Get Mystery Box with random crypto!

፠ መሰረታዊ የቀረፃ ሂደቶች! ★በመጀመሪያ ለውስን የሆኑ እይታዎች ፣ የተለመደውን የዳይሬክቲንግ | የፊልም ቋንቋ አካዳሚ / Film Language Academy👌

፠ መሰረታዊ የቀረፃ ሂደቶች!

★በመጀመሪያ ለውስን የሆኑ እይታዎች ፣ የተለመደውን የዳይሬክቲንግ ፍሬሚንግ ልኬት አውራጣትን እና ሌባ ጣትን በማገጣጠም ክፈፋችሁን/ፍሬማችሁን በመወሰን እንዲቀረፅ ማድረጋችሁን እንዳትረሱ!

★አንድ ሰው አንድ ነገር ሲያደርግ ለማሳየት አስባችሁ ከሆነ ደግሞ፣ በመጀመሪያ መቼቱን በሚገባ ለማስተዋወቅ (exposition shot) ሁለት ረዥም እይታዎች/long shot/ ወይም በጣም የረዘመ እይታ/extrem long shot/ ቅረጹ!

★ከዚያ ደግሞ የግለሰቡን የቅርብ እይታ/Close shot/ ወይንም መሀከለኛ እይታ/Middim shot/ ማግታችሁን አረጋግጡ።

★እና ደግሞ ሰውየው ከሚያደርገው ነገር ጋር መቅረፃችሁንም እንዳትረሱ በተጨማሪ ሰውየውን ለብቻው የሚደረገውን ነገር እንዲሁም የሚደረግበትን ቁስ፣ ነገር ወይም አንዳች አስፈላጊ ሁኔታ ሊሆን ይችላል ለብቻ ቅረፁት።

★በስተመጨረሺያ ደግሞ ሁልጊዜ እርሶ ሊቀርፁ ተዘጋጅተውበት ከመጡት ሁለት ተጨማሪ እይታዎችን/shots/ ቅረፁ።