Get Mystery Box with random crypto!

#የማረሻው ቅኔ ውዴዬ የኔ ሁሌ የምትጠይቂው አዳዴም ከሜዳው ሽቅብ ስትመለከችው እደው ግራ | 💃እኔ መፃፍ ብችል✍

#የማረሻው ቅኔ

ውዴዬ የኔ ሁሌ የምትጠይቂው
አዳዴም ከሜዳው ሽቅብ ስትመለከችው
እደው ግራ አጋብቶሽ ነብስሽን ያስጨነቃት
ልብ ባትያው እጂ እሷ ራሱ መልሱ አላት
… … … … … … #ጥያቄሽ ፩
እደው የቤሬዎቹ መታሰር ሲገርመኝ
ገበሬው እደራሱ ስሪት መምራቱ ደነቀኝ
እዲህ ነው ያልሺኝ ይሄነው ጥያቄሽ
………… #ልብበይ መልሱን ልገርሽ
በሬዎቹማ ዛሬን የምናያት እኔና አቺነን
እደ አንድ ያረጋቸው ማረሻው ያልሽው
እሱ…እሱማ አንድ ያደረገን ፍቅራችን ነው
እና በሬን ከማረሻ አዋህዶ መሪ የሆነበት
አፈርን ቀምሞ ስጋ አልብሶ ሰው ያሰኘበት
…………#የሰራው ፈጣሪሽ እሱ ነው
እደው እዳይገርምሽ ከዚህም በላይ
ጥበብ ከዚህም በላይ ግርምት በጁነው
………………… #ጥያቄሽ ፪
በርግጥ ልቤ ተደምሟል ደንቆታልም
ያሰረው ፈጣሪ ታሰሪዎቹ እኛ ከሆንም
የሚዘራውስ ዘር ከካ የሚበቅለው
ጥፋት እዲሆንም አረም የሚያበቅለው

ልብሽ የሚሻውን በደንብ አውቄዋለው
ውድዬ አድምጪኝ መልሱም ጥያቄው
ጥያቄ የፈጠረብሽ ልብሽነው መልሱ
የሚዘራውን ዘር ምድር ያመጣው እሱ
ነገንበኛ ተስፋ ዛሬን በኛው ፍሬ የሚያዩት
ልጆቻችን ናቸው በጥንድዮሽ ያፈራናቸው
ታዲ ስናሳድግ ነገንም ስናሳያቸው
ጥፋት እዲመስል የሀሳብ አረም
…………………… #አይቄሬነው

አረሙንም ነቅለን ነገን የምናሳያቸውን
እኔና አንቺ ነን በሬ አስመስሎ ፍቅርን ያለበሰን
መሪሆኖ ትናትን ዛሬን የሚያድስ
የጥበብ የፍቅር ፈርቀዳጅ የሚወደስ

የማረሻው ቅኔ ምን ሆነ መሰለሽ
በልባችን ክፍተት እዳይኖረኝ እዳይኖርሽ
ያሰረው ፍቅርነው ሁሉየሚያስደምምልሽ
በትናት ትውውቅ በዛሬውም ፍቅር
ህያዋዊ ቅኔ ፈቺው የትም የማይኖር
የኛ ሰሪው ፈቺው ፈጣሪ ብቻ ነው
እናም እናት ልብሽን አረጋጊያት
አምላክ የሰራውን የሰው ልጅ አይፈታት

ዛም ነገም ሜዳው ላይ በሬዎችን ስታያ
ከምድር አልፎ አለምን ያስጠበበው
ከቶም የማይቅበት የፍቅር ጀማረው
ዛሬም በእኔና አንቺ በማረሻው ቅኔው
……………… #ጨረሰው
እናም ማታ ማታ ጎንሽ አረፍ ሲል
ጥያቄው ሲመጣ ቤትሽን ተመልከች
ማረሻውን ሳይሆን ልብሽን አትኩሪ
መልሱ ከእሷ አለ በሰራት ፈጣሪ

#ልደት የ አቡካዬ ቃል
@fkrlene
@fkrlene