Get Mystery Box with random crypto!

፠ ምን ያህል መቅረፅ አለብዎት? የቀረፃው ሰዓት መግባቢያዎችስ ምን ይመስላሉ? | የፊልም ቋንቋ አካዳሚ / Film Language Academy👌

፠ ምን ያህል መቅረፅ አለብዎት? የቀረፃው ሰዓት
መግባቢያዎችስ ምን ይመስላሉ?

ለማይንቀሳቀሱ ነገሮች ፣ ወይም ለአጠቃላይ እይታ (exposition shot) ወይም ለብዙ ሰዎች እይታ፣ ለእያንዳንዱ ሾት ቢያንስ አስር ሰከንዶች ያንሱ።

ሰዎች የሚያወሩበት ወይም ድርጊት ያለበት ትዕይንት ፣ ሲሆን ደግሞ ለቀረፃዎቻችሁ “መግቢያ እና መውጪያ” መቅረፅ ያስፈልግዎታል፤ ይህውም ትወናው ወይም ድርጊቱ ከመጀመሩ ከጥቂት ሰከንዶች በፊት ካሜራውን አስጀምሩት ፣ እና ትወናው/ድርጊቱ ካበቃ በኋላ ለጥቂት ሰከንዶች ያህል ዝምብሎ እንዲቀርፅ ተውት።

ቀረፃውን ራስዎ እየሰሩ ከሆነ(ወይም እራሶ ካሜራማን ሆነው እየቀረፁ ከሆነም ሊሆን ይችላል)፣ ማድረግ ያለብዎት በጣም ጥሩው ነገር ካሜራውን መጀመር እና መቅረፁን ማረጋገጥ ፣ ቀስ በቀስ እስከ አምስት መቁጠር እና ከዚያ ተዋናዮቹን የእጅ ምልክት በመስጠት ወይም ‘Action’‹ጀምር› ብሎ በመጮህ እንዲጀምሩ ማድረግ ነው። ከዚያ ሲጠናቀቅ፣ ቀረፃውን ከማቆምዎ በፊት ሌላ አምስት ሰከንዶች ይቆጥሩ።