Get Mystery Box with random crypto!

#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ስድስት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ | 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


...."አስተናጋጁ ሁለተኛውን ዙር ምግብ አመጣላቸው፤ ኮተሌትና ሰላጣ ቪኖም ቀዳላቸው:

አባትም የቀረበላቸውን ምግብ በሹካ እየወጉ አፋቸው ውስጥ ከተው
በንዴት ያኝካሉ፡፡ ማርጋሬት የአባቷን ፊት ስታይ ከንዴታቸው በስተጀርባ
የግራ መጋባት ሁኔታ ይነበብባቸዋል፡ እንደዚህ ድንብርብራቸው ሲወጣ
አይታ አታውቅም፡፡ ሰማይ እንደተደፋባቸው ተገንዝባለች ይህ ጦርነት
ራዕያቸውን ሁሉ ድባቅ መቶባቸዋል፡፡ የእሳቸው ፍላጎት የእንግሊዝ ህዝብ
ፋሺዝምን በእሳቸው መሪነት እንዲቀበል ነበር፤ ጭራሽ እንግሊዝ በፋሺዝም
ላይ ጦርነት አውጃ እሳቸውን ለስደት ዳረገቻቸው፡

የተመኙት የፖለቲካ ሁኔታ አፈር መብላቱ ሳያንስ ልጆቹ ደግሞ እያመጹ አስቸገሩ: ፔርሲ ይሁዳዊ ነኝ እያለ ይቀባጥራል፤ ማርጋሬት
ልትጠፋ ሞከረች ከሁሉም በላይ የእሳቸው አስተሳሰብ ተከታይና የአመለካከታቸው ተጋሪ የነበረችው ኤልሳቤት ደግሞ ትዕዛዛቸውን ጣሰች፡

ማርጋሬት ለመብላት ብትሞክርም የጎረሰችው አልዋጥልሽ አላት፡፡
እናትም ‹‹በርሊን ፍቅረኛ አለሽ?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡

‹‹የለኝም›› አለች ኤልሳቤት፡ ማርጋሬት አምናታለች። ማርጋሬት እንደምታውቀው ኤልሳቤት ጀርመንን የምትወደው በሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት ብቻ አይደለም፧ እነዛ ጸዳ ያለ ዩኒፎርም የሚለብሱትና
የሚያብረቀርቅ ጉልበት የሚደርስ ቦት ጫማ የሚያጠልቁት ዘንካታና ጸጉረ ነጭ ወታደሮች ልቧን ሰልበዋታል፡፡ ኤልሳቤት እንግሊዝ ውስጥ መልከ ጥፉ ተብላ ብትቆጠርም ጀርመን ውስጥ ግን የጀርመንን ናዚዝም የሚያደንቅና የሚደግፍ የእንግሊዝ ባላባት ልጅ ናት ተብላ ትከበራለች፡፡ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት መቀስቀሻ ላይ አገሯን ከድታ የመጣች መሆኗ ዝነኛ ያደርጋታል፡፡ እዚያ ‹‹አንበሳ›› ነው የምትባለው፡ከቀናትም አንዱን ወጣት
መኮንን ታፈቀርና ወይም ስልጣን በስልጣን ላይ የጫነ የናዚ ፓርቲ አባል
ታገባና ጸጉረ ነጭ ልጆች ትወልድለታለች፧ ልጆቹም ጀርመንኛ እየተነጋገሩ
ያድጋሉ፡፡

‹‹አሁን ልታደርጊ ያሰብሺው ነገር አደገኛ ነው የኔ ማር፤ አባትሽ እና እኔ የተጨነቅነው ለደህንነትሽ ነው›› አሉ እናት፡፡

ማርጋሬትም አባታችን የኤልሳቤት ደህንነት ያስጨንቀው ይሆን?›
ስትል አሰበች፡፡ እናታቸው ያስጨንቃቸዋል፤ አባታቸው ግን የተናደዱት ኤልሳቤት ትዕዛዛቸውን ባለማክበሯ ነው፡፡ በእርግጥ ከቁጣቸው በስተጀርባ የሩህሩህነት ጭላንጭል ይታያል፡፡ ድሮ እንዲህ ጨካኝና ክፉ አልነበሩም፤ አንዳንዴም ልጆቹን ያጫውቷቸው ነበር፡ ይህ ሁሉ በሃሳቧ መጣና አዘነች።

‹‹አደገኛ እንደሆነ አውቃለሁ, አለች ኤልሳቤት ‹‹የወደፊት እጣ ፈንታዬ በዚህ ጦርነት ላይ የተመሰረተ ነው፤ በይሁዳውያን ባለሃብቶችና
በቆሻሻ ኮሚኒስት የሰራተኛ ማህበራት የተሞላ ዓለም ውስጥ ከምኖር ሞቴን
እመርጣለሁ››

‹‹ታዲያ ከኛ ጋር ሂጂያ
አሜሪካ ጥሩ አገር ነው›› አሉ እናት፡፡

‹‹የአሜሪካ የባንክ ቢዝነስ ማዕከል (ዎል ስትሪት) በይሁዳውያን እጅ
ነው ያለው›› አለች ኤልሳቤት፡፡

‹‹ይሄ መቼም ተጋኗል›› አሉ እናት ፈርጠም ብለው የባላቸውን አይን እየሸሹ፡፡ ‹‹በእርግጥ በአሜሪካ የቢዝነስ ስራ ውስጥ በርካታ ይሁዳውያንና
ብልሹ ሥነ-ምግባር ያላቸው ሰዎች መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡ አያትሽ
ደግሞ የባንክ ባለንብረት እንደሆኑ አትዘንጊ፡፡››

‹‹በሁለት ትውልድ ከቀጥቃጭነት ወደ ባንክ ባለንብረትነት መለወጣችን
የሚደንቅ ነው›› አለ ፔርሲ፡፡ ሆኖም ማንም ጆሮ የሰጠው የለም፡፡

እናትም ቀጠሉና ‹‹በፖለቲካ አመለካከትሽ እኔም እስማማለሁ፤ አንቺም
ይህን ታውቂያለሽ ነገር ግን በአንድ ነገር ስላመንሽ ለእሱ ስትይ ህይወትሽን
ትሰውያለሽ ማለት አይደለም›› አሉ
ማርጋሬት ይህን ስትሰማ ደነገጠች፤ እናታቸው የፋሺስት አስተሳሰብ
ህይወት የሚሰዉለት አላማ አይደለም እያሉ ነው፤ ይህም በአባታቸው ዘንድ
ክህደት እንደመፈጸም ይቆጠራል፡ እናታቸው እንደዚህ አባታቸውን ፊት
ለፊት ሲቃወሙ ማርጋሬት አይታ አታውቅም፡፡ ኤልሳቤትም የእናታቸው
አነጋገር ገርሟታል፡፡ ሁለቱም አባታቸውን ገርመም አደረጓቸው፤ ‹ምን ይል ይሆን?› በማለት፡፡ እሳቸው ግን ፊታቸው በርበሬ ከመምሰሉና በመጠኑ ከማጉረምረም በስተቀር በንዴት አልጮኹም፡፡

ቡና ለተሳፋሪዎች ሲታደል ማርጋሬት ከሳውዝ ሃምፕተን ከተማ ጥግ
መድረሳቸውን ተገነዘበች፡፡ ባቡር ጣቢያ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ
ይደርሳሉ፡ ኤልሳቤት እንደ ፎከረችው ታደርግ ይሆን?›
ባቡሩ ፍጥነቱን ቀነሰ፡፡
ኤልሳቤትም አስተናጋጁን ጠራችና ‹‹የሚቀጥለው ጣቢያ ላይ ወራጅ
ነኝ›› አለችው፤ ‹‹የሚቀጥለው ፉርጎ ውስጥ እመቤት ኤልሳቤት ኦክሰንፎርድ የሚል የተጻፈበት ሻንጣ አለልህ ይዘኽልኝ ና››

‹‹እሺ እመቤት›› አለ አስተናጋጁ፡

ማርጋሬት አባቷን ታያቸዋለች፡ ምንም ቃል ባይተነፍሱም ፊታቸው
በታመቀ ንዴት መወጠራቸውን ያሳብቅባቸዋል፡ ሚስታቸው እጃቸውን እባላቸው ጭን ላይ አስቀመጡና ‹‹እባክህ ሰው እንዳይሰማ ዝም በል፣ የኔ ውድ›› አሏቸው፡፡ ባላቸው ግን መልስ አልሰጡም፡፡

ባቡሩ ጣቢያው ጋ ደርሶ ቆመ::

ኤልሳቤት የተቀመጠችው በመስኮቱ በኩል በመሆኑ ማርጋሬትን አየት ስታደርጋት ማርጋሬትና ፔርሲ መንገድ ለቀቁላት፡፡ አባትም ቆሙ
ተሳፋሪው በሙሉ በአባትና በልጅ መካከል የተከሰተውን ፍጥጫ እንደ ትንግርት ያያል፡፡
ኤልሳቤት ተገቢውን ጊዜ መርጣለች፡ በዚህ ሁኔታ አባቷ ኃይል ተጠቅመው እንደማያስቀሯት አውቃለች፡፡ በፍርሃት ሰውነቷ እየራደ
ቢሆንም፤ ከሞከሩም ሌሎች ተሳፋሪዎች አይፈቅዱላቸውም።

አባቷ ፊታቸው በንዴት ቀልቷል፡፡ ዓይናቸው ተጎልጉሎ ሊወጣ የደረሰ
ይመስላል ኤልሳቤት በፍርሃት ብትንቀጠቀጥም ፈርጠም እንዳለች ነው፡፡

‹‹ከዚህ ባቡር ብትወርጂ ዳግም አይንሽን አላይም፤ መቃብሬም ላይ
እንዳትቆሚ›› አሏት።

‹‹እባክህ አባባ እንዲህ አትበል›› ስትል ማርጋሬት አለቀሰች፡ አባት አንድ ጊዜ ብለውታል፡፡ የተናገሩትን መልሰው ሊውጡት አይችሉም፡፡

እናት ይነፋረቃሉ፡

ኤልሳቤትም ‹‹ደህና ሁኚ እንግዲህ›› አለቻት እህቷን፡
ማርጋሬት እህቷ አንገት ላይ ተጠመጠመችና ‹‹መልካሙን ሁሉ
እንዲገጥምሽ እመኝልሻለሁ እታለም!››

‹‹ለአንቺም እንዲሁ›› አለችና ጀርባዋን መታ መታ አደረገቻት፡

ኤልሳቤት የወንድሟን ጉንጭ ሳመችና ወደ አባቷ ዞራ ድምጿ እየተንቀጠቀጠ ‹‹አባባ አትሰናበተኝም?›› ብላ እጇን ዘረጋች፡

አባትም ፊታቸው በጥላቻ ተጀቡኖ ‹‹ልጄ ከእንግዲህ ሞታለች፤ ልጄ አይደለሽም፧ ክጄሻለሁ›› አሏት፡

እናት ይሄን ሲሰሙ በተስፋ መቁረጥ እዬዬያቸውን አቀለጡት፡

የቤተሰቡ ውዝግብ እንዴት እንደሚጠናቀቅ ለማየት ተሳፋሪው በሙሉ
ትንፋሹን ውጦ ይጠባበቃል፡፡

ኤልሳቤት ፊቷን አዙራ ወደ በሩ አመራች፡፡

ማርጋሬት የአባቷ አድራጎት አበሳጭቷታል፡ ለአንዴ እንኳን እንዴት አይረታም! ስትል አሰበች፡፡ ኤልሳቤት ልጅ አይደለችም። እድሜ ልኳን አባት እናቷ የሚሉትን ሁሉ አሜን ብላ ስትቀበል አትኖርም፡ አባቷ ዕድሜ
ልካቸውን ሊቀጧት መብት የላቸውም፡፡ በቁጡ ባህሪያቸው ቤተሰቡን
ለያዩት፡ እዚያ በንዴት ጦፈው እንደ አበያ በሬ እንደተገተሩ ‹‹የተረገምክ!›፣
ጨቋኝ!›፣ ደደብ›፣ ብትላቸው በወደደች፡ ነገር ግን እንደልማዷ ከንፈሯን
ከመንከስ በስተቀር ምንም ቃል አልወጣትም፡፡