Get Mystery Box with random crypto!

ተፈናቃይ ብለው የሚያስገቡት ይህንን ዘራፊ ኃይል ነው! ትህነግ በወረራው ወቅት አማራና አፋርን | Getachew shiferaw

ተፈናቃይ ብለው የሚያስገቡት ይህንን ዘራፊ ኃይል ነው!

ትህነግ በወረራው ወቅት አማራና አፋርን መዝረፍን ጀብዱ አድርጎ ለወጣቱ አስተማረው። አትክልትና ፍራፍሬ ጭምር "ከአማራ ክልል የመጣ" እየተባለ በሞንታርቦ እየተጮኸ ሲሸጥ ነበር። የአማራ ክልል ታርጋን አንስተው ታርጋ አልባ መኪና የሚነዱት "አምጥቶ ነው" እየተባሉ በጀብድ ተነገረላቸው። እርጉዝ ሳይቀር ለዘረፋ መጥታ አማራ ወልዳ ተይዛለች። ወጣቱ "እኔም ይህን አምጥቻለሁ" እያለ በጀግንነት እንዲያወራ ተደረገ። ከጦርነቱ በኋላ ግን ዘረፋውን ትግራይ ውስጥ ቀጠሉት። አማራ ላይ ጀግና የተባሉበት ነዋ! የቀራቸው ነገር የለም። ፍርድ ቤት ስላልቻለ እንደ ድሮው በአደባባይ በዚህ መልክ መቅጣት ጀምረዋል።

ታዲያ ወደ ራያ የላኩት ይህን ዘራፊ ኃይል ነው። አዲስ ልብስና ጫማ ሳይቀር እያስወለቀ ሲወስድ የሚታወቅ ዘራፊ ራያን እያራቆተ ነው። በወረራው ወቅት ሲዘርፍ ጀግና ያሉትና ከወረራ በኋላ ትግራይን ያስመረረውን ነው ወደ ራያ የላኩት። ወደ ጠለምትና ወልቃይትም ለማስገባት የወሰኑት ይህ ሰው በላ የሆነን ኃይል ነው።