Get Mystery Box with random crypto!

የትህነግ ታጣቂ ራያ ላይ እየፈፀመው ያለው ሰቆቃ በገለልተኛ ሚዲያ እይታ! ከስር ያለው መረጃ ዓል | Getachew shiferaw

የትህነግ ታጣቂ ራያ ላይ እየፈፀመው ያለው ሰቆቃ በገለልተኛ ሚዲያ እይታ!

ከስር ያለው መረጃ ዓል አይን አማርኛ የትህነግ ታጣቂ እየፈፀመው ያለውን ተነግሮ የማያልቅ ሰቆቃ በወረራ ስር ያሉትን ነዋሪዎች አናግሮ ከዘገበው የተወሰደ ነው።

#የትግራይ ታጣቂዎች ከመጡበት ዕለት አንስቶ ንብረታችን እየተነጠቀ ነው፡፡ ለገበያ የደረሰ ሀብ ሀብ አትክልቴን በልተውብኛል ሲጠግቡ ደግሞ በያዙት ጦር መሳሪያ በሰደፉ እና በአፈሙዙ እየመቱብኝ ነው”

#በቀበሌያችን ከገቡበት ከሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በገበሬው ቤት እየገቡ እየደበደቡን ነው። አርሶ አደር ጦር መሳሪያ አምጡ እያሉ እኛ ገበሬዎች ነን ፖለቲካ አናውቅም ብንልም ሊተውን አልቻሉም"

#ከዚህ በፊት አብረውን ይኖሩ የነበሩ ነገር ግን በስጋት ምክንያት ወደ ትግራይ ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ካሳለፍነው ሰኔ እና ግንቦት ወር ጀምሮ እየገቡ መኖር ጀምረዋል፣ ሳይገቡ የቀሩት ከዚህ በፊት በነበረው አስተዳድር ጊዜ ህዝብን ሲያንገላቱ እና ሲያማርሩ የነበሩት ብቻ ቀርተው ነበር"

#ታጣቂዎች ሲቪል እየለበሱ ወደ ከተማዋ ነዋሪ መስለው እየገቡ ነው፣ የመንግስት ተቋማትን እየዘረፉ እና ፋይሎችን እያወደሙ የከተማዋ ነዋሪዎችንም ፍርሃት ውስጥ እንዲገባ የተለያዩ ጫናዎችን እያደረጉ ነው። በከተማዋ ያለው የፌደራል የጸጥታ ሀይል ቢኖርም ነዋሪውን ከመሰደድ አልታደገውም"

#የፌደራል መንግስት ለራያ እና አላማጣ ጉዳይ ዘለቄታዊ መፍትሔ ይሰጠዋል ብለን እየጠበቅን ለትግራይ ታጣቂዎች አሳልፎ ሰጥቶናል።

#በሰሌን ውሃ ቀበሌ የሚኖረው ሌላኛው አስተያየት ሰጪ በበኩሉ የትግራይ ታጣቂዎች የራያ እና አላማጣ የገጠር ቀበሌዎችን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መቆጣጠራቸውን፣ በየቀኑ አዳዲስ እና ተጨማሪ ታጣቂዎች ወደ አካባቢዎቹ እየገቡ መሆኑን አክሏል፡፡
ታጣቂዎቹ በየሰው ቤት እየገቡ የልጆችን ምግብ ሳይቀር እየበሉ እንደሆነ፣ ለባሏ የምሳ እቃ ለማድረስ ወደ እርሻ ቦታ እየሄደች ያለችን እናት ለአማራ ታጣቂ ልትሰጪ ነው በሚል እያንገላቱ ነው ያሉት እኝህ አስተያየት ሰጪ ታጣቂዎቹ ይህን ሲያደርጉም የፌደራል የጸጥታ ሀይሎች እያዩ የማስቆም ፍላጎት እንደሌላቸውም ነግሮናል፡፡

#ከዚህ በፊት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ወደ መቀሌ እና ሽሬ የሄዱ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ ቤታቸው ተመልሰው አብረን በጋራ እያረስን እና እየኖርን ቢሆንም ታጣቂዎቹ በድንገት መጥተው ለእንግልት እንደዳረጓቸውም አክሏል፡፡

#ታጣቂዎቹ በየጊዜው እየሰበሰቡም ከእንግዲህ እምናስተዳድራችሁ እኛ ነን፣ የያዛችሁትም የአማራ ክልል የነዋሪነት መታወቂያ ከእንግዲህ አይጠቅማችሁም፣ ልጆቻችሁን አምጡ እና ለአማራ ታጣቂዎች ድጋፍ እያደረጋችሁ ነው የሚሉ ወከባዎችን እያደረሱባቸው እንደሆነም እኝህ አስተያየት ሰጪ ተናግረዋል፡፡

#ወቅቱ የሚያዚያ ወር አዝመራ የምናዘምርበት ቢሆንም እርሻችንን ትተን በየቀኑ ምን እንሆን ይሆን የሚል ስቃይ ውስጥ ነን"