Get Mystery Box with random crypto!

ከሙዚቃ ምርጫ .. .. ኑሮዬን ኖረሽ ብታይ ትርታዬ ቢሰማሽ ከበዛው ካለኝ ፍቅር ስተቴን | 🦋Fonkaye 🦋💖

ከሙዚቃ ምርጫ

..
.. ኑሮዬን ኖረሽ ብታይ ትርታዬ ቢሰማሽ
ከበዛው ካለኝ ፍቅር ስተቴን ባልተረዳሽ
ባታውቂልኝ መውደዴን ቢጎልም
ከሚገባውስ እያለኝ የነፈኩሽ 1 የለም
አልፎ ቀን ቢያስተምርም
ሰው መግፋት ባንቺ አያምርም
ተይ ግድ የለም
እኔ ግን... ይቅርታ
ባላመንኩት ጥፋት ስሞታ
ይቅርታ.. ልኬአለሁ በላክሽው ትዝታ
ይቅርታ.. በጊዜ ካልመሸ መዋደድ
ይቅርታ..ለእርቅ አያንስም ያለፍነው መንገድ
ሰውን ያጡት ቀን ከቦታ
ይፈራረቃል ተይ ተይ
የምር አይመስልም እውነታ
ይፈራረቃል
አያልቅም ያለም ትወና ይፈራረቃል ተይ ተይ
ግድ የለም ነይ እንደገና
ሁሉን ተይና
..
....
......
እንዴት ጠፋሽ መውደዴ
ቢያመልጠኝ ካፌ አንድ ቃል
ስምሽ ነው ይታወቃል
የኔ አካል
በዚ አለም አንቺን ማጣት
በኔ አቅም ይሄ ቅጣት
ቢከብድም.. እኔ ግን..ይቅርታ
ባላመንኩት ጥፋት ስሞታ
ይቅርታ... ልኬያለሁ በላክሽው ትዝታ
....
...
..
.አህመድ ተሾመ /ዲምቢ @fkrnneeee