Get Mystery Box with random crypto!

ለአማራ ሕዝብ አስባለሁ ለሚል ሁሉ! ከወራት በፊት አንድ ሴራ ከሽፏል። ሴራው የሶማሊ ክልል ወጣቶ | Getachew shiferaw

ለአማራ ሕዝብ አስባለሁ ለሚል ሁሉ!

ከወራት በፊት አንድ ሴራ ከሽፏል። ሴራው የሶማሊ ክልል ወጣቶችን በሱዳን ሊቢያ ወደ አውሮፓ እንወስዳችኋለን በሚል አማራ ክልል ሲደርሱ አሰቃቂ ግድያ በመፈፀም አማራና ሶማሊ ሕዝብ መካከል ግጭት ማስነሳት ነበር። ለዚህ አላማ የተመለመሉ ሰዎች ሶማሊ ክልል ላይ ተይዘው የማን አላማ እንደሆነ ግልፅ አድርገዋል።

የሶማሊ ክልል አስተዳደር በርካታ ችግር ይኖርበታል። ቢያወግዙት፣ ቢወቅሱት የሚከላከሉለት የራሱ ሰዎች ይኖሩታል። ይሁንና ከባለፈው ሴራዎች የቀጠሉ የክፉዎች አጀንዳ አሁንም ብቅ እያሉ ነው። የትህነግ አጀንዳ ሰጭ የሆነው ርዕዮት ሚዲያ ሰሞኑን እነ ሙስጦፌን አልሸባብ አድርጎ አቅርቧቸዋል። ራሳቸውን የመከላከል የራሳቸው ስራ ይሆናል። ጉዳዩ ግን በእነ ሙስጦፌ የሚቆም አይደለም። ክልል ተሻጋሪ ነው።

ሶማሊ ክልል ላይ በአማራ ሕዝብ ላይ ይፈፀመው የነበረው ማፈናቀልና ግድያ በዚህ ወቅት ስለቆመ ሌላ ችግር እንዲፈጠር የሚፈልጉ አካላት አሉ። አንዳንዶቹ ከወለጋ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ "እኛ ጋር ብቻ ሳይሆን ችግሩ ሌላም ቦታ አለ" ብለው የእነሱ ተጠያቂነት እንዲቀንስላቸው የሚፈልጉ አሉ። አማራ በየቦታው ሲሰቃይ የግጭት ቀጠና ፈጥሮ የራሱን ፖለቲካ መስራት የሚፈልግም ሞልቷል። አንደኛው እነ ርዕዮት የሚሰሩበት አጀንዳ ነው።

እነ ርዕዮት እየሰሩ ያሉት ራጆ ከተሰኘ ገፅን ከሚያንቀሳቅሱ ፅንፈኞች ጋር ነው። አብዛኛው መረጃ የሚደርሳቸው በእሱ በኩል ነው። እነ ኤርሚያስም የእነ ርዕዮትን አጀንዳ ተቀብለው አብረው እየሰሩ ነው። እነ ኤርሚያስ ለአማራ የሚያስቡ የሚመስለው የዋህ ካለ ሲገለጡለት ወይኔ ብሎ አይወጣለትም። ዛሬ ከእነ ኤርሚያስ ጋር አጀንዳ እየተጋራ የሚገኘው ራጆ የሚባል ገፅ ሶማሊ ክልል ያሉ አማራዎች እንዲጠቁ ተግቶ ሲሰራ የቆየ ነው። በሀሰት ሶማሊ ክልል ውስጥ ፋኖ ገብቶ እየሰራ እንደሆነ አድርጎ ሲዘግብ የከረመ ነው። ዛሬ የእነ ርዕዮ ሚዲያና የእነ ኤርሚያስ መረጃ ምንጭ ይህ አካል ነው። አላማቸው ተመሳሳይ ነው።

በአንድ በኩል እነ ኤርሚያስ የአማራ ብሔርተኛ ድምፅ አድርገው ስለሚወስዱ ሙስጦፌ በአማራ ብሔርተኞች ተወገዘ እያሉ ነው። የአማራ ብሔርተኛ ሙስጦፌን የማወደስን የማውገዝም ተልዕኮ ሊኖረው አይችልም። ስለ አማራ ሕዝብ ይመለከተኛል የሚል ግን ከዚህም ከዛም እያሉ የህወሃትን አጀንዳ ሲያስፈፅሙ ከሚውሉ ሰዎች ቢጠነቀቅ ለሕዝብ ይጠቅመዋል። እነ ኤርሚያስ በአማራ ስም የዪቱዩብ ገንዘብ ከመሰብሰብ ውጭ ወኪልም እንዳልሆኑ መታወቅ አለበት።