Get Mystery Box with random crypto!

#MoE በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች #የዩኒቨርሲ | Free Education Ethiopia ✔️︎

#MoE

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች #የዩኒቨርሲቲ_ምደባን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ ማብራሪያ

የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-

1. በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1,000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

2. የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

3. የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡

4. የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞችና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5. በተቋማት የጾታ ተዋፅኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋፅኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል።

6. የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ያግዛል፡፡

7. የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር ያግዛል፡፡

8. የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው፡፡ በመሆኑም በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡

9. በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡

10. ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል።

11. የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል ዕድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምትውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል።

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!