Get Mystery Box with random crypto!

#የጊዜ_ስኮርት_የለውም ገንዘብህን ለጠየቀህ ሰው ሁሉ አፍሰህ ትሰጣለህ? ገንዘብ ለጠየቀ ሰው | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

#የጊዜ_ስኮርት_የለውም

ገንዘብህን ለጠየቀህ ሰው ሁሉ አፍሰህ ትሰጣለህ?

ገንዘብ ለጠየቀ ሰው ሁሉ ታፍሶ ካልተሰጠ፣  እና ታዲያ ውዱን ጊዜህን እንዴት ለማንም  ትሰጣለህ?

ገንዘብ ከተረፈህ ባንክ ልታስቀምጠው ትችላለህ።

ልታበድረው ወለድም ልታገኝበት ትችላለህ። ገንዘብ ከሌለህ ልትበደር አልያም ሰርተህ ልታገኘው ትችላለህ።

የጊዜ ትርፍ ግን የለውም። ሲተርፍህ ለሰው ልታበድረው ወይም ሲያንስህ ከሰው ልትዋሰው አትችልም።

የጊዜ ስኮርት የለውም!!

ያለህ ጊዜ ተመጥኖና ተሰፍሮ ነው የተሰጠህ።

ስለዚህ ጊዜና ትኩረትህን ለጠየቀህ ሁሉ አትስጥ። ሶሻል ሚዲያ ላይ፣ በፌስቡክ እና በቲክቶክ፣ በቲቪ ሰዎች የሰሩትን በማየት እንዲሁ ጊዜህን በከንቱ አታባክን።

ጊዜህን እራስህን ለመስራት ተጠቀምበት።

ሕይወት እና ጊዜ ዋጋ ለሌለው ነገር ሊሰጡ አይገባምና።

#የሕይወት_ኬሚስትሪ መጽሐፍ #
@gasha_tube