Get Mystery Box with random crypto!

የአማራና ትግራይ ጉዳይ ሰሞኑን ትልቅ አጀንዳ ሆኗል። እውነታው ግን እንደሚባለው አይመስለኝም። ከል | Getachew shiferaw

የአማራና ትግራይ ጉዳይ ሰሞኑን ትልቅ አጀንዳ ሆኗል። እውነታው ግን እንደሚባለው አይመስለኝም። ከልባቸው አይደለም።

ከልባቸው ቢሆን ኖሮ የኃይማኖት አባቶችን "አማራ ናቸው" ብለው ፈርጀው በማውገዝ አይቀጥሉም ነበር። "መንበረ ሰላማ" የተሰኘው ቡድንኮ ዋናው ሲኖዶስ የሚጠራበት "የአማራ መንበር ነው' በሚል በሀሰት ፈርጀው የተነሱበት ነው። ያለፈው ይብቃ ይሉና ሲኖዶሱ ጦርነት አውጆብናል እያሉ እያወገዙ ተገንጣይ ሲኖዶስ አዋቅረው ጳጳሳትን "ሚሊሻ፣ ፋኖ" እያሉ ፈርጀው አሁንም ይጠሯቸዋል። ይህ ከአብይ አህመድ ጋር የሚጋሩት ነው። እሱም ኦሮሚያ ላይ ተነጣይ ሲኖዶስ አዋቅሯል። ሁለቱ ተነጣዮች ተነጋግረው አጀንዳ ያስይዛሉ።

የትግራይና የአማራ ሕዝብ መቀራረብ አለበት የሚሉት በአንድ ሚዲያ/ፕሮግራም ያለፈው አለፈ ብለው፣ በሌላ ፕሮግራም ደግሞ ጳጳሳትን አማራ አድርገው ከተነጣይ መንበራቸው ጋር ሲቀድሱ ይሰማሉ። ይህ ስለ ህዝብ ሰላም የሚያወሩት ሀሰት መሆኑን ማሳያ ነው።

ጳጳሳቱን በአማራነት ፈርጀው፣ አብይ አፈርሳታለሁ የሚላትን ቤተ ክርስቲያን በሀሰት የአማራ መጠቀሚያ አስመስለው እናፈርሳለን እያሉ ስለ ሰላም ሊያወሩ አይችሉም! የጦርነቱ ሀሰት ተይዞ ሌላ ሰላምና እርቅ ከተፈለገ ሰላምና እርቅ አይመጣም።

የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያነሳሁት የአማራ ዋና አጀንዳ ስለሆነ አይደለም። አማራን በሀሰት የሚፈርጁበት ስለሆነ ነው። አማራ ናቸው ካሏቸው ውጭ የሚዘምቱባቸው አባቶች የሉም። ቤተ ክርስቲያንን የሚዘምቱባት ባለፈ ጦርነት ነው። ያለፈው ይቅር ብለው ከአብይ ጋር ሰንብተዋል። ያለፈው ይቅር እንታረቅ እያሉ በሀሰት በአማራነት የፈረጇትን ቤተ ክርስቲያን ግን ጥርስ እንደነከሱባት ነው።

በነገራችን ላይ እነሱ ገራፊውን ጌታቸው አሰፋን ይዘው እንደሚመጡ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ በሰነድ "አማራ ጠላት ነው" ብሎ በማንፌስቶ ያሰፈረውን ትህነግን ከፊት አድርገው እንደሚቀርቡ፣ ለአመታት ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት የፈፀመ ኃይልን ዋና ተደራዳሪ አድርገው እንደሚመጡ የምናጣው ይመስላቸዋል።

አልቆረጡም! የአጭር ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ማለፊያ ነች። ይህ ደግሞ አያዋጣም።

ሰላም ከተባለ አንዱ ቅድመ ሁኔታ "የአማራ ናት" እየተባለ፣ መንበረ ተክለኃይማኖት የእነሱ፣ የሸዋ ነው እያሉ የሚያወግዟትን ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጭምር ጥለው መሆን አለበት። ከዛ መንበረ ሰላማ የሚባል ቡድን በጎን አስቀምጠህ ጌታቸው አሰፋኖ ደግሞ ተቀበሉኝ ማለት አያስኬድም! ጳጳሳትን እያወገዙ በመንበረ ሰላማ በኩል ተገንጣይነትን እየሰበኩ በፖለቲካ ደግሞ ሰላም ያስፈልጋል እያሉ ነው። የኃይማኖቱ አማራ ላይ የሀሰት ፕሮፖጋንዳና ጥላቻ እያዛመቱ፣ በፖለቲካ ከአማራ ጋር ሰላም መፍጠር አይቻልም። የኃይማኖት አባቱን ያውም በራሱ ብሔር ፈርጀህ፣ በሚያከብረው ፋኖ ስም ያንቋሸሽክ እየመሰለህ፣ ቤተ ክርስቲያንን ከኦሮሞ ብልፅግና በተመሳሳይ አጀንዳ ላፍርስ እያልክ ሰላም ፈልገህ ነው ብሎ የሚያምንህ አማራ አይኖርም!

ውሸታቸውን ነው። አልቆረጡም። ጊዜያዊ ስልት ነው። ይህ ደግሞ አያዋጣም!