Get Mystery Box with random crypto!

#የታሪኩ_እርዕስ_ኢምሩ_ከቀብርህ_በላይ #ፀሀፊ_በፎዚያ #ክፍል_አንድ 'አልሀምዱሊላህ በደረሰብኝም | Lovely😍😘

#የታሪኩ_እርዕስ_ኢምሩ_ከቀብርህ_በላይ
#ፀሀፊ_በፎዚያ
#ክፍል_አንድ

"አልሀምዱሊላህ በደረሰብኝም ነገር በሚደርስብኝም ሁሉ አልሀምዱሊላህ ጥራት ይገባዉ ለአላህ አዎ በድጋሚ አልሀምዱሊላህ በፍፁም ስለጌታዬ አንዳች ነገር እንኳን በሚያደርስብኝ ነገር አላዝንም"

<አንተ አማር እብድ ነህንዴ?
<<አልሀምዱሊላህ ጤነኛ ነኝ እህቴ
<ታድያ ወንድምህ ሞቶ አንተ ጭራሽ ፈጣሪህን ታመሰግናለህ
<<አዎ አመሰግነዋለዉ አልሀምዱሊላህ ወንድሜን የሰጠኝም ወንድሜንም የቀማኝም አንድ አሏህ ነዉ በሱ ደሞ አላዝንም።
<ምን እንዴት ኢምሩ በመሞቱ ደስተኛ ነህ ማለት ነዉ?
<<አይ በመጥፎ አታስቢዉ እሱ ግን በመሞቱ አላህን ማሳዘን አልፈልግም ምክንያቱም ከኔ በበለጠ ጀሊሉ ይወደዋል
<የምር ጨካኝ ነህ ጨካኝ እሺ አንተ አረመኔ ከሀዲ ለዚ ክህደትህ ደሞ እሰራልሀለዉ እኔ ሂወቴን ተቀምቼ አንተ ግን ትቀልዳለሀ ብዬ በጥፊ መታሁት እሱ ግን መልስ አልሰጠኝም ቀናም ብሎ አላየኝም አማር ወደ ቤታቸዉ ቀጥ ብሎ ተመልሶም ሳያየኝ ገባ የምር በተናገረዉ ንግግር ተናድጃለሁ።

<ልጄ ምንድ ነዉ የሆንከዉ?
<<ኡሚዬ ምንም አልሆንኩም ምነዉ
<ነስርኮ ከአፍንጫህ እየፈሰሰህ ነዉ
<<አይ አሁን በፀሀይ ስለተራመድኩ ነዉ የነሰረኝ በቃ ልተጣጠብና እመጣለሁ።
<እሺ ቶሎ በል የማወጋህ ነገር ደሞ አለ።

"እኔ አማር እባላለሁ 24 አመቴ ሲሆን ተመርቄ ስራ በመፈለግ ላይ ነኝ ነገር ግን ስራዉ ጠፍቶ ሳይሆን እኔ ዉሎዬ ሁሉ መስጂድ ስለነበር ነዉ።
ቅድም ከመግባቴ በፊት ደሞ የመታችኝ የወንድሜ እጮኛ ነበረች ኒካት በአሰሩ በሳምንቱ የኔ መንትያ ወንድሜና የሷ የሀያት ባል የዱኒያ ህይወቱን ጨርሶ ወደ አኼራ ሄደ እኔ በጣም አዝኛለሁ ግን በአላህ ዉሳኔ ደሞ መግባት ስለማልፈልግ በዱአ ነዉ ሀዘኔን ለመርሳት እየሞከርኩ ያለሁት
እኔና አማር መንትያ ከመሆናችን ጋር ተመሳሳይ ነን ግን ባህሪያችን የተለያየ ነዉ የእዉነት ጭራሽ አይገናኝም ሀያትም እንደሱ ናት የወንድሜ ስሙ ኢምራን ይባላል ኢምሩ ነዉ የምንለዉ በኑሮአችን ደስተኞች ነን ብዙም ባይባል የተወሰነ ነገር አለን አልሀምዱሊላህ እናም
እኔ አሁን የተረጋጋሁ ወጣት ሆኛለሁ ወንድሜ ግን አላህ ይርሀመዉና ዱርዬነት ያጠቃዉ ነበር።

"መንታ ነን ግን ባህሪያችን አይደለም የመንትያነት ይቅርና የወንድማማችነት እራሱ አይመስልም
ኢምሩ ከመሞቱ በፊት በቲኒሹም ቢሆን ስለራሱ ያወራኛል እኔ ግን ስለራሴ አዉርቼዉ አላዉቅም ብቻ ሁል ግዜ ስገድ እያልኩ ቅራ እያልኩ ነበር የምመክረዉ በዚህም የተነሳ ይናደድብኛል
በእርግጥም እኔም ከአመታት በፊት ከሱ የባስኩ ነበርኩኝ እናም ጓደኞቼ አንድ ቀን ግን በሂወቴ ተሳስቼ የማላዉቀዉ ነገር ተከሰተ ከዛን ጊዜ ቡሀላ ነዉ ሁሉን እርግፍ አድርጌ የተዉኩት.....


#ክፍል_ሁለት_ይቀጥላል....

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን