Get Mystery Box with random crypto!

የእስር ሰለባው ጋዜጠኛ ለምክክር ኮምሽኑ ያነሳቸው ወሳኝ ጥያቄዎች ሞኝን እብባ ሁለት ጊዜ ነደ | Getachew shiferaw

የእስር ሰለባው ጋዜጠኛ ለምክክር ኮምሽኑ ያነሳቸው ወሳኝ ጥያቄዎች

ሞኝን እብባ ሁለት ጊዜ ነደፈው፤ አማራስ ሁለት ጊዜ ይነደፍ ይሆን! በፍጹም!

(ዳዊት በጋሻው ከቃሊቲ እስር ቤት)

ሚያዚያ 13 እና 14 2016 ዓ.ም በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙ ኃይሎች ወደ ምክክር እንዲመጡና ለዚህም ከለላ እንደሚደረግ የሚገልፀ ዜና ተመለከትኩ፡፡ ይህንን ያሉት የሀገራዊ ምክክር ምክትል ዋና ኮሞሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ ናቸው፡፡ ወቅቱ አሰቃቂ የጭንቅ ጊዜ ሆነ እንጅ ንግግራቸው ሙሉ የኮሜዲ ይዘት ያለው ነው፡፡ ግለሰቧ ይህንን በተናገሩበት ወቅት የአማራ ልጆች በማንነታቸው ብቻ እየተመረጡ የሀገሪቱን እስርቤቶች ሞልተዋል፡፡ የአማራ ልጆች በአዲስ አበባ እና በሌላው የሀገሪቱክፍሎች በሀሠት እየተከሰሱ ፤ እንደ አዋሽ አርባ ባሉ የማሰቃያ ቦታዎች መከራቸውን እያ ባለበት ወቅት ከለላ እናደርጋን እንመካከር እያሉ ማውራት ህሊና ቢስነት ነው፡፡ በታሪክ ፊትም ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ የአማራ ልጆች የዕድሜ ፣የሙያ የፆታ፣ የእምነት፣ የት/ት ደረጃ ልዩነት ሳይኖር በጅምላ እየታሰሩ ነው፡፡ በሀገሪቱ ያሉ እስር ቤቶች በመሙላታቸው የብልፀሸግና ፓርቲ አመራሮች በኦሮምያና በአፋ አማራ የሚታጎርባቸው ወህኒ ቤቶች በአጭር ጊዜ እንዲሰሩ ማዘዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው እንግዲህ ስለምክክርና ስለከለላ ዋስትና እየተወራ ያለው፡፡ እስኪ ለኮሚሽኑ አባላት በተለይም ለዋናና ለምክትላቸው እነዚህን ጥያቄዎች ላንሳ፡-

1. በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋትወንጀል እያያችሁና በዚህም ላይ ምንም ሳትሉ ስለምክክር ስታወሩ ህሊናችሁ ምን ይላችኋል?

2. በአስቸኳይ አዋጅ ሰበብ ንፁሀንን በድሮን እየተጨፈጨፉ እናንተ እንመካከር ስትሉ ህዝቡ ምን የሚል ይመስላችኋል?

3. ፖሊስና ደህንነት የነቁ አማሮችንበመላው ሀገሪቱ እያሳደዱ ባሉበት ሁኔታ እናንተን አምኖ ጠረንጴዛ የሚስብ ያለ ይመስላችኋል?

4. እናንተ ከለላ እንስጣችሁ የምትሏቸው የአማራ ህዝብ የትግል መሪዎች በፍትህ ሞኒስቴር ተከሰው በጋዜጣ ተጠርተዋል፡፡በአንድ በኩል የወንጀል ክስ ከፍቶ በሌላ በኩል ከለላ ልስጥ ማለት አይጋጭም ወይ?

በመሰረቱ እኔ ጥያቄን ባሳደገኝ ህዝብ ጨዋነት ልክ በትህትና ላቅርብ ብዬ እንጅ ስለ 11ዱም ኮሚሽነሮችመረጃም ማስረጃም አለኝ፡፡

ለምሳሌ ያህል ስለ ፕ/ር መስፍን አርአያ ፣ መሐመድ ድፈር፣ ዮናስ አዳዬ፣ ዘገዬ አስፋው በደንብ መናገር ይቻላል፡፡
የምክክር ኮሚሽኑ አባል አቶ ዘገዬ አስፋው የኦነግ ስራ አስፈጻሚ መሆን በሽግግሩ ወቅት የአማራ ህዝብን አስጨፍጭፏል፡፡ ይህ ተራ አሉባልታ ሳይሆን በሰነድ የተቀመጠ ሀቅ ነው፡፡በመሆኑም በወቅቱ የግብርና ሚኒስትር ነበር፡፡ በጥቅሉ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመና ያስፈፀመ በመሆኑ ህዝብ በወንጀል ይፈልገዋል ፡፡ በተጨማሪም የአማራ ልጆች በአዲስ አበባ ዙርያ ቤታቸው ፈርሶ፣ ተፈናቅለው በስቃይ ላይ ሆነው ፤ለንብረታቸውና ለህይወታቸው ምንም ይቅርታና ዋስትና ሳይደረግ በማን አለብኝነት ሸገር ከተማ ብሎ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከተማ ሲያስመርቅ አቶ ዘገየ አስፋው የድግሱ ተካፋይ ነበር፡፡ ስለሌሎችም ሙሉ ማስረጃ አለ፡፡ የኮሚሽኑ ገለልተኛነት እዚህ ድረስ ነው፡፡ ለማንኛውም ለአፍና ለይምሰል እንኳን እነዚህን ጥያቄዎች ለማንሳት ሞክሩ፡-

1) መንግስት የምትሉት አካል ተኪስ እንዲያቆምና የዘር ፍጅቱን እንዲተው

2) አዋጅ ተብዬው መግደያና ማሳደጃ እንዲቀርና ለዚህም ተጠያቂ እንዲሆን

3) በመላው ሀገሪቱ ያለውን የንፁሀን ግድያ እንዲያቆም በተደጋጋሚ ብትናገሩ ለይምሰል እንኳን የተሸለ ይሆናል፡፡

በመሰረቱ ዐቢይ አህመድ ምክክር ኮሚሽንና ሽግግር ፍትህ እያለ ያለው፦

1. በነዚህ ተቋማት ሰበብ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት

2. ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ይሄው ላወያይ ነው ለማለትና ስልጣንን ለማራዘም ነው፡፡ ያም ሆነ ይሕ ግን ከዚህ በኋላ የአማራን ህዝብ ለዓመታት አይደለም ለቀናት መሸወድ ወይም በሽመልስ አብዲሳ አገላለፅ (ኮንቪንስና ኮንፊውዝ) ማድረግ በፍፁም አይቻልም፡፡ ከዚህ በኋላ ጥቅም ላይ የሚውል አይደለም፡፡

ለማንኛውም ለይምሰል የሚደረግ የትኛውም ድርጊት ከህዝብ አያመልጥም፡፡
መንግስቱ ሀይለማርያም በስተርጅና ለስደትና ለውርደት፤ መለስ ዜናዊን በህዝብ ፊት ለውርደት ብሎም ለሞት የዳረጓቸው ሁኔታዎች እልህና ይምሰል ናቸው ( የፈጣሪን ሀያልነት ረስቼ አይደለም)፡፡ ያም ሆነ ይህ አማራን እያሳደዱ መመካከር፤ ማስነገር ጊዜው አልፎበታል፡፡ የአማራ ህዝብ ከዚህ በፊት በወለጋ፣ በመተከል፣ በሀረርጌ፣ በአርሲ፣ …. ሲጨፈጨፍ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ጭፍጨፋው ቤቱ በር ላይ ነው፤ይ የማንክደው ሀቅ ነው፡፡ ለህልውና መታገል ደግሞ ፈጣሪም ዓለም አቀፍ ማህበረሰብም የሚደግፈው ነው፡፡
ሕዝብ ማሸነው አይቻልም
የአማራ ህዝብ ትግል ለእውነት፣ ለፍህ፣ ለለውጥ ነው፡፡