Get Mystery Box with random crypto!

የእኛ ሚና ምንድን ነው? ትህነግ ዳግመኛ ጥ*ቃ*ት ፈፅሞብናል። ይህ ኃይል ባለፈው ከቆቦ እስከ | Getachew shiferaw

የእኛ ሚና ምንድን ነው?

ትህነግ ዳግመኛ ጥ*ቃ*ት ፈፅሞብናል። ይህ ኃይል ባለፈው ከቆቦ እስከ ሸዋሮቢት፣ ከላሊበላ እስከ ጋይንት፣ ከዋግኸምራ እስከ ጭና የፈፀመብንን እናውቃለን። ያን በደል አሁን እንዲደግመው መፍቀድ የለብንም። ለሕዝባችን የሚጨንቀን ከሆነ እኛ እንችለዋለን የምንለውን ሚና መጫዎት ግድ ይለናል። የራያ ወገናችን ሲጠቃ ጦርነቱን ከዘነጋን ከትናንቱ አልተማርንም ማለት ነው። የራያ ወገናችን ላይ የተከፈተውን አሁኑኑ መቀልበስ አለብን። ሁላችንም በምንችለው ማበርከት አለብን! እስከ ነገ መዘግየት የለብንም። ዛሬ

1) ስንቅ ማሰባሰብ የሚችል በስንቅ ማገዝ አለበት
2) ኃይል አሰባስቦ መድረስ የሚችል ዛሬውኑ ያን ጥቃት ለመቀልበስ መነሳት ግዴታው ነው።
3) ሕዝብ በተሳሳተ መረጃ እንዳይረበሽ ማረጋጋት የጦርነት አንዱ አካል ነው። ትህነግ ከመሳርያው ያላነሰ ፕሮፖጋንዳን የስነ ልቦና ጦርነት አካል አድርጎ ይጠቀማል።
4) ሰርጎ ገብ ሊያደርሰው የሚችለውን ጉዳት ከአሁኑ ለመከላከል መዘጋጀት ያስፈልጋል።
5) መረጃዎችን መቀያየር፣ ለሕዝብ በሚጠቅም መልኩ ማሰራጨት ያስፈልጋል።

በትክክለኛውም ሆነ በተሳሳተ ወሬ ተደስቶም ተበሳጭቶም ለውጥ አይመጣም። ለውጥ የሚመጣው የእኔ ሚና ምንድን ነው ስንል ነው። በሰበር ዜና ተደስተን ደስታው ቀጣይ ሊሆን አይችልም። ትህነግ ሰበር ዜና በሚለው ተናድዶ ለውጥ አይመጣም። የገባንበት ጦርነት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል። ብዙ ፅናት፣ ብዙ ትግስት ያስፈልገዋል። ስሜታችን ትንሿ ነገር ነች። የእህቶቻችን ተስፋ ያጨልማል፣ የወጣቶችን ህይወት ይቀጥፋል። ስሜታችንን እምቅ አድርገን ሚናችን ምንድን ነው እንበል።

ሚናችን ከለየን የተነገረው ሰበር ዜና ሁሉ ጮቤ አያስረግጠንም። ሚናችን ከለየን የተነገረው የትህነግ እውነትም ይሁን ውሸት ተስፋ አያስቆርጠንም። ሚናችን ከለየን በቀጣይስ የምንሰራው ምንድን ነው የሚለው ያስጨንቀናል። ሁላችንም ሚናችን ምንድን ነው እንበል። በሰበር ዜና መደሰት፣ መጨነቅም ሚና አይሆንም። ከአሁኑ ጀምረን ሚናችን ምንድን ነው እንበል!



ማሳሰቢያ:_

በዚህ ወቅት በረባ ባልረባው መጨቃጨቅ ለጠላት የሚጠቅም እንጅ ለወገን የምንሰራለት ሚና አይደለም።

ትህነግ በየትኛውም ማንነት አይነጥለንም። የሁላችንም አንገት ለእሱ አንድ ነው። በስስት የሚያቅፈው አይደለም። በጥላቻ የሚቆርጠው ነው።