የሚባለው ነጭ ውሸት ነው። ማዘናጊያ ነው። የጓዳ ውሉን ማድበስበሻ ነው!