Get Mystery Box with random crypto!

እሱም ዝርዝሩን እንደማያውቅ ነገረኝ። እኔ እንዲነግረኝ ለመኩት።ለማንም እንዳልናገር እና የያቤፅ አ | 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜

እሱም ዝርዝሩን እንደማያውቅ ነገረኝ። እኔ እንዲነግረኝ ለመኩት።ለማንም
እንዳልናገር እና የያቤፅ አባት በህይወት እንዳሉ ሞቱ የተባለው ውሸት መሆኑን
ነገረኝ። ነገር ግን እሳቸው እኔን ማግኘት በሚፈልጉበት ጊዜ እይደሚያገኑኝ
ነገረኝ። ከ3ቀን በኋላ የያቤፅ አባት ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ አልጋው ጠረዝ ላይ
ተቀምጠው አየዋቸው።
፨ፈጥኜ ነበር የተጠመጠምኩባቸው።
ስትል ያቤፅ "አያቴ በህይወት አለ ማለት ነው? ይገረማል" አለ።
ሶስናም "አዎ ልጄ" ብላ ፈገግ አለች። ፅናት "በጣም ደስስ" ይላን አለች።
ያቤፅም ተነስቶ "ማሪኝ እናቴ ማሪኝ ይቅር በይኝ" ሲላት። ሶስና ያቤፅን እና
ፅናትን አቀፈቻቸው። እና " እሺ ልጄ እሺ ሊላ ጥሩ ዜና አለኝ" አለች። ያቤፅ
"ምንድነው" አላት ።
ሶስናም ከእቅፏ ካወጣቻቸው በኋላ። አያትህ ስለ አባትህ ችግር ነግሮኝ ነበር።
አባትህ የአይምሮ ሆስፒታል ገብቶ ነበር ግን ደሞ ደና እየሆነ ነው ብለው እኔን
ሳያገኑ እና ልጄም ሳይወለድ ነው ያስወጡት ይህንን ነግረውኝ ሲያበቁ ልጆቸው
መቃብር ጋር ይዘውኝ ሄደው። ልጄን ይቅር በይው አሉኝና ይቅር አልኩት።
፨ የያቤፅ አያት በህይወት የመቆየታቸውን ሚሰጥ ግን ምንም አውቅም በቃ ሊላ
የቀረ ካለ ሊላ ቀን ገና ብዙ ጊዜ አለን።" አለች። ያቤፅም ልክ ነሽ ግን አያቴ
አሁን የት ነው ሲል" ሶስና "ልጄ እሱን አላውቅም እኔም ያን ቀን ነው ያየዋቸው
በሉ አሁን ወደ ቤት ልሂድ" አለችና ተነሳች። ፅናትን ስማት ያቤፅ እስከበር
ሸኝትዋት ሄደች።
ያቤፅ ፅናት እና ሶስና ሁሌም ማታ ማታ ቡና ይጠጣሉ በፀሎት እና ሊባኖስም
በስልክ ያወሯቸዋል። ደመቁም ስራዋን እየሰራች ነው። ዛሬ ማታ ግን ሶስና ያቤፅ
እና ፅናት ቡና ሊጠጡ ተሰብስበው አልያም ደሞ በፀሎትን እና ፅናትን በስልክ
እያወሩ ሳይሆን እነሱን ሊቀበሉ አየር መንገድ ናቸው ሁሉም ተነፋፍቀዋል።
አይናቸውን እያከራተቱ ነው።

ይቀጥላል.....

https://t.me/fetaenbeel