Get Mystery Box with random crypto!

​​​​┄┉✽̶ ✿ምኞቴ ̶̥✽̶┉┄             ▬▬▬❁ክፍል አንድ▬▬▬            . | የፍቅር መንገድ

​​​​┄┉✽̶ ✿ምኞቴ ̶̥✽̶┉┄
    
       ▬▬▬❁ክፍል አንድ▬▬▬

           ... ረድኤት ከረፋዱ አራት ሰዓት አከባቢ የቤታቸዉን በረንዳ በማፅዳት ላይ ሳለች የግቢያቸዉ
በር ተንኳኳ፡፡ ማን ሊሆን ይችላል? ብላ እያሰበች ወደ በሩ ተጠጋች "አባዬና እማዬ ዛሬ የስራ
ቀን ስላልሆነ ቤት ዉስጥ ናቸዉ፡፡" እና ማን ነዉ? እያለች የግቢዉን በር ጠጋ አለችና "ማን
ነዉ?" አለች "እኔ ነኝ" የሚል ለስላሳ ድምፅ ከዉጭ የተሰጣት መልስ ነበር፡፡ ድምፁን
ከዚህ በፊት ባታዉቀዉም ሰላም ያለ ሰዉ እንደሆነ በድምፁ ስለተረዳች በሩን ከፈተችለት፡፡
በጣም ቆንጅዬ ወጣት ነበር፡፡  "ደህና ነሽ" አላት፡፡ እሷም "ደህና ነኝ" ብላ
ስትመልስለት "የሚከራይ ቤት አለ ብለዉኝ ነበር... አለ እንዴ?" ሲላት የረድኤት አባት
ለረዢም ሰዓት በር ላይ እንደቆመች ስላዬ
"ማን ነዉ?" እያሉ ወደ በሩ ተጠጉ፡፡ ወጣቱንም ባዩ ጊዜ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
ወጣቱ ልጅ ለረድኤት የጠየቃትን ጥያቄ ለአባቷ ለጋሽ ሀብታሙ ደገመላቸዉ፡፡ ጋሽ ሀብታሙም አለ ወደውስጥ ግባ ልጄ፡፡ አሉት  እሺ ብሎ ገባ የሚከራየውን ቤት ገብቶ አየ ስንት እንደሚከራይ ጠየቃቸውና ተስማምተው ቢኒያም ወደ ቤት ተመለሰ ፡፡ ... ከዚህ ጊዜ በኃላ ነበር ረድኤት ቢንያምን ያወቀችዉ፡፡ ቢንያም እጅግ በጣም ዉብና
ማራኪ ልጅ ነዉ፡፡ ሚስቱ ደግሞ ኤደን ትባላለች፡፡ እጅግ ሲበዛ ዝምተኛና ቆንጂዬ ናት፡፡ ቤት
ስለምትዉልና ረድኤትም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብትሆንም ሰመርን ከቤተሰቦቿ ጋር ስለምታሳልፍ ሁሌም አብረዉ ይዉሉ ነበር፡፡
ኤዲ ምንም ያክል ዝምተኛ ብትሆንም ለባሏ ግን ፍቅርን መስጠት የምትችል፤ በተለይ
ሲጫወቱና ሰዉነቱ ላይ እየተንከባለለች ቅብጥብጥ ቅብጥ፤ ሽፍድ ስትልበት... ረድኤት "እኔ በሆንኩ" ብላ ትቀናባታለች፡፡ .
.
..... ቢኒያም ከስራ ሊመጣ አከባቢ ኤዲ እጅግ በጣም ተዉባ ከወትሮዉ በተለዬ ይበልጥ
አምራ የግቢዉን በር ለመክፈት ከቤቷ ወጥታ በሯ አጠገብ ትቀመጣለች፡፡ ልክ በሩ
እንደተንኳኳ ሩጣ ትሄድና ቶሎ ትከፍታለች፡፡ ቢኒያምም እቅፉ ዉስጥ አስገብቶ ሲስማት
ለተወሰነ ሰዓታት የተለያዩ ሳይሆን ለአመታት ተራርቀዉ ተነፋፍቀዉ የተገናኙ ይመስላሉ፡፡
ቢኒያም ፍቅር መስጠት ተክኖበታል፡፡
ሲያፈቅራትና ሲወዳት ምድር ላይ ሌላ ሴቶች እስከመፈጠራቸዉም ረስቶ ነዉ፡፡ ለሱ ሴት
ማለት እሷ ብቻ ናት፡፡ እንደ እናት ያከብራታል፤ ያፈቅራታል በጣም ይሳሳላታል፡፡ ፍቅራቸዉ
እንኳን አብሯቸዉ ለሚኖር ሰዉ ለአንድ ቀን በመንገድ ላይ ያያቸዉ ራሱ ይቀናባቸዋል፡፡
.
....ከግቢዉ ነዋሪም ጋር በጣም ተግባብቷል፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ለብቻቸዉ ባገኛቸዉ ሰዓት "አባባ
ገና ወጣት ነህ አረጁ የሚል ሰዉ ተሳስቷል፡፡ አሁን እኔ እና አንቱ ሩጫ ብንሽቀዳደም
አዝነውልኝ ካልተዉልኝ በስተቀር ትበልጡኝ የለ እንዴ! አንቱኮ ሀይሌ ገ/ስላሴን ያስንቃሉ፡፡" እያለ
ይቀልዳቸዋል፡፡ እሳቸዉም የወጣትነት ጊዜያቸዉ ታዉሷቸዉ በጨዋታዉ ከሳቁ በኃላ "አይ
ልጄ..." ብለዉ ትረካቸዉን ይጀምራሉ፡፡ ለወሬያቸዉ አክብሮ ጆሮ ስለሰጣቸዉ ከስራ
የሚመለስበትን ሰዓት እንደ ኤዲ እርሳቸዉም ይጠባበቃሉ፡፡ በተለይ ደሞ ረድኤት...!

           አስተማሪ የፍቅር ታሪክ
   ......ክፍል 2 ይቀጥላል....

ክፍል 2 እንዲለቀቅ ሸር በማረግ ተባበሩን....

የፍቅር መንገድ
https://t.me/fkr2727

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share የፍቅር መንገድ
https://t.me/fkr2727
የፍቅር መንገድ
https://t.me/fkr2727
┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄