Get Mystery Box with random crypto!

#ስንክሳር ነሐሴ_22 #ነቢዩ_ሚክያስ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነ | ገድለ ቅዱሳን

#ስንክሳር ነሐሴ_22

#ነቢዩ_ሚክያስ

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ ሁለት በዚህች ቀን ታላቅ ነቢይ የሞራት ልጅ ሚክያስ አረፈ። ይህም ነቢይ በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት በመናገር አስተማረ።

ስለ ጌታችን መውረድም እንዲህ አለ። እነሆ እግዚአብሔር ከልዑል መንበሩ ወደዚህ ዓለም ይወርዳል ።

ሁለተኛም ሰለ ልደቱ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ የኤፍራታ ዕጣ የምትሆኚ አንቺም ቤተ ልሔም የእስራኤል ነገሥታት ከነገሡባቸው አገሮች አታንሺም ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና ።

ስለ ምኵራብ መቅረት፣ ስለ ቤተክርስቲያን በዓለም ሁሉ መታነፅ ትንቢት ተናግሯል። ዳግመኛም ስለ ሕገ ወንጌል መሠራት ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል አለ። የትንቢቱም ወራት ሲፈጸም ወደ በጎ ሽምግልና ደርሶ ወደ ወደደው እግዚአብሔር ሔደ።

የትንቢቱም ዘመን ከጌታችን መምጣት በፊት በስምንት መቶ ዓመት ነው። ማርታ በምትባልም ቦታ ተቀበረ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
https://t.me/Gedelat