Get Mystery Box with random crypto!

45 የሸኔ ታጣቂዎች እርምጃ ተወሰደባቸው በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ቴንዘ ቀበሌ ትምህርት | ጋሻ ƬƲƁЄ ꍟ꓄ꃅꀤꂦᖘꀤꍏ

45 የሸኔ ታጣቂዎች እርምጃ ተወሰደባቸው

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ቴንዘ ቀበሌ ትምህርት ቤትን እንደ ካምፕ ሲጠቀሙ በነበሩ የሸኔ ታጣቂዎች ላይ በተወሰደ እርምጃ 45 የቡድኑ አባለት መደምሰሳቸው ተገለፀ።

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በሸኔ ታጣቂዎች ላይ እየወሰዱ በሚገኘው ተከታታይ እርምጃ ትናንት ማለዳ አካባቢ በተከናወነው ኦፕሬሽን ከተደመሰሱት 45 የሸኔ ታጣቂዎች በተጨማሪ ሁለት የቡድኑ አባላትና 35 ክላሽ ጠመንጃዎች እንደተማረኩ ኢዜአ ምንጮችን ጠቁሟ ዘግቧል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን ቢላ ወረዳ ቢሎ እና ጎቤ በተባሉ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰው የአሸባሪው የሸኔ ቡድንም በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየተወሰደበት የሚገኘውን የተጠናከረ እርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ ተፍረክርኮ እየተበታተነ መሆኑን የገለፁት ምንጮች ቡድኑ ቦታ ለመቀየር እየሞከረ መሆኑን አመልክተዋል።

መንግሥት በሕዝብ ላይ ሽብር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ በሚገኘው አሸባሪ ቡድን ላይ የተጠናከረ ህግ የማስከበር እርምጃ እየወሰነደ እንደሚገኝ መግለጹ ይታወቃል።

@gasha_tube