Get Mystery Box with random crypto!

✨ፍካሬ ከዋክብት✨

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkarekewakbt — ✨ፍካሬ ከዋክብት✨
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkarekewakbt — ✨ፍካሬ ከዋክብት✨
የሰርጥ አድራሻ: @fkarekewakbt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 711
የሰርጥ መግለጫ

#በዚህ ቻናል የምታገኙአቸው ነገሮች
_ኮከባችሁን ለማወቅ⭐️
_ስለ ፀባያችሁ♏️
_አነቃቂ ሀሳቦች🤔
_አስገራሚ እውነታዎች🌎
_ጠቃሚ አባባሎች💦
_ግጥሞች📝
_አስተማሪ ታሪኮች💧
any comment
👇👇👇👇👇
@Bruka_plus @Bruka_plus_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 11:42:06 ስለ አስትሮሎጂ ትክክለኝነት ማወቅ ከፈለጋችሁ የግድ ይሄን ማወቅ ወይም ማንበብ አለባችሁ

፩.አሁን እኛ ግሩፕም ይሁን ሌላ ግሩፕ ላይም እንዲሁም መፀሃፍት ላይ ሳይቀር ኮከባችሁን እንድታውቁት የምንጠቀምበት መንገድ ፀሃይ በተወለዳችሁበት ጊዜ የትኛው ዞዲያክ ላይ እንደነበረች በማየት ነው ።

፪. ይሄ የብዙዎቻችሁ ጥያቄ ነው ከአንዱ ግሩፕ ወደሌላው ግሩፕ ወይም ከአንዱ መፀሃፍ ወደ ሌላኛው መፀሃፍ ስናነብ ቀናቶች ይቀያየሩብናል ለምን ? ምክንያቱ ፀሃይ አንድ ዞዲያክ ላይ የምትቆየው ሰላሳ ቀን ወይም አንድ ወር ይህም ማለት ፲፪ቱን ዞዲያኮች ለመዞር ፲፪ ወር ይፈጅባታል እዚህ ጋር ነው ዋናው ሃሳብ የቀረው ፭ አንዳንዴም ፮ ቀናች የዞዲያኮችን ቀናት በትንሹ ከአመት አመት ታሸጋሽጋለች እና ለዚህ መፍትሄው ምንድንነው ለምትሉኝ የዞዲያኮች የመጨረሻ ቀናት ላይ የተወለዳችሁ ካልሆነ ለእናንተ ችግር የለውም ግን የመጨረሻው ቀናቶች ላይ ከሆኑ ማለትም አንድ ወይም ሁለት ማለት ነው እናንተ ከፊት እና ከዋላ ያለውን በማንበብ እናንተን በደንብ የገለፃችውን የእናንተ ኮከብ መሆኑን መወሰን ነው ።
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
42 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:00:25 ሞክሩት

259×የእርሶ እድሜ× 39 = ውጤቱ የእርሶ እድሜ ሶስት ጊዜ ተደግሞ ያገኙታል

Example:- እድሜያችሁ #19 ቢሆን 259×19×39= 191,191ይሆናል
ሁላችሁም ገብታችሁ ሞክሩት

አድሜያችሁ ከ10-99 የሆነ ሰዎች ብቻ
▰ከሆነ ካልሆነ

@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
146 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:12:21 የኮከቦች አስቸጋሪ ባህሪ

ኤሪስ▰▰▰▰▰ ቅናት
ቶረስ▰▰▰▰▰ ግትርነት
ጄሚኒ ▰▰▰▰▰ወላዋይነት
ካንሰር▰▰▰▰▰ጭቅጭቅ
ሊዮ▰▰▰▰▰▰ኩራት
ቪርጎ▰▰▰▰▰ አለመታመን
ሊብራ▰▰▰▰▰ክርክር
ስኮርፒዮ▰▰▰▰ በቀለኛነት
ሳጂታርየስ▰▰▰▰ቂመኛነት
ካፕሪኮርን▰▰▰▰ብኩንነት
አኳርየስ▰▰▰▰▰ትዕቢት
ፓይሰስ▰▰▰▰▰ተጠራጣሪ


share
ጓደኞቻቹን እየጋበዛቹ
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
202 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:54:55 የኮከብ_መጠሪያ_ስም_ሊብራ_ወንድ

የውልደት ቀን ከመስከረም 14 እስከ እስከ ጥቅምት 13

#በሊብራ ውበት አንዴ ከተማረክሽ ለመላቀቅ አስቸጋሪ ነው፣ ልታመልጪው ስትሞክሪ በዚያ ሎጂካዊ ክርክሩ አብረሽው እንድትሆኚ ያስገድድሻል፣ ከዚህ በተጨማሪም ጣፋጭ እና ጨዋ ሆኖ ስለሚቀርብሽ ያናደደሽን ሁሉ ረስተሽ ቁጭ ትያለሽ።

#ነገር ግን ፍቅሩ ውጣ ውረድ የሌለው የላባ ፍራሽ ይሆናል በለሽ ካሰብሽ የዋህ ነሽ ፣ ሚዛኑ ሲስተካከልለት ግን ህይወት ከሊብራ ጋር በፍቅር የምታሰክርና የምታስፈነድቅ ነው እምትሆነው።

#የሚፈልጋትን ሴት ልጅ በቀላሉ በጁ የሚያስገባበትን ጥብብ ታድሏል፣ ሆኖም አንዴ በጁ ካስገባት በኋላ ቀጥሎ ምን ➟እንደሚያደርግ ግራ ይገባዋል፣ እሺ ካሰኛት ቧላ ያቅማማል፣ ይጠቀምባት ወይስ የጋብቻ ሀሳብ
ያቅርብላት? ምን ማድረግ እንዳለበት አያውቅም።

#የሰውን ስሜት መጉዳት ብዙ አይፈልግም፣ እምቢ ማለትን ስለማይችል እና ስለማይሆንለት ጊዜ እያረዘመ ያጉላላሻል ማጉላላቱ ግን በደል መሆኑን ቶሎ አይገነዘብም። አየሽ በሁለት አጣብቂኝ መካካል ያለ ሰው ነው ማለት ነው ፣ ሊብራ ወንዶች ሳይታሰብ ድንገት ልውጥ ማለታቸው የማይካድ ነው ፣ በተለይ በወጣትነት ጊዜ የማጥፋት አዝማሚያ አላቸው ፣ ጓደኝነትና ፍቅርን ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ግራ ያጋቡታል፣ ሊብራ ወንድ ያልተሳካውን ግንኙነት ፈጥኖ ስለሚረሳ ብዙም የስሜት ተጎጂ አይሆንም።

#ሚስጥርሽን አያነፈንፍብሽም (አያውጣጣሽም)፣ የግለሰቦችን ግላዊ ሁኔታ እየቆፈረ ነፃነታቸውን መጋፋት አይወድም፣ አንድአንዴ ደግሞ ማፅናኛውን ፈልገሽ አንድ ሰው ምን ያህል እንዳናደደሽ ሮጠሽ ስትነግሪው " አንቺ ምን ብለሺው ነው? " ብሎ አንቺኑ ሲያፋጥጥሽ ቅር መሰኘትሽ አይቀርም፣ ፍትህ አዛብታላች ብሎ ካሰበ ላንቺ ይቆማል ብለሽ አጠብቂ።

#ሊብራ ወንድ የሴት ጓዳኛውን ውስጣዊ ፍላጎት ባለመረዳቱ የተነሳ ችግር ይፈጠራል፣ ከሊብራ ጋ ስትኖሪ መቻል ያለብሽ አንዱ ፀባዩ ይሄ ነው ። በያንዳንዱ ቀንና ሰዓት ቤቱ እንግዳ አይጠፋም።

#ሊብራ ወንዶች ፈጥነው ትዳራቸውን እንዲያፈርሱ ከሚያደርጋቸው ሁኔታ ውስጥ አንዱ የቤታቸው መዝረክረክ ነው፣ ምስቅልቅል ሁኔታን ይጠላሉ፣ ውስጣዊ እርጋታን ለማግኘት በውጫዊው ሁኔታ ህብር መፍጠርን ይፈልጋል።

#ሊብራን ወንድን ከልብሽ ካፈቀርሽው "እንጋባ" ብለሽ ሃሳቡን አቅርቢለት ፣ ከወደደሽ ለጥያቄው ቅድሚያውን በመውሰድሽ እፎይታ ይሰማዋል፣ እሱ እንደሆነ ያቅማማል።
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
@fkarekewakb

ANY COMMENT @Bruka_plus
228 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 22:31:19 ፍካሬ ከዋክብት
▰ሊብራ
▰ቪርጎ
▰ካንሰር
▰ጄሚኒ
▰ቶረስ
▰ካኘሪኮርን
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
480 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 22:15:42 ▰▰▰▰▰▰▰▰
የዞዳይኮቹ ምልክቶች

___ኤሪስ
___ቶረስ
___ጄሚኒ
___ካንሰር
___ሊዮ
___ቪርጎ
___ሊብራ
___ስኮርፒዬ
___ሳጂታርየስ
___ካኘሪኮርን
___አኳርየስ
___ፓይሲስ
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
@Bruka_plus
262 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:52:28 ይህንን ያውቁ ኖሯል

▰ሙዝ ለጤናችን የሚሰጠን 10 አስደናቂ ጥቅሞች!

ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንድ ሲሆን በውስጡ በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም ፣ ፓታሲየም፣አይረን፣ ዚንክ፣ አዮዲንና ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኢ፣ኤፍን ይዛል።

1- የሀይል ምንጭ ነው:- ሙዝ በውስጡ ቫይታሚን፣ሚኒራል እና ካርቦሀይድሬት በመያዙ ሀይል ለማግኘት ይጠቅማል፡፡

2- ለምግብ መንሸራሸር ይጠቅማል:- ይህም የሚሆነው ሙዝ በውስጡ የቃጫ ባህሪ(ፋይበርነት) ስላለው ነው፡፡

3- የጨጓራ ህመምን ያስታግሳል:- ጨጓራ ጠንካራ ግድግዳ እንዲኖረው እና በጨጓራ ውስጥ ያለውን አሲድነት በመቀነስ ህመምን ያስታግሳል፡፡

4- የልብን ጤንነትን ይጠብቃል:- ሙዝ በፖታሲየም የበለፀገ ስለሆነ ይህም ለልብ ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡

5- ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ አነስተኛ ቅባት እንደዚሁም ብዙ ፋይበር ሰለያዘ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

6- አኔሚያን ለማከም ይረዳል:- ሙዝ በውስጡ በዛ ያለ የብረት ማእድን ስለያዘ ይህም የቀይ የደም ሴልን ማነስ ይከላከላል፡፡

7- ነብሰጡሮችን ከህመም ይታደጋል:- ነብሰጡር ሴቶችን የሚያጠቃ የጠዋት ህመም የሚባለውን ለማከም ይረዳል፡፡

8- የአይንን ጤና ያሻሽላል:- ሙዝ ቫይታሚን ኤን ስለያዘ የአይን በሽታን ይከላከላል፡፡

9- በወባ ትንኝ የተነደፈን ይፈውሳል:- የተነደፈበት ቦታ በሙዝ ልጣጭ በማሸት ከህመሙ ይፈውሳል፡፡

10. ጥርስን ያነጣል፦ በሙዝ ልጣጭ ጥርስዎን ሁልጊዜ ጥርስዎን ሲፍቁ ለአስደናቂ ፈገግታ ይኖርዎታል፡፡

@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
269 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 19:56:17
ማንም ብትሆን የሰው ልጅ
እስከሆንክ ድረስ ትንሽ ነኝ ብለህ አታስብ።
.
.
ትናንሽ ቁልፎች ትላልቅ በሮችን
ይከፍታሉ....ትናንሽ ቃላቶች ትላልቅ
ምክሮች ይሠጣሉ .....ትናንሽ ስጦታዎች
ትላልቅ ደስታን ይለግሳሉ
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
290 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 21:38:43 ስለ ጓደኝነት
▰ጓደኝነት የሰው ልጅ ከሌላው መጣበቅ የመፈለግ ተፈጥሮአዊ ግፊት መግለጫ ከራስ ሲሸሹ የሚያገኙት መጠጊያ ፤ ካለመኖር ጭቆና የአፍታ ነፃነት ማግኛ ፤ ብሶትን በቀልድ ማምለጫ ፤ ችግርን በድጋፍ መውጫ ነው
"ወንድም የስጋ ጓደኛ ነው"
"ጓደኛ ደግሞ የነብስ ወንድም ነው"
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
573 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 19:54:10 ጊዜ

ህይወት እረቂቅ ምስጢር ናት። አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ምስጢራዊ ህይወት እድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን። ይህችንም ከረጢት በውስጧ እድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች።

ከረጢቷ እንዳትሰረቅ ያለ ጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጭ እንዳትሆን ፣ ሀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን።

በከረጢትዋ ውስጥ ያሉት ፈርጦች አንድ ባንድ፣ አንዳንዴም ካንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለ ከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ።

ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜ ያልተጠቀምንባቸው የዕድል ፈርጦች ከጊዜው ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈው ይነጉዳሉ ። ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም። ድህነት የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው እንጂ የአርባ ቀን ዕድል አይደለም።

ምንጭ :- የተቆለፈበት ቁልፍ በዶ/ር ምህረት ደበበ
@fkarekewakbt
@fkarekewakbt
525 viewsвяυкα፩፮¥¤ Ριυѕ , edited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ