Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉም ሲናገር ያን ጊዜ ዝም በሉ ! « እናንተ ተማሪዎች ናቸሁ። አርቆና አቅርቦ የሚያይ ዓይን ፣ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

ሁሉም ሲናገር ያን ጊዜ ዝም በሉ !

« እናንተ ተማሪዎች ናቸሁ። አርቆና አቅርቦ የሚያይ ዓይን ፣ እያጠለለ የሚሰማ ጆሮ ፣ ያየውንና ያደመጠውን ደግሞ የሚጠይቅ በሚዛናዊነት የሚተነትን የሠለጠነ አእምሮ ያስፈልጋችኋል።

ስኬታማ ሰዎች አእምሯቸውን የመቆጣጠር አቅም ያላቸው ናቸው ። ከአንደበታችሁ ይልቅ ጆሮዎቻቸሁ ክፍት መሆንን መልመድ አለባቸው ። በሰማችሁት ሳይሆን በተናገራችሁት ነገር ሰው ታስቀይማላችሁ። የልቡና ስፋት ሳይሆን የምላስ መርዘም አገር ያጠፋል። ሁሉም ሲናገር ያን ጊዜ ዝም በሉ ። በጸጥታችሁ ሰላም ይፈጠራል። ልሰማ ባይ በበዛበት ስፍራ አድማጭ ሁኑ። በዝምታ ውስጥ ያለ ያስተውላል። በልባቸው የምታስቡትን ፣ በአንደበታችሁ ፣ የምታናገሩትን በድርጊታችሁ የምትገልጹትን ለይታችሁ እወቁ ።

በገዛ ጥረታችሁ ከእነዚህ ሦስት ነገሮች የምታገኙት በምክንያታዊ ስሌት ነው አስቡ ። በጉዟችሁ በስተመጨረሻ የአስተሳሰባችሁን ፣ የአነጋገራችሁን ፣ የድርጊታችሁን በፍሬ ታገኛላችሁ ። »
የልቡና ስፋት ሳይሆን የምላስ መርዘም አገር ያጠፋል !

Yonas Zewde
@gasha_tube