Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱን የህግ ከለላ አነሳ የአዲስ አበባ ከተማ | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱን የህግ ከለላ አነሳ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ያለመከሰስ መብት ያላቸውን የምክር ቤቱ አባል የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱን የህግ ከለላ በአብላጫ ድምፅ አንስቷል።

ምክር ቤቱ ውሳኔውን በ93 ድጋፍ እና በ6 ድምፀ ታእቅቦ አፅድቋል።

የከተማውን ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂን በበላይነት የሚመራው የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱን የህግ ከለላ የፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት እንዲነሳ በአብላጫ ድምፅ አንስተዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባልና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ እንዲነሳ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው ከለላው እንዲነሳ የወሰነው።

የህግ ይነሳልን ጥያቄው ከቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር ፍትህ ሚኒስትርን ደብዳቤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል።

@gasha_tube