Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለኹላችኹም ይኹን! ግእዝን በርቀት በ ፲፩ኛ ዙር ለመማር የተሰባሰባችኹ ወንድሞቼና እኅቶቼ | Geez Daily ግእዝ

ሰላም ለኹላችኹም ይኹን!

ግእዝን በርቀት በ ፲፩ኛ ዙር ለመማር የተሰባሰባችኹ ወንድሞቼና እኅቶቼ እንኳን
በደኅና መጣችኹ!

ግዛቸው ደጀኑ እባላለኹ።
እስካኹን "ግእዝን በርቀት" በተሰኘ መርሐ
ግብር በቴሌግራም በ፲ ዙሮች በብዙ ሺሕዎች ለሚቈጠሩ ተማሪዎች ስለ ግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርትን ሳካፍል ቈይቻለኹ።

አኹን ደግሞ የእግዚአብሔር መልካም
ፈቃድ ኾኖ ለ፲፩ ኛ ጊዜ ከእናንተ ጋር
ለኹለት ወራት ስለ ግእዝ ቋንቋ እየተነጋገርን አብረን እንቈይ ዘንድ በዝግጅት ላይ ነኝ።

በመኾኑም ትምህርቱን ለመጀመር የመመዝገቢያውን ጊዜ መወሰን አስፈላጊ ኾኗል።

በተለያየ ምክንያት የግእዝ ቋንቋን መማር ለሚፈልጉ ኹሉ የመጨረሻው የምዝገባ
ጊዜ እስከ

#ሰኔ_፲፪ , ፳፻፲፬ ዓ.ም ማታ ፲፪ ሰዓት

ድረስ ብቻ መኾኑን እየገለጽኹ ከተገለጸው
ቀንና ሰዓት በኋላ መግባት የማይቻል በመኾኑ ግእዝን በርቀት ያለምንም ክፍያ በነጻ መማር የሚፈልግ ማንኛውም ሰው እንዲገባ ለቤተሰቦቻችኹ፣ ለጓደኞቻችኹ ወይንም
የግእዝ ቋንቋን መማር ለሚፈልግ ኹሉ ሊንኩን በመላክ እንድትጋብዟቸው አደራ እያልኹ እስካኹን በትዕግሥት ስትጠብቁ ለነበራችኹ ኹሉ ምስጋናዬ ከልብ ነው። ትምህርቱ ቀለል ባለ መንገድ ስለሚሰጥ ዕድሜአቸው ከ 10 ዓመት በላይ የኾኑ ኹሉ ቢገቡ ውጤታማ ይኾናሉ።

በቅርቡ የምዝገባ ጊዜው ሲጠናቀቅ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በድጋሚ እንገናኛለን።

#ማሳሰቢያ፦
አንድ ሰው ለ፲፩ኛ ዙር ትምህርት ተመዘገበ የሚባለው በዚህ ቻናል ውስጥ ከገባ ብቻ ነው። ለምሳሌ እናንተ ኹላችኹም ተመዝግባችኋል ማለት ነው።

ከዚህ በታች ያለውን መልእክት ደግሞ
እናንተ ቢያንስ ለአንድ ሰው በመላክ አስተላልፉ።


▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭

የግእዝ ቋንቋን ባሉበት ሀገር ኾነው
ያለምንም ክፍያ ለኹለት ወራት በቴሌግራም አማካኝነት ግእዝን በርቀት በ፲፩ኛ ዙር
ይማሩ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።

ትምህርቱ የሚተላለፍበትን ቻናል ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ።

@Geezdistance11

ለትምህርቱ የምዝገባ የመጨረሻ ጊዜ
#ሰኔ_፲፪ , ፳፻፲፬ ዓ.ም ማታ ፲፪ ሰዓት
ድረስ ብቻ በመኾኑ ይህ ዕድል እንዳያመልጥዎት አኹኑኑ ይመዝገቡ።


▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭