Get Mystery Box with random crypto!

ሲ ፒ ጄ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ዘርፉ አስቸኳይ ህክምና እንዲያገኙ ጠይቋል። | Getachew shiferaw

ሲ ፒ ጄ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ዘርፉ አስቸኳይ ህክምና እንዲያገኙ ጠይቋል። ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ዘርፉ የታሰሩበት አዋሽ እስር ቤት በንፋስና ጎርፍ በደረሰበት ጉዳት ለአደጋ መጋለጣቸውን ገልፆ በአስቸኳይ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ጠይቋል።

እነ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸው ተደርገው "የኢትዮጵያው ጓንታናሞ" እየተባለ በሚጠራው ክፉ እስር ቤት ከታጎሩ ወራት አልፈዋል። ከጋዜጠኞቹ በተጨማሪ ፖለቲከኞችና ሌሎች ንፁሃን በአማራነታቸው በዚህ የግፍ እስር ቤት እየተሰቃዩ ነው።