Get Mystery Box with random crypto!

ይቺ ልቤ ዘላል ነች ... አይነኩ ቅኔ ትቀኛለች ይህ ቀልቤ ውልብታ ነው ....የመ | BEST shopping

ይቺ ልቤ ዘላል ነች
... አይነኩ ቅኔ ትቀኛለች
ይህ ቀልቤ ውልብታ ነው
....የመገፈፍ ቆሌ ስንኝ የቋጠረው

ነፍሴ ጤዛ ጠዋት ጦማ
ልቤን ነግራ
አቅሜን መክራ
ማታ ገድፋ የምትገባ
ቅርፊት ብቻ ባየችው ትልም የምትለማ።

'ርግማን አይሉት በአንዲት አሮጊት
ሳያቅ በገፏት ጊዜ ለሰራት
መስቀል ታቃፊ ሀሙስ ለቀራት

ምርቃት አይሉት ሰንበተ እለት ሽልንግን ማፍሰስ
ዝክር ለሞቱት ፍቅርን ለጠማው ምግምን ማጎረስ
ከቤክስቲያን ለጠቀመጡ ገብረ ክርስቶስ።

እንጃ መሐል ሲሰራኝ ተፈጠር ሲለኝ
ብቻዬን ገንጠል ገሰው መገለል
ቅብዝብዝ ፍየል
ምንኗን የምትገልጥ ሰማይ የምታይ ዕጣዋ ገደል።

ከ'ዚም ሲያጸድቀኝ ...
የበግ የዋህ ዓይነ ግቡ
ብቻን መብላት የሚፈሩ
ወዳጅ ጠርተው ሚመገቡ
መንጋ ህብረት......የልብ ስክነት።

ከአዋልላላ ሜዳ ሲያንከራትተኝ
መሄድ የጀመርኩ መድረስ ያቃተኝ
እኔ...........ነኝ

ታዲያ

ይቺ ልቤ... ስትቀኝ
ይህ ቀልቤ.... ሲርቀኝ
ደግሞም ነፍሴ... ስታንቀኝ

በፊቴ ሽብሻብ ሲያሳብቅ
ጀንበር ስጠልቅ ሲስቅ
ህይወት ጣዕሟ ሲርቅ
* * *
መተት ተብትቦ ዓመድ አስሮብኝ
ከመንበር ቆሞ ጊዜ አሾፈብኝ።