Get Mystery Box with random crypto!

በዩጋንዳ 102 ልጆችና 568 የልጅ ልጆች አባት የሆነዉ ግለሰብ በስተመጨረሻ የወሊድ መከላከያ ለመ | ጠቅላላ እውቀት™

በዩጋንዳ 102 ልጆችና 568 የልጅ ልጆች አባት የሆነዉ ግለሰብ በስተመጨረሻ የወሊድ መከላከያ ለመጠቀም ወሰነ

የ67 አመቱ ኡጋንዳዊ ገበሬ መዚ ሙሳ ሃሳህያ ከ12 ሚስቶች 102 ልጆች እና በስሙ 568 የልጅ ልጆች በማስመዝገብ ግዙፍ ቤተሰብ መስርቷል።ከአንድ በላይ ማግባት ህጋዊ በሆነበት የትውልድ መንደር ሉሳካ በአስከፊ ድህነት ውስጥ ሃሳህያ ቢያድግም በቂ ሀብትና ክብር በማካበት ለብዙ አስርት አመታት የመንደር ሊቀ መንበር ሆኖ ለመሾም እና ለማግባት ሲተጋ ቆይቷል።

ሃሳህያ የመጀመሪያ ሚስቱን በ1971 በ16 ዓመቷ ያገባ ሲሆን 12 እስኪሞሉ ድረስ አዳዲስ ሚስቶችን ማግባቱን ቀጥሏል። አባቴ ሁለት ልጆችን ብቻ ስለወለደ፣ ዘራችን ሊጠፋ ይችላል የሚል ስጋት ነበረብኝ ሲል ገልጿል፡፡

ሟቹ አባቴ ምዋማዲ ሙዱምባ ሁለት ሚስቶች ነበሩት ግን ሁለት ልጆችን ብቻ ነው የወለደው። ይህም የቤተሰባችን የመጥፋት አደጋ ላይ ጥሏል ሲሉ መዚ ሙሳ ሃሳህያ ለኡጋንዳው ሞኒተር ጋዜጣ ተናግረዋል።ከሃሳህያ ልጆች መካከል አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ከእሱ እና ከሚስቶቹ ጋር አብረው የሚኖሩ ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ ወጥተው የራሳቸው ቤተሰብ መስርተዋል። የ67 ዓመቱ አርሶ አደር በቤት ውስጥ ያሉትን ልጆች በስም እንደማያውቃቸው ተናግሯል።ከዚህ በኃላ ባለው ህይወቱ የወሊድ መከላከያ ለመጠቀም መወሰኑን ገልጿል።

@General_knowledge_st
@General_knowledge_st