Get Mystery Box with random crypto!

ልዬ የጸሎት መርሐ ግብር ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ ድንግል | ፍሬ ሃይማኖት

ልዬ የጸሎት መርሐ ግብር

ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ

ድንግል ሆይ በቤተልሔም ከአንቺ የተወለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስ ያሟሟቁትን አሳስቢ

ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋራ ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ

ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደው ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ

ድንግል ሆይ ረኃብና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከእርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ

ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ
ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ

ቅዳሴ ማርያም


የፍልሰታ ለማርያምን ፆም ምክንያት በማድረግ በሰ/ት/ቤታችን ከ ለሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 13 ቀን ድረስ ልዩ የፀሎት መርሐ ግብር ከምሽቱ 12 ፡ 30 - 1 ፡ 15 ድረስ ተዘጋጅቷል ሁላችሁም የመርሐ ግብሩ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ እናሳውቃለን