Get Mystery Box with random crypto!

FOCUS IN'T MINISTRY

የቴሌግራም ቻናል አርማ focusinternationalministry — FOCUS IN'T MINISTRY F
የቴሌግራም ቻናል አርማ focusinternationalministry — FOCUS IN'T MINISTRY
የሰርጥ አድራሻ: @focusinternationalministry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.84K
የሰርጥ መግለጫ

NEW CREATION MANIFESTATION
👉በዚህ ቴሌግራም ቻናል #በፎከስ #ሚንስትሪ #ትምህርቶች ይቀርባሉ፡፡
እንዲሁም
#የፀሎት#የነፃ መውጣትና#የፈውስ አገልግሎት የምትፈልጉ#እንዲመለስላችሁ የምትፈልጉትን#ጥያቄ ያላችሁ#Facebook ላይ
👉 #Woubshet #Humaso የሚለውን #follow
        👉በማድረግ ማቅረብ ትችላላችሁ 👇
https://www.facebook.com/whumaso

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 10:23:31 #በረከት_ዘፍ 13-4-7
በአብርሃም እና በሎጥ መካከል የተፈጠረው ችግር የበረከት ነው በረከት ሲመጣ በረከቱን መሸከም የሚችል ቦታ ስለሌላቸው ተጣሉ

#የፍላጎት_ልዩነት
እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ፍላጎት አለው ነገር ግን  ያ ፍላጎት በራሱ ጥፋት አይደለም - ያንን ፍላጎት ሊያገኝ የሚሔድበት መንገድ ሰዎችን ያጣላል

#የአመለካከት_ልዩነት (understanding)

#ለውጥ_ አንዳንድ_ሠው #ለለውጥ ልቡ ዝግጁ አይደለም - አንዳንዱ ደግሞ ለለውጥ ዝግጁና ለውጥ አምጪ ነው የሁለቱ ሀሳብ አለመግባባት ጥል ይመጣል

#የራዕይ_ልዩነt__ ይሕ ማለት የኔ ብቻ ነው የሚል ሀሳብ ልዩነት ይፈጥራል ---
ሁሉም አስፈላጊ ነው በመስማማት መስራት ማገልገል አለብን

#ስፍራን_አለማወቅ_እያንዳንዱ የየራሱ ስራ አለው ነገር ግን አንዱ የአንዱ ስራ ውስጥ ሲገባ ፀብ ይፈጠራል 

#ስጋዊነት

#ሚስ_አንደርስታንዲንግ ( miss understanding

#ወሬ_ወሬ_ማለት_አንዳንድ_ሰው እራሱን ከማመን ይልቅ ፣ የእግዚአብሔርን ድምፅ ከማስማት ይልቅ  ፣ ቤቱን ከመስማት ይልቅ ጓደኛን ፣ ቤተስብን መስማት ይቀለዋል ይሄ ደግሞ ግጭት ይፈጥራል

#የራስን_ኃላፌነት_በአግባቡ_ አለመወጣት

#መርሕ_አልባ_ሕይወት_ሲኖር ግጭት ይፈጠራል  _ እያንዳንዱ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ሰረዓት አላቸው ብዙዎቻችን ሁሉን ነገር በቁጥጥራችን ስር ማድረግ እንፈልጋለን :ነገሮችን order አናደርግም ለምሳሌ በቤተክርስቲያን ውስጥ ኳይሮች ጋር ተጠያቂ _ፀሎት ሕብረት ጋር ተጠያቂ :

#ችግርን_ለመፍታት

1 #ፍቃደኝነት
ለመታረቅ ያልተዘጋጀን ልብ ለማስታረቅ መሞከር ልፋት ነው

2 #ግልፀኝነት አንድ ሠው ፍቃደኛ ከሆነ ቡኋላ የተፈጠረውን ችግር በግልጽ መነጋገር አለበት .

3 #እራስን_በመግዛት
በስሜት የተለያዩ ሚስጥርን እንዳንናገር _መናገር ያለብንን ነገር በማወቅ

4..focus on love እና በአላማ ላይ   :: https://t.me/focusinternationalministry

https://t.me/focusinternationalministry
211 views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:47:00
ጽድቅ የማገኝው ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሰርቶ የጨረሰውን ስራ በማመን ብቻ ነው (ጽድቅ በማመን ብቻ ነው የሚገኝው ነው) ኤፌ 2:8

በማመን ያገኝነውን ጽድቅ በምንሰራው ኋጢአት አናጣም ( በማጨስ፣ በመጠጣት፣ ሰው በመግደል ፣ሀጢአት በምንላቸው ስራዎች አናጣውም)
በብሉይ ኪዳን የበጎችና የፍየሎች ደም  በአመት አንዴ በማቅረብ ሀጢያት ይከደን ነበር የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ግን ለአንዴና ለመጨረሻ መሰዋት ሆኖ ለሀጢያታችን ቀርቧል ።( ስለዚህ ጽድቃችን ወላለማዊ ነው )ዕብ 9;28

በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ አዲስ ፍጥረት የሆነም ፣ያላመነ ሰው በሚሰራው ሀጢያት ወደ ሲኦል አይገባም ።  ሰውን ወደ ሲኦል የሚገባው ሲጋራ ስላጨሰ አይደለም፣ሰው ስለገደለ አይደለም፣ስለሰረቀ፣ስላመነዘረ፣ስለዘሞተ፣ብዙ አጢያት የምንላቸውን ነገሮች ስለሰራ አይደለም ። ሰው ወደ ሲኦል የሚገባው በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ተሰርቶ የተፈጽመውን ስራ ባለማመኑ ብቻ ነው ።

ሰው የሚሰራው ሀጢያት ወደ ሲኦል ይከተዋል ካለን ወይም የሚገባ ቢሆን ኖሮ ማንም ሰው አይቀርም ። ምክንያቱም ትንሽና ትልቅ የሚባል ሀጢያት የለም ሁላችንም እንሰራለን ፣ምን አልባት ሰው አልገደልን ይሆናል ግን ወንድሞቻችንን እንዋሻለን ፣አላጨስን ይሆናል ነገር ግን በጓዳ የምናደርገው ስንት ሀጢያት አለ ፣በየ ሚድያዎች እንዲሁም በየ መስሪያ ቤቶቻችን በቤተክርስቲያን በየ ቦታው ብዙ አይነት ሀጢያት እንሰራለን ስለዚህ በምንሰራው ሀጢያት ሲኦል እንገባለን ማለት ነውን ? አይደለም የምናደርጋቸው ሀጢያት በራሳቸው ውጤት አላቸው ; ሀጢያትን እያደፋፈርኩ አይደለም ።

https://t.me/focusinternationalministry

https://t.me/focusinternationalministry
131 views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:55:10 የኢየሱስ ስም ሐይል 8ቱ መርሆች :-
. /#ወንጌል ስለ #ኢየሱስ/ ስለ #ህይወት/ነው !
#ፓስተር #ነብይ ነን ባይ #ኮሜድያን #ሸቃጮች ተመለሱ
#ፀጋና #ሐዋርያነት #የተሰጠን ስለ #ኢየሱስ #ለመስበክ
ሐዋ1፥5
#በኢየሱስ ስም ላይ #አትጨማምሩ #ብቻውን #በቂ ነው
ሐዋ4፥12ፊሊ2፥9, ከሲኦል ለመዳን ፣ለፈውስ ፣ለአርነት
#የሐዋርያትና #የመንፈስ ቅዱስ #ምስክርነት ስለ #ኢየሱስ
ሐዋ5፥32
የእግዚአብሔር ክብር መንፈስ ቅዱስ በሐይል እንዲገለጥ
በህወታችን በቤተክርስቲያን ከፈለግን ኢየሱስን እንስበክ
ሐዋ3፥6, ሐዋ4፥29-31 ሐዋ8፥4-8,12 ,ዩሐ14፥26
የኢየሱስ ስም በህይወትህ እንዲሰራ 8ቱ መርሆች፦
ዮሐ6፥69,ሐዋ4፥12 ፊሊ2፥9 ሉቃ10፥17,ዩሐ3:6
1/የኢየሱስን ስም እወቅ ስሙ ማንነቱ ነውና
2/በኢየሱስ ስም እመን ስሙን ታመን
3/የኢየሱስን ሰም ጥራ ፣በስሙ እዘዝ ፣በስሙ ፀልይ
4/የኢየሱስን ስም አክብር፣ፍራ፣ቀድስ በልብህ በአንደበትህ
5/በኢየሱስ ስም ታዘዝ ፣ተቀበል፣ስጥ፣ በስሙ አድርግ
6/ስለ ኢየሱስ ስም ተናገረ፣ስለ ስሙ አስተምር ስበክ
7/ስለ ኢየሱስ ስም መከራን ተቀበል ፣ተነቀፍ ክብርህ ነው
8/የኢየሱስን ስም ምትጠራ ከሆነ ከአመፅ ራቅ ተቀደስ




https://t.me/focusinternationalministry

https://t.me/focusinternationalministry
278 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:38:18 ወደ እግዚአብሔር ቃል እንመለስ
ኤር2:31   FOCUS ON THE WORD IF GOD
"     ትውልድ ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ተመልከቱ"
                    ከቃሉ የራቀ ትውልድ:-
የሚያምነውን አያውቀውም ስለ እግዚአብሔር አያውቅም
እምነቱ የሚዋዥቅ ፣በስሜት የሚነዳ፣ቶሎ ተስፋ የሚቆርጥ
በክርስቶስ ያለውን ማንነት ስለማያውቅ በማንነት ቀውስ ይጠቃል
በተለያዩ የተሳሳቱ  ትንቢቶችና እና ልምምዶች ይስታል
በሐሰት ትምህርቶች እና የህግ ስርአቶች የተተበተበ ነው
በአእሮው መታደስ ስለማይመጣ በኑሮው አለምን ይመስላል
በጠላች ፈተናና ሽንገላ በቀላሉ ይወድቃል  ይጠመዳል
የፅድቅ ኑሮ ላይ ያመቻምቻል አቋም የሌለው  ነው ሚሆነው
ፀሎቱ ፣መዝሙሩ፣ ንግግሩ ሁሉ ከቃሉ የተቃረነ ነው
በአነቃቂ ንግግሮች  እንጂ በፅድቅ ቃል አይታነፅም
ጠንካራ መሰረት የሌለው በአሸዋ ላይ እንዳለ ቤት ነው
የእግዚአብሔርን ፈቃድ፣ አላማ፣ድምፅ ለይቶ አያውቅም

https://t.me/focusinternationalministry
362 views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:39:44 #የጻዲቅ_ሰው_ሕይወት

የጻዲቅ ሕይወት ሙሉ ቀን እስኪሆን ,,,ምሳ 4:18
#ጽድቅ ማለት ማንነት ነው
#ጽድቅ ማለት በአብ ፊት ሙሉ #ተቀባይነትን ማግኘት ነው
#ጽድቅ ማለት ከእርግማን ውጪ መኖር ማለት ነው
#ጽድቅ ማለት ስልጣን ማለት ነው ።

#የጻዲቅ_ሕይወት_እየተጨመረ ይሔዳል ሲል ኢየሱስ እለት እለት እየመጣ ጽድቅ ይሰጠናል ማለት አይደለም እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ልጁን በመስጠት ልጁም ሕይወቱን በመስጠት አጽድቆናል ።

#ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝ አድርገን ስንቀበል አዲስ ፍጥረት ሆነናል ያኔ በመንፈሳችን የእግዚአብሔር ሕይወት በመንፈሳችን ገብቷል ይሕ በመንፈሳችን የገባው ጽድቅ በነፍስና በስጋችን እለት እለት ፣እየተጨመረ፣ እየተገለጠ እየታየ ይሔዳል ማለት ነው ።ሮሜ 5:5 ቆላ 2:10 2ኛ ቆሮ 5:17

2ኛ ጴጥ 1:2-5 በመንፈሳችን እግዚአብሔርን ለመምሰልና ለሕይወት የሚሆነን ነገር ሁሉ ተሰጥቶናል ስለዚህ ፍቅር ነው የጎደለኝ ፍቅር ስጠኝ፣ ትሁት አድርገኝ፣ልጅህ አድርገኝ፣ሰላም ስጠኝ እያለን መዘመርም መጸለይም የለብንም ብዙ ሰዎች ከቃሉ ውጪ የሆነ ትሕትና የሚመል የትዕቢት ቃል ይናገራሉ ። እኛ በመንፈሳችን የገባውን የእግዚአብሔር ሕይወት ማወቅ አልቻልንም ማለት የለንም ማለት አይደለም ስለዚህ የተሰጠንንና ያለንን ሁሉ ማወቅ አለብን ።

ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ ,,,ሙሉ ቀን እስኪሆን ማለት ምድራዊ ነገር ሟሟላት አይደለም አሜሪካ ሔዶ መኖር አይደለም ያለ ችግር መኖር ማለት አይደለም ።ሙሉ ቀን እስኪሆን ማለት ስለብሬት ማድረግ ሳይሆን አገልጋይ መሆን ማለት ነው ኢየሱስን እስከ መምሰል መሔድ ማለት ነው፣ኢየሱስን መግለጥ ማለት ነው፣ኢየሱስ የኖረውን ኑሮ መኖር ማለት ነው፣እውነትን በጽድቅ በቅድስና መግለጥ መህን ነው ። ሙሉ ቀን እስኪሆን የሚጨምረው ከመንፈሳችን ወደ ነፍሳችንና ወደ ስጋችን ነው ። ከውስጥ ወደ ውጪ ። የእኛ እስታንዳርድ የሕይወት ምሳሌ ኢየሱስ ነው ።

https://t.me/focusinternationalministry
367 views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 10:45:27
የአንድነት ሀይል
ማር 11:1-2

#በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ,እውቀት,ከጸጋ, ቀጥሎ አንድነት ትልቁ ሀይል ነው

#አንድነት የእግዚአብሔር መንግሥት ሀይል እንዲገለጥ ያደርጋል
በቤተክርስቲያን አንድነት ከሌለ የእግዚአብሔር ክብር አይገለጥም አንድነት ከሌለ የበለጠ ስኬት, የበለጠ ሀይል ,አቅም አይኖርም
ለዛ ነው ሰይጣን የቤተሰብን ,የቤተክርስቲያንንና የሀገርን አንድነት ማፍረስ የሚፈልገው ።

#መጸሐፍ ቅዱስ አንድ አሥር ሺ ሁለቱ ደግሞ አሥር ሺ እንደሚያሳድዱ ይነግረናል በዚህ ጊዜ በትዳር ውስጥ የሌላችሁ እህትና ወንድሞች አንድ ነገር ልምከራችሁ

#ምንም አይነት ምክነያት ክሌላችሁ ብቸኝነትን (single) አትምረጡ singleness የአጋንንት program ነው ።

#በቤተክርስቲያን ውስጥ በመከፋፍል ውስጥ ያላችሁ አገልጋዮች የእግዚአብሔር የመንግሥት ሀይል እንዳይገለጥ ለአጋንንት አጀንዳ መንገድ እየሆናችሁ ነው ,ሀዋርያቱ መካከል የአመለካከት ልዩየት የአስተሳሰብ ,የሀሳብ,የባህል,የዶክትሪን ልዩነቶች ነበር ግን የሚሰሩት ለአንድ መንግሥት በአንድ መንፈስ መሆኑንን ተረድተው በመያያዝ በአንድነት አገልግለውም ኖረውም በድል አልፈዋል ።

https://t.me/focusinternationalministry
376 viewsedited  07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 13:59:39
1_#ጽድቅ_ምንድነው ?
#ጽድቅ ማንነት ነው (እግዚአብሔር ያለው አይነት ሕይወት )ዕብ 2:12 2ኛቆሮ 5:21
#ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ሙሉ መብትን ማግኘት ነው (ተቀባይነት ፣ሞገስ፣ድፍረት)
#የተባረክ ማለት ነው (ማንኛውም እርግማን የተሰበረለት ከኩነኔ ውጪ የሚኖር ማለት ነው

@ይሕን ጽድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን አንዴ ካገኝን ቡኋላ ድጋሜ አይወስድብንም ለዘላለም ነው የጸደቅነው
@ጽድቅ በስራ የሚገኝ ሳይሆን በእምነት የሚገኝ ነው ሮሜ 4 ፣18 አብረሃም ሰርቶ ሳይሆን አምኖ ነው የጸደቀው ። እኛም አምነን ነው ያገኝነው እንጂ የረጅም ጊዜ ጾምና ጸሎት ገብተን አይደለም ፤መልካም ስራ ሰርተን አይደለም ።

#እንዴት_ነው ጻድቅ ሕይወቱን የሚጠብቀው ፤ በከፍታም በዝቅታም ከጸጋው ላይ አይናችንን ባለማንሳት እና ህግን ባለመደባለቅ ( በጸጋው መደገፍ)

#በዚህ_ምድር ስንኖር በመንፈሳችን የገባው የእግዚአብሔር ጽድቅ ከውስጥ ወደ ውጪ የሚገለጥ ፤የሚጨመር፤የሚያድግ ነው ።

እንዴት ነው የጻዲቅ ሕይወት እየጨመረ የሚሔደው ? የእውነት እውቀት ሲያገኝና በትጋት ነው (በእውቀት እና በትጋት ይጨምራል )

#ጻድቅ በበጋም በክረምትም እያፈራ ይኖራል (በማንኛውም ሁኔታ ያፋል)
#ጻድቅ ያበድራል እንጂ አይበደርም
#ደጻድቅ ይጠይቃል እንጂ አይለምንም
#ጻድቅ ሁሌ ደስተኛ ነው ።የጻድቅ አሳቡም ብረሃን፣ጥጋብ፣በረከት ነው ስለዚህ በማንነታችን ልክ ማሰብ መኖር አለብን ።

https://t.me/focusinternationalministry
384 views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:58:37
ነፃ ለመውጣት እነዚህን መርሆች እንከተል
ኢሳ 10÷27. ሐዋ  10÷38

በሰው ህይወት ውስጥ ነፃ ለመውጣት እነዚህ አራት ነገሮች ያስፈልጋሉ
1/ የእግዚአብሔር ቃል
2/ የእግዚአብሔር ቅባት
3/ የእኛን ፍቃድ
4/ እስራት ውስጥ እንዳለን ማወቅ

አስራ ሁለት አመት ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ለብዙ አመታት ብዙ መድኃኒት ፍለጋ ተንከራታለች ምንም መፍትሄ አጣች አንድ ቀን ግን በእምነት ፍቃዷን በመስጠት የጌታ የኢየሱስን የልብሱን ጫፍ ብነካ የዘመናት ጥያቄ ይመለሳል ብላ ፍቃዷን የሰጠችው የኢየሱስን የልብሱን ጫፍ በነካች ጊዜ ያ ዘመን ያስቆጠረ የደሟ ምንጭ ቆመ ተፈወሰች

እኛም ዛሬ እግዚአብሔር የቀባቸው ያስነሳቸው አገልጋዮች ጋር ስንመጣ አምነን እፈታለው ጌታ አገልጋዮችን ተጠቅሞ ይፈታኛል ብለን የሆነ መልስ ጠብቀን ነው ልንመጣ የሚገባው ያለ እምነት ፣ ያለፍቃዳችን ብንመጣ ዘመን እናስቆጥራለን እንጂ አንዳች ነገር በህይወታችን አናይም (አይሆንም) ከዚህ ልምድ ምልልስ ነፃ ልንወጣ ልንፈታ ያስፈልጋል ያልተፈታ አይፈታም እኛ ለሌሎች መፈታት ምክንያት ተጠርተናል ያ የሚሆነው ግን ለሌሎች የምንተርፈው እኛ ነፃ ስንወጣ ነው ።
https://t.me/focusinternationalministry
476 views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 10:50:08
.       ቅንነታችንን አንጣል //!  2ቆሮ11:3  
       //   ቅንነት ሲገዛን   ቅንአት  ይዋረዳል //
(( ቅንነት ከእግዚአብሔር ጋር፣ከራሳችን ጋር ፣ከሌሎች ጋር  ከራዕያችን ፍፃሜ  ጋር፣ ከጠላት ውጊያ ጋር የተያያዘ ነው))
1     #ለእግዚአብሔር ያለንን ቅንነት እየዋሸን
       ስለ እግዚአብሔር መልካምን፣ታማኝነት ፣ፍቅር ..
(ስለ እግዚአብሔር ማንነት፣ባህርይ፣ሀይልና:ቃል ይዋሸናል)
2     #ስለ እራሳችን ያለንን ቅንነት
          ከሆነው አሳንሶን በማሳየት
          ከሆነው በላይ እንድናስብ በማድረግ
3      #ስለ ሌሎች ሰዎች ያለንን ቅንነት እንድንካሰስ በማድረግ.....በጎ ህሊና በማሳጣት !
    ሰዎች ቅንነታቸውን የምንጥልባቸው ምክንያቶች
1/ከሰይጣንና ከአለም በምንወርሳቸው ክፉ እውቀቶች !
2/ በቅንነታችን ምክንያት  ሰዎች ሲበድሉን  !!
3/የሰማዩንና የዘለአለሙን ትርፍ በምድራዊውና ጊዜአዊው
      ጥቅምና ትርፍ ስንለውጥ !
https://t.me/focusinternationalministry
509 views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 08:05:47
እግዚአብሔርን ወንጌልን።በቅድስና ኑሮ በመመላለስ
እግዚአብሔርን “”” በመንፈስ ቅዱስ ሐይል ተሞልቶ
እግዚአብሔርን “””””። ገንዘብ ላይ ባለማተኮር
እግዚአብሔርን””””። የቃሉን እውነት ሳንሸቃቅጣ
እግዚአብሔርን”””””። በአላማ ማገልገል ይገባናል
# #SAUDI, #BAHRAN #Beirut በሆነው ሁሉ
ክብሩ ለስራው ባለቤት ለእግዚአብሔር ብቻ ይሁን
በልዪ ልዪ መንገድ በብዙ አብራችሁ በፆምና በፀሎት
የደከማችሁ የፎከስ መሪዎች ፣የፀሎት ቡድን ጦረኞች፣
የፎከስ ተማሪዎች፣የየ ሀገሩ የቤተክርስትያን እረኞች ፣በመገኘት ፎቶ በመነሳት ፣ሼር በማድረግ ፣በመጋበዝ
ለዚህ ሁሉ ድል የተሳተፉችሁ ሁሉ ዋጋችሁ ታላቅ ነው
የዚህ ጉዞ ሙሉ $13,000 ዶላር ወጪ በራሳችን ነው
የረዳን ጌታ ክብሩን ይውሰድ

http://t.me/focusinternationalministry
685 viewsedited  05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ