Get Mystery Box with random crypto!

ወልዲያ፣ ሌላኛዋ ማርሽ ቀያሪ! ህወሓት ባለፈው አመት የተለያዩ ቦታዎች ተመትቶ ተዳክሞ ነበር። በ | Fano tv 24

ወልዲያ፣ ሌላኛዋ ማርሽ ቀያሪ!

ህወሓት ባለፈው አመት የተለያዩ ቦታዎች ተመትቶ ተዳክሞ ነበር። በአፋር ተመትቷል። ደባርቅ ላይ ተመትቷል። ጋይንት ላይ ተመትቷል። ደብረሲና ላይ ተመትቷል። ጋሸና ላይ ተመትቷል። ወልዲያ ሌላኛዋ ማርሽ ቀያሪ ነች።

ህወሓት ወያኔ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ አግተልትሎ እንደመጣ ነው መጀመርያ ቆቦ፣ ከዛም እስከ ወልዲያ ባለው መስመር በርካታ ኃይሉን ያጣው። ህወሃት ወልዲያን እይዛለሁ እንዳለበት ሁሉ ደብረታቦርና ደባርቅን ለማያዝ ጥሯል። ካራ ምሽግን ከዛም ደብረብርሃንን ለመያዝ ጥሯል። በእነዚህ ሁኔታዎች ያላደረገው ሙከራ አልነበረም። በአንዱ ሲመታ በሌላው ይሸሻል። በአንደኛው ተመለሰ ሲባል በሌላው ይመጣል። የሰሞኑ ወልዲያን ለመያዝ ያደረገው ትንቅንቅ ደብረታቦርን፣ ደባርቅንና ደብረብርሃንን ለመያዝ መጥቶ ተቀጥቅጦ ከተመለሰበት ጋር ተመሳሳይ ነው።

እንዲያውም የወልዲያው ረዥም ጊዜ አግኝቶ የሰለጠነ ነው። በጥምር ኃይሉና በደጀኑ ሕዝባችን መስዋዕትነት አላማው ተጨናግፏል። ይህ ግን በቂ አይደለም። በተደራጀ መልኩ ከተመታ ወደ ራያና ወልዲያ መስመር የመጣው ኀይል መመታቱ አሸባሪውን ቅስሙን ይሰብረዋል። ወልዲያን አላስነካም ያሉ ጀግኖቻችንን አግዘን ይህን አሸባሪ በሚገባ መቅጣት ከቻልን ኩራታችን ወልዲያ ሌላኛዋ የትግሉ ማርሽ ቀያሪ ትሆናለች። ሸዋ፣ ጋይንት፣ ጋሸና እና ወቅን ላይ የተመታው ትህነግ መግቢያ እንዳጣው ሁሉ አሁን ተረባርበን ወደ ወልዲያ አሰፍስፎ  መጥቶ የነበረውን ማስቀረት ከቻልን የትህነግ ወሽመጥ ይቆረጣል።

መልካም አጋጣሚው ደግሞ የዋግሹም ልጆች ትህነግ የከፈተብንን ወረራ በሚገባ እየመከቱ፣ መልሶ ማጥቃት እያደረጉ በመሆኑ ወደ ራያና ወልዲያ የሄደው ኃይል ትንፋሽ እንዲያጥረው ይሆናል።

ጌታቸው ሽፈራው