Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ሕዝብ ብልፅግናን አስቤዛ የጠየቀ አስመሰለውኮ። የአማራ ሕዝብ በሕይወት የመኖር፣ እንደ ሰው | Getachew shiferaw

የአማራ ሕዝብ ብልፅግናን አስቤዛ የጠየቀ አስመሰለውኮ። የአማራ ሕዝብ በሕይወት የመኖር፣ እንደ ሰው ተከብሮ የመኖር፣ የአገር ባለቤትነት፣ የማንነት፣ የፍትሕና እኩልነት ግዙፍ ጥያቄዎች ነው ያሉት። በዓለም ማንም ሊጥሳቸው አይገባም የተባሉ መብቶችን ሁሉ ነው የተነጠቀው።

ልጆቹ በግፍ ታስረዋል! በድሮን እየተደበደበ ነው! ወደ ዋና ከተማው ማለፍ አይችልም!

ብልፅግና ለማሾፍ ወደ አማራ ክልል ስለሄደ "መንግስት አቅሙ በፈቀደ አያጓድልም" ይልሃል። አቅሙን ለመግደል ነው እየተጠቀመበት ያለው። ደግሞ ህዝብ አስቤዛ አሟላልኝ ብሎ አልጠየቀም። የአማራ ህዝብ ብልፅግናን አልፈለገም። የጠየቀውም መብቱን ነው። የጠየቀው ችሮታን አይደለም። አቅሙ ፈቀደም አልፈቀደም ጉዳዩ አይደለም።

ይህ ግን ለብልፅግና ንቀትና ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ማሳያ ነው!