Get Mystery Box with random crypto!

በኤርሚያስ በኩል የሚስተጋባው የግድያና የወ*ረ*ራ ዝግጅት! ደብረፅዮን የሰላም ስምምነቱን ህወሓት | Getachew shiferaw

በኤርሚያስ በኩል የሚስተጋባው የግድያና የወ*ረ*ራ ዝግጅት!

ደብረፅዮን የሰላም ስምምነቱን ህወሓት አያውቀውም ብሏል። ደብረፅዮን ይህን መግለጫ የሰጠው ከብልፅግና ጋር ያደረጉት የድብቅ ስምምነት ባሰቡት መልኩ ስላልሄደላቸው ነው። ስለሆነም ራያ ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳ አድርገዋል። በወልቃይት ወ*ረ*ራ ለመፈፀም ዝግጅት ማድረጋቸውን የራሳቸው አክቲቪስቶች ጭምር እየፃፉት ነው። ለዚህ ሲባል ቀድሞ ፕሮፖጋንዳ መስራት አስፈልጓደዋል። አንደኛው አማራውን መነጣጠል ነው።

ትህነግ/ህወሓት በራያ ትንኮሳ ከመፈፀሙ በፊት የፀጥታና ሌሎች አመራሮችን ገድሏል። በአካባቢው ሰው በሀሰት ስማቸው እንዲነሳ በማድረግ ጭምር ከአምስት በላይ አመራሮች ተገድለዋል። በቀጣይ ወልቃይት ከዛም አልፎ ጎንደር ላይ አስበዋል። ለዚህም በእነ ኤርሚያስ በኩል በሀሰት ስም ማጥፋት ፕሮፖጋንዳ ቀጥለውበታል።

በሁለት አመቱ ጦርነት ወቅት ትህነግ/ህወሓት በእነ ኤርሚያስ በኩል "ስኳድ" የሚል ሰነድ ሰርተው በትነው ነበር። ወቅቱ የትህነግ/ህወሓት ጎንደርን እይዛለሁ ብሎ የሚለፋቨየሚለፋበት ወቅት ነበር። በጦርነቱም በፕሮፖጋንዳውም አልተሳካላቸውም።

ትህነግ/ህወሓት ከ60 ቀን ግምገማው በኋላ ለኤርሚያስ ትዕዛዝ ሰጥቶ በየሚዲያው አንዳንዴ በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ ሳይቀር ራሱ የሰራውን ሰነድ ህዝብን ለመከፋፈያነት ሲጠቀምበት ይውላል። ዋናው ትህነግ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት አንዳንድ ግለሰቦችን ለማስገደል፣ ወረራም ለመፈፀም የሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት ሲሆን ኤርሚያስ TMH፣ ማሪያማዊት የምትባል የህወሓት አባልና ሌሎች ሚዲያዎች ላይ እየተመላለሰ እየሰራበት ነው። የዚህ ነውረኛ ውሸታው የግድያና ጦርነት ቅስቀሳ በህግ ጭምር የሚያዝ ስለሆነ ወደፊት እመለስበታለሁ።

ለማነፃፀሪያ እንዲሆን ግን አብይን እየተከላከለ፣ በረከትን እየተከላከለ፣ በይፋ በፓርቲ የመጣውን ኩሽኩን እየተከላከለ፣ የጎንደር ህዝብ እያለ የሚነዛውን ጥላቻ ተመልከቱት! ኤርሚያስ የሀሰት ሰነዱን ለማስረፅ ሶስት አመት ሙሉ ሰርቶበታል። ምክንያቱ ደግም ትህነግ/ህወሓት አማራን ነጣጥሎ፣ መጀመሪያ ጎንደርን መትቸ ወደሌላው አቀናለሁ የሚለውን የወ*ረ*ራ አላማ ለማስፈፀም ነው።

"ህወሓት ሲባል የትግራይን ህዝብ ማለታቸው ነው" እያለ የሚያስተባብለው ኤርሚያስ፣ "ኦህዴድ ሲሉ ኦሮሞን ነው" የሚለው የበረከት ስምኦን ልጅ፣ ጎንደር እያለ ግን አደረጃጀት ብቻ ሳይሆን ህዝብን እንደ ህዝብ እየዘመተበት ያለው በትህነግ ቀጣይ የወ*ረ*ራ እቅድ መሰረት ነው።

(በዚሁ አጋጣሚ መሰል የሀሰትና ጥላቻ ቅስቀሳ ቪዲዮዎች ያሏችሁ ወገኖች ከስር እንድታያይዙ ትጠየቃላችሁ)